የሀገራችንና የሕዝቧ ህልውና መቀጠል ካለበት በዘውገኛ ፖለቲከኞች ላይ ሰይፋችንን እናንሣ! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

Gondr 7

ከዚህ ቀደም የዘውግ ፖለቲካን ተፈጥሯዊ አጥፊነትን ግፈኝነትና ኢፍትሐዊነትን የወያኔንና የሌሎችን የጥፋት ኃይሎችን እራሳቸውን በጠባቡ አጥረው ሞትንለት መሥዋዕትነት ከፈልንለት የሚሉትን ዘር ከሌላው በተለየ መልኩ ተጠቃሚ ለማድረግ ያደረጉትንና እያደረጉት ያሉትን ኢፍትሐዊ የአድልኦና ከራሳቸው ዘር ውጪ ያለውን ደግሞ እንዴት ባለ ስር የሰደደ ጥላቻ እንደሚመለከቱና እንደሚያጠቁ ያሉ ተጨባጭ ኩነቶችን በማሳያነት በማቅረብ፣ የዚህን የዘውግ ፖለቲካ ኋላቀርነትን ለማሳየት ደግሞ ዜጎች በዜግነታቸውና በችሎታቸው ብቻ መመዘን ሲገባቸው ዘርን፣ ቋንቋን፣ ቀለምን፣ ጠባብና ኋላቀር አስተሳሰብን መሠረት ያደረገ አግላይና ኢፍትሐዊ አሠራርን መሠረት ያደረገ አስተሳሰብ በመሆኑ በዚህም ምክንያት በሠለጠነው በምዕራቡ ዓለም የማይሠራበት የተናቀና የተገለለ ከንቱ የደነቆረ አስተሳሰብ መሆኑን መሬት ላይ ካሉ ተጨባጭ ማሳያዎች በማረጋገጥ፣ የአንዲት ሀገርን ዜጎች የሁሉንም ህልውና መብት ጥቅምና ነጻነት ሊያስጠብቁ ከሚችሉ ትክክለኛና ፍትሐዊ ከሠለጠነ ዘመኑን ከዋጀ አማራጭ ጋር ለረጅም ጊዜ ስጽፍበት የቆየሁበት ጉዳይ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ጠባቦቹ ወይም ዘውገኞቹ ዘውገኛ አስተሳሰብ ኋላቀር የደነቆረና ጎጂ አስተሳሰብ ከመሆኑ የተነሣ በሠለጠነው ዓለም እንደማይሠራበት ሲነገራቸው በእስፔን በብሪታኒያና በካናዳ ያሉ የዘውግ ጥያቄዎችንና እንቅስቃሴዎችን በማንሣት ለዚህ ደካማና ኋላቀር አስተሳሰባቸው መደገፊያ ለማግኘት ሲጣጣሩ ይስተዋላሉ፡፡

ሲጀመር የእኛንና የእነዚህን ሀገራት ሁኔታ ምንም የሚያገናኘው ወይም የሚያመሳስለው ጉዳይ የለም፡፡ ቀድሞውንም አንድ ከነበረች ሀገር መለየት ማለትና አስቀድሞ የተለያዩ ሀገራት ከነበሩ በአንድ የታሪክ አጋጣሚ ግን ወደ አንድነት ከመጡ እንደገና ወደቀድሞው ሁኔታቸው መመለስ ፈልገው መለያየትን በጠየቁ ሀገራት መሀል በግልጽ የሚታይ ልዩነትና አለመመሳሰል አለ፡፡

ሀገራችን ሲረዝም የአምስት ሽህ ሲያጥር የሦስት ሽህ ዓመታት ታሪክ ያላት ሀገር ናት፡፡ ይህች ጥንታዊት ኃያል ሀገር የዛሬን አያድርገውና ግዛቷ አፍሪቃን አጠቃሎ ወደ ምሥራቁ ህንድን አልፎ እስከ ቻይና የባሕር ጠረፍ ድረስ በምዕራቡ የአትላንቲክ ውቅያኖስን ደቡባዊ ክፍል “የኢትዮጵያ ውቅያኖስ” አሰኝታ ግዛቷ እዚህ ድረስ ይደርስ የነበረች ታላቅ ሀገር ናት፡፡ ኃይሏ እየተዳከመ ከመምጣቱ ጋር በተያያዘ እየተሰበሰበች መጥታ አሁን ባላት ስፋት ልትወሰን ከመቻሏ በስተቀር አሁን ባላት ስፋት የተለያዩ ሀገራት ኖረው ቆይተው በታሪክ አጋጣሚ ወደ አንድነት በመምጣት አንድነትን ሲፈጥሩ የመሠረቷት ሀገር አይደለችም፡፡

እርግጥ ነው ማዕከላዊው መንግሥት ከመዳከሙ ጋር በተያያዘ አንዳንድ የሀገራቸችን ክፍሎች በአንዳንድ ወቅቶች ተዘንግተው የቆዩበት ሁኔታ ነበረ፡፡ ማዕከላዊው መንግሥት እንደገና ሲጠናከር መሰብሰብ የቻለውን ያህል በመሰብሰብ አሁን ባለችው ስፋት ብቻ ቢወሰንም ቅሉ (የባሕረ ምድርን ወይም የኤርትራን መገንጠል ሳናስብ ማለቴ ነው)፡፡ በመሆኑም ዘውገኞቹ ከሚጠቅሷቸው ሀገራት አውድ ጋር ምንም የሚያመሳስለን ጉዳይ ባለመኖሩ እንደምሳሌ ሊጠቀሱ አይችልም፡፡

በእነኛ ሀገራት የመገንጠል ጥያቄ ያነሡ አካላትም ቀደም ሲል ከተፈጠሩ ታሪካዊ ስሕተቶች የተነሣ የስሕት ገመዱ አንቆ ይዟቸው ሥልጣኔ ከዘውግ አስተሳሰብ ሊያላቃቸው ስላልቻለ ጥያቄውን ሊያነሡ ቢችሉም ተቀባይነት አግኝቶ የተስተናገደ ግን አይደለም፡፡ ካለመስተናገዱም በላይ እንቅስቃሴዎቹ ከላይ ለጠቀስኳቸውን የዘውግ ፖለቲካ (እምነተ አስተዳደር) ችግሮች ተጨማሪ ማሳያዎች ሊሆኑ ቢችሉ እንጅ በራሳቸው ምላሾች አለመሆናቸውን የኞቹ ዘውገኞች ማስተዋል አልቻሉም፡፡

የዚህን የዘውግ አስተሳሰብ ጠቃሚ አለመሆን እንደኔ ሁሉ ሌሎች ብዙዎችም ጽፈዋል፡፡ ይሁን እንጅ የዘውግ ፖለቲካን (እምነተ አሥተዳደርን) የሚያራግቡት ቡድኖች ግን ለሚቀርቡላቸው አግባብነት ያላቸው ጠንካራና አሳማኝ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ተስኗቸውና የማያዋጣ አኪያሔድ መሆኑን ተገንዝበውም እንኳ ፈጽሞ መስሚያ ጆሮ ሊኖራቸው አልቻለም፡፡ በተቀባባ አስመሳይ ስብከታቸው ሕዝብን ለማሳሳት ጥረት በማድረግ በከፊልም በማሳሳት እስከ አሁን መጓዝ የቻሉትን ያህል እየተጓዙ እዚህ ደርሰዋል፡፡ የሚነገራቸውን ሊሰሙ ያልቻሉበት ምክንያቶቹ ደግሞ፡-

  1. እኩልነትን፣ ነጻነትን፣ ፍትሕን፣ ሰብአዊ መብትን ለማስፈን ትግሉ የሚጠብቅባቸውን የሚፈልግባቸውን ብስለት፣ የማሰብ የማገናዘብ ችሎታ ወይም ብቃት፣ ቀናነት፣ ታማኝነት በማጣት፡፡
  2. በጠባብነት፡፡
  3. በልባቸው አርግዘው የያዙትን ድብቅ ዕኩይ የጥፋት ዓላማን ለመጣል ለመተው ባለመፈለግ፡፡
  4. በግል ጥቅም፡፡
  5. በቅጥረኝነት፡፡
  6. በአስመሳይ ሐሰተኛ ስብከታቸው ተታሎ ተወናብዶ የሚከተላቸውን ሕዝብ በመተማመን፡፡

