ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ ፌድራል ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ጠቅላይ ሚንስትር – ዓለም አቀፍ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ማሕበር

ጉዳዩ፤ ስለ ቀድሞዉ የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ዓለም አቀፍ ማህበር መቋቋምና የሰብአዊ መብት ጥያቄ

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር

logo-formerethiopianarmedforceworldwideበቅድሚያ እኛ በመላዉ ዓለም በስደት የምንገኝ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች አባላት በአንድነት ከምድር ጦር ፣ ከአየር ኃይል፣ከባህር ኃይል ፣ከፖሊስ ፣ከሚሊሺያና ከብሔራዊ ሠራዊት እ,ኤ,አ በግንቦት 28 ቀን 2014 በቀድሞዉ ጦር ኃይሎች የሰብአዊ መብት መከበር ዙርያ ያጠነጠነ ስምንት ነጥብ ያላቸዉ ዓላማ ይዘን በመነሳት (ዓለም አቀፍ የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ማህበር) በሚል መጠሪያ ማህበር ማቋቋማችንን በዚህ አጋጣሚ እንገልፃለን። (በአሜሪካ ሀገር ያለትርፍ አገልግሎትና በሰብአዊ መብት ዙርያ ለመስራት እንድያስችለን በሕጋዊነት በይፋ የተቋቋምንበትን ህጋዊነት የሚያረጋግጥ ማስረጃም ከዚህ ደብዳቤ ጋር አባሪ አድርገን ልከናል።

ክቡርነትዎ እንደሚያዉቁት በማንኛዉም ሀገር የአንድ ሀገር የመከላከያ ሠራዊት ከህዝቡ የወጣና የህዝብ አካል ሲሆን ፤ ዓላማዉ ደግሞ የሃገሩን ዳር ድንበር በወቅቱ ወይንም በጊዜዉ በስልጣን ላይ ባሉት መሪዎች ወይም መንግስት በሚሰጠዉ መመሪያ መሰረት በላቡ ,በደሙና በህይወቱ መስዋዕትነት ከፍሎ ዳር ድንበሩን ፤ የባህር በሩንና የአየር ክልሉን ማስከበር ነዉ። ( ሙሉውን ከዚህ ላይ ያንብቡ, PDF )

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.