ፍርዱን ለሕዝብ… ዛሬ በማለዳ ገርጂ ካዲስኮ ሆስፒታል

habtamu 33ፍርዱን ለሕዝብ… ዛሬ በማለዳ ገርጂ የሚገኘው ካዲስኮ ሆስፒታል አቀናሁበስፍራው የቀድሞ አንድነት ጓዶች ጠበቃ ተማም ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ሀብታሙ አጠገብ ይገኛሉ፡፡ ሰው ለመጠየቅ የሆስፒታሉ መመሪያ ከ11 ሰዓት ጀምሮ ቢሆንምየሕክምና ባለሙያዎች በሚያደርጉት ትብብር በየተራ ለመጠየቅ ፈቀዱልን ሀብታሙ ተኝቶ ባለበት ክፍል ስንገባ የገጠመን የምናቀው ሀብታሙ አይደለም፡፡ ምንም ነገርመናገር አይችልም፡፡ እጅግ አሳዛኝ አደጋኛ ቁጭት በሀዘን የተዋጡ የትግል ጓዶች በለቅሶ ክፍሉ ተጨናነቀ ወገን መናገር ከምችለው በላይ ያሳዝናል፡፡ ኣንድ ዜጋ በግፍታስሮ ከተሰቃየ በኃላ በዚህ ደረጃ በቀል መፈጸም ያውም በመንግስት ሃላፊነት ያለ እንዲህ መውረድ ፍርዱን ለሕዝብ መተው ነው፡ ሀብታሙ ትላንት በማዕከላዊ የግፍእስር ቤት በደረሰበት ኢሰብአዊ አያያዝ ምክንያት ህይወቱ ለአደጋ የተጋለጠ መሆኑ እየታወቀ ወቅታዊ የጤና ሁኔታ ከግምት በማስገባት የከፍተኛው ፍርድ ቤትየተጣለበትን የጉዞ እግድ እንዲያነሳለት እና የተሻለ ህክምና ወደሚያገኝበት ሀገር በመጓዝ ህይወቱን ለማትረፍ ዛሬ ለፍ/ቤቱ ያቀረበው ጥያቄ ግዜ ያስፈልገዋል በማለትለ28/10/2008 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶዋል፡፡ ከዚህ በላይ ግፍ ምን ኣለ?

Sintayehu Chekol

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.