የሚገርመው ይሄንን የዘውግ ፖለቲካ ከሚያራግቡ ልኂቃን አብዛኞቹ የተማሩና ምሁራን የሚባሉ መሆናቸው ነው፡፡ ለእነዚህ ሰዎች መማር ለሰዎች ከሚያበረክተው የሥነ ልቡናና ሥነ አእምሮ ግንባታና ሌሎች አዎንታዊ ትሩፋቶች ወይም ጥቅሞች የትኛውን እንዳበረከተላቸው ስትመረምሩ ብትውሉና ብታድሩ አንዱም ሊገኝባቸው አለመቻሉ እጅግ የሚያሳዝንና የሚያሳስብም ጉዳይ ነው፡፡ ይህ በሆነበት ሁኔታ እነኝህን ሰዎች እንዴት አድርገን እንደምሁር ልንቆጥራቸው እንደምንችል አይገባኝም፡፡ እንደ ምሁር አይደለም እንደ አንድ ተራ ያልተማረ ዜጋ እንኳን ልናያቸው የሚያስችል የሰብአዊ ዕውቀት ተዋስኦ አላገኘንባቸውምና፡፡

ባለፈው መጋቢት 17 እና 18 ቪዥን ኢትዮጵያ የተባለ ድርጅትና ኢሳት ራዲዮና ቴሌቪዥን (ነጋሪተ ወግና ምርዓየ ኩነት) ባዘጋጁት የመወያያ መድረክ ላይ ፕሮፌሰር (ሊቀ ማእምራን) መሳይ መኮነን የተባሉ ሰው አንድ ጽሑፍ አቅርበው ነበር፡፡ ይህ ጽሑፍ እጅግ እንዳስቆጣኝ እንዳበሳጨኝም እንዳስገረመኝም መደበቅ አልችልም፡፡ በአንዳንድ ምክንያቶች አልመቸኝ ብሎ እስከ አሁን ዘገየሁ እንጅ የመልስ ጽሑፍ ሳዘጋጅ ደቂቃም እንኳን አልቆየሁም ነበር፡፡

ሰውየው በዚያ “ጥናታዊ” በተባለ ጽሑፋቸው “ላም ባልዋለበት መስክ ኩበት ሊለቀም ይችላል” የሚል ከንቱ ስብከታቸውን ሲሰብኩ ዋሉ፣ አረም ዘርተው ስንዴን ማፈስ ይቻላል እያሉ ሲቃዡብን ዋሉ፣ ዘይትና ውኃን መቀላቀል እንደማይቻል እያወቁ መቀላቀል እንደሚቻል ሲወሸክቱ ዋሉ፡፡

ጽሑፉ በርካታ እርስ በእርሱ የሚጋጭ ሐሳብ የተሞላ ጽሑፍ ነው፡፡ የራስ ገዝን ሥርዓት “ጠቃሚ ያልሆነ ሕዝብ ሳይመክርበት በግዳጅ ሥራ ላይ የዋለ የተጫነ ነው!” ይሉና መልሰው ደግሞ እራሱኑ ይጠበቅ ይላሉ፡፡ በደንብ ግልጽ ሊያደርጉት ያልፈለጉት ጉዳይ ቢኖር ግን ለምን? የሚለውን ነው፡፡ እርግጥ ከላይ ከጠቀስኳቸው 6 ምክንያቶች ሊወጣ እንደማይችል እርግጠኛ መሆን ይቻላል፡፡

ለአባባሌ ይቅርታ ይደረግልኝና ይህንን የሰውየውን ጽሑፍ ስሰማ የኑኩሊየር ቦምብ (የጅምላ ጨራሽ ፈንጅ) ቁልፍ በ3 ዓመት ሕፃን እጅ የገባ ያህል ነው የተሰማኝ፡፡ ሰውየው በዚህ ጽሑፋቸው ኃይል (Power) የሚጠይቀውን ከፍተኛ ጥንቃቄ፣ ኃላፊነት፣ የሰብእና ከፍታና ልቀት ጉዳይ ጨርሶ ምንም የሚያውቁት ነገር የሌለ ሆነው ነው የታዩኝ፡፡

ሰውየው መንገደኛ ፖለቲካኛ (እምነተ አሥተዳደራዊ) ከመሆናቸው የተነሣ ጎሳን መሠረት ያደረገ ፌደራሊዝም (ራስ ገዝ) ኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ ፈጽሞ እንደማይቻል ገና አልገባቸውም፡፡ እንኳንና ይህ የራስ ገዝ ሥርዓት በትክክል ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ሆኖ ይቅርና ለይስሙላ ወያኔ ተግባራዊ ባደረገው ሥርዓት እንኳ ምን ያህል የእርስ በእርስ ግጭት ቁርቁስና ቀውስ ውስጥ እንደገባል ሰምተው የሚያውቁ አልመሰለኝም፡፡

ኃላፊነትን ፈጽሞ መሸከም የማይችሉ እጅግ ያልበሰሉ ከዚህም የተነሣ ሥራየ ብለው ሐሰተኛ የፈጠራ ታሪኮችን እየነዙ ርካሽ የፖለቲካ (የእምነተ አሥተዳደር) ጥቅማቸውን ለማግበስበስ፣ ሕዝብን ከሕዝብ ለማፋጀት የሚጥሩ በጥላቻ የተመረዙ ተምረው ያልተማሩ ፖለቲከኞች የዘውገኛ ፖለቲካ መድረኩን ተቆጣጥረውት ሞልተውት የሀገሪቱን ህልውና አደጋ ላይ ጥለው እየዛቱም ባሉበት ሁኔታ “የጎሳን ወይም የብሔረሰብን አሰፋፈር መሠረት ያደረገ ራስ ገዛዊ ሥርዓት ነው መፍትሔው!” ብሎ መምከር ምን ማለት ነው? ይሄ ከአንድ የተማረና ሽማግሌ ከሚባል ዜጋ የሚጠበቅ ምክርና ትምህርት ነው እንዴ? እስኪ ከጽሑፋቸው ልጥቀስ፡-

“…ዘውጋዊ እንቅስቃሴ የተፈጸመውን በደል በማስቆም ብቻ እንደማይወሰን ነው፡፡ የዘውግ ጥያቄ ለመብት እኩልነትና ለሰብአዊ መብቶች መከበር ብቻ የሚታገል ቢሆን ኖሮ ሊበራል ዲሞክራሲ መፍትሔ በሆነ ነበር፡፡ …እንቅስቃሴው ስለ አንድ የተበደለ ኅብረተሰብ ነጻ መውጣት ስለሆነ ነጻነቱ እስከሚረጋገጥ ድረስ የቡድን መብት ቅድሚያ ያገኛል!” ሰውየው የዘውጋዊ እንቅስቃሴ ግብ ይሄ ቢሆንም መቀበላቸውን ልብ በሉልኝ፡፡

ቀጠሉና “…በዘውጋዊ ፖለቲካ ዓይን የአንድ ማኅበረሰብ ክብር የሚታደሰው የተዋረደው ማኅበረሰብ የራሱን መንግሥት ሲመሠርትና እራሱን በራሱ ሲያስተዳድር ነው፡፡ አንድ መንግሥት ዲሞክራሲያዊ ቢሆንም የራስ ገዝ መብት ካልተቀበለ ውርደቱን ሊያጠፋው ወይም ሊፍቅለት አይችልም!” በማለት ሰውየው ይህ አስተሳሰብ የዘውገኞቹ እንደሆነ ቢገልጹም “የራስ ገዝን ሥርዓት መቀበል አለብን!” ብለው ከመወትወታቸው የምትረዱት ሐሳቡ የራሳቸውም እንደሆነ ነው፡፡

የኔ ጥያቄ፡- የዘውገኞቹ ግብ ይሄ መሆኑን ካወቅን ለምንድን ነው እሱ ወደዚያ ግባቸው የሚያደርሳቸውን መንገድ ተባባሪያቸው በመሆን ከፊት ከፊታቸው እየቀደምን መንገዱን ልንጠርግላቸው የሚገባን? ኃላፊነት እንደሚሰማው ዜጋ ይሄንን ነው ማድረግ የሚገባን ወይስ እንደ የሰው ልጅ በዚህች መከራ በበዛባት ዓለም ስንኖር እንዲሁም የሀገሩን ህልውና የሚፈታተን ፈተና እንዳለበት ዜጋ የግድ ልንታገለው የሚገባ ፈተና መሆኑን አውቀን በአጭር ታጥቀን ልንታገለውና ልናስወግደው ነው የሚገባው?

በጽሑፍዎ በገለጹት መልኩ የማንፈልገው መሆኑ እየታወቀ ዜጎች ለእሱ እጅ መስጠት ነው የሚገባቸው ወይስ ተመሳሳይ ፈተና ገጥሟቸው በድል እንደተወጡት ሀገራት እኛም በርትተን ታግለን ይሄንን ፈተና ማስወገድ ነው የሚገባው? እርስዎ ከወዲሁ እጅ መስጠትዎና መልካም እንዳልሆነ እየተናገሩ ግን መደገፍዎ ደካማ ተሸናፊ አያሰኝዎትም ወይ? ነው ወይስ መሆኑን የማይፈልጉት እንደሆነ እየተናገሩ መንገዳቸው እንዲጠረግላቸው ማመቻቸትዎ ነጭ ለባሽ ሆነው ኖሮ ነጭ ለባሽነትዎን ለመደበቅ ያደረጉት ጥረት ነው?

ሌላው ጥያቄየ “የዘውገኝነት የመጨረሻው ግብ ነጻ መውጣት ወይም መገንጠል ነው!” ብለዋል፡፡ ይሔም ማለት ተጀምሮ እስኪጨረስ በዘውገኞች ልቡና ውስጥ አንድነት ቦታ የለውም ማለት ነው፡፡ እውነቱ ይሄ ከሆነ እርስዎ ሀገሪቱ እንዳትገነጣጠል በመፍትሔ ሐሳብነት ያቀረቡት ፕሬዘዳንታዊ ሥልጣን እንዴት ሆኖ ነው አስታራቂ ሚና ሊጫወት የሚችለው እባክዎን?

በዚህ ላይ ደግሞ ዘውገኞቹ ለመገንጠላቸው ሰብብ “ባለፉት ዘመናት ተፈጸመብን የሚሉት በደልና መዋረድ ነው” ካሉ የመጨረሻው ግባቸው መገንጠል ብቻ ሳይሆን በደል አድርሶብናል በሚሉት አካል ላይም ግፍ በመፈጸም መበቀል ነው የመጨረሻው ግባቸው ሊሆን የሚችለው፡፡ ለነገሩ ይሄንን ለማድረግ የራሳቸውን ሀገርና መንግሥት መመሥረት አላስፈለጋቸውም አስቀድመው ፈጽመውታልና፡፡ እርስዎ ጥናት እንዳደረገ ሰው ይሄንን እንዴት ሳይገልጹት ቀሩ? የራስ ገዛዊ አሥተዳደር ወደዚህ የሚያመራንና መጨረሻው ይሄ ከሆነ እንዴትስ ሆኖ ነው ታዲያ ለዚህች ሀገር ችግር ራስ ገዝ መፍትሔ ሊሆን የሚችለው ሰውየ ሆይ?

ሰውየ ሆይ! ለመሆኑ “የተዋረደው፣ በደል” ምንትስ የሚሉት ምኑን ነው? ማን? የት? መቸና በማን? ተዋረደ በደል ደረሰበት? ይሄ ፋሺስት ጣሊያን እንቅፋቴ ነው ብሎ የሚያስበውን የአማራን ሕዝብ ለማስጠቃት ለሸፍጠኛ የጥፋት ዓላማው ፈጥሮ ያወራውንና ይሄንን የፈጠራ ወሬ ሥራየ ብሎ በሰፊው ባወራበት ወቅት ዛሬ የጥፋት ኃይሎች ኦሮሚያና ደቡብ በሚሉት የሀገሪቱ ክፍል በአማራ ሕዝብ ላይ እንዲፈጸም ባደረገው መጠነ ሰፊ ጥቃት ቁጥሩ ያልታወቀ በርካታ ሕዝብ እንዲገደል፣ እንዲሰለብና እንዲፈናቀል እንዳደረገና ለወደፊቱም በብሔረሰቦች መካከል ቂም ጥላቻና በቀል ሰፍኖ እንዲኖር እንዳደረገ ሁሉ ዛሬም ከሱ ተቀብለው ለተመሳሳይ የጥፋት ዓላማ ወያኔ ኦነግና ሌሎች የጥፋት ኃይሎች የሚያራግቡትን የአኖሌና የጨለንቆ የፈጠራ በደል ታሪክን ነው “በደል ውርደት ምንትስ” የሚሉት?

የልቅ የፈጠራውን ወሬ ትተው እነኝህ በደል ውርደት ደረሰባቸው የሚሏቸው ወገኖች ከየት ተነሥተው ተስፋፍተው አሁን ይዘውት ያለውን የሀገሪቱን ክፍል ምን ምን ዓይነት ግፍና ጥቃት በነባሩ ማኅበረሰብ ላይ በመፈጸም ወርረው እንደያዙት ለምን አይነግሩንም? ገዳማትንና በውስጡ ያሉ መናንያንን ሳይቀር እያቃጠሉ እየጨፈጨፉ ወረው ያዙ