ሰበር ዜና …. ተከታታይ መረጃ የጎንደር ከተማ ህዝብ ከተማዋን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል

ሰበር ዜና: በጎንደር የተነሳው ውግያ ተባብሷል! – ከታች አርማጨሆ ህዝብ ወደከተማ እየገባ ነው(EMF) ማራኪ እየተባለ በሚጠራው የጎንደር 18 ቀበሌ የተነሳው ውግያ እየተባባሰ መምጣቱን የ ኢ.ኤም. ኤፍ ዘጋቢ ከስፍራው አስታውቋል:: ዛሬ ማለዳ በጎንደር ህዝብ እና በሀወሃት ታጣቂዎች በተነሳው በዚህ ውግያ በርካታ ሰዎች ከሁለቱም ወገን ማለቃቸውን ዘገባው ጨምሮ ገልጿል::
ለውግያው ምክንያት የሆነው ልዩ የተባለው ጦር ከቀበሌ 18 (ማራኪ) የወልቃይት የዐማራ ማንነት አስተባባሪ ከሚቴዎችን አፍኖ
gondar-under-sieg

ፌደራል ፖሊሶችና መከላከያዎች ባንኮችንና የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ብቻ እየጠበቁ ነው። የህወሃት የንግድ ቤቶችና ሰላም ባስ አውቶቡስ ተቃጥሏል። ወጣቱ አካባቢውን በድንጋይ እየዘጋ ፖሊሶች መተላለፊያ እንዳያገኙ እያደረገ ነው። ጎንደር ከዚህ ቀደም ባልታዬ
ከፍተኛ ተቃውሞ እየተናጠች ነው።
የወልቃይት ህዝብ ኮ/ል ደመቀ ዘውዱን ለማገዝ በጉዞ ላይ መሆኑም ተሰምቷል። ወታደሮች ጥግ ጥግ ይዘው አካባቢውን እየቃኙ ነው። የአማራ ክልል ልዩ ሃይል አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል።
እስካሁን ባለን መረጃ 7 ሰዎች እና 4 የፌደራል ፖሊሶች ተገድለዋል። በመንግስት በኩል የተሰጠ መግለጫ ባለመኖሩ የሟቾችን ቁጥር ለማወቅ አልተቻለም። ኢሳት የኮሚቴው አባላትንና ነዋሪዎችን አነጋግሯል። ሁሉም በአንድ ድምጽ ጎንደር ታይቶ በማይታወቅ ተቃውሞ እየተናጠች ነው ይላሉ።

ሲያቃጥሉት ኖረው በነገር በአበሳ
ማቃጠል ጀመረ ጎንደሬ ተነሳ!

13615121_10205046217193485_8964813869750069248_n
የህወሃት ንብረት የሆነው ሰላም አውቶቡስ ጎንደር ከተማ ውስጥ ሲጋይ

ዛሬ እንደተሰማው ጎንደር በተቃውሞ በአመጽ እና እምቢኝ ባይነት ስትናጥ ውላለች። እነ ራዲዮ ፋና እንደዘገቡት የጎንደር አመጽ የተነሳው ኤርትራ ውስጥ ባሉ ታጣቂዎች አማካይነት ነው። እኛ እንደምናውቀው ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች በመንግስታቸው ቁርሾ ከያዙ ሰንብተዋል እና የሚጠባበቁት አጋጣሚ ነው… የሃገሬ ሰው በየአቅጣጫው፤ እናንተ ፌስ ቡኩን ዝጉ እኛ ምንገዱን እንዘጋዋለን ከዛም ጉሮሯችሁን… እያልን እያልን እንቀጥላለን እያለ እየዛተ መሆኑን ኢህአዴግ ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው እንዲሉ ሆኖ የሰማላት አይመስለኝም።

ህብረተሰቡ በተቻለው አቅም ችግሮችን ለመፍታት ሰላማዊ አማራጮችን ሲጠቀም ቁጭ ብሎ እንደታዘበ ሰው የምንለው ነገር ቢኖር ኢህ አዴግሆይ… መጨረሻሽን ያፍጥነው! የህዝብ ልጆች ሆይ ጉዳቱን ገለባ ያድርግላችሁ ነው!

እንግዲህ እነ አርበኞች ግንቦት ሰባት ከታማች

13627153_560041274183635_5593429528619862716_n

የህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ ጉጀሌ መንግስት ንብረት የሆነው ሰላም ባስ በጎንደር ወጣቶች አማካኝነት ተሳፋሪዎቹን በማስወርደ በ እሳት አጋይተውታል እንዲሁም ከተማዋን ሙሉ በሙሉ ህዝቡ ተቆጣጥሮታል ብራቮ ጎንደር።

 

13680832_293691000980028_2346930258822733776_n 13645103_293690940980034_1252681468872031156_n 13659053_293690970980031_9095508382608936044_n - Copy 13659053_293690970980031_9095508382608936044_n 13669200_560041260850303_826482224627307577_n

13615214_10205046217233486_8163914991732522326_n

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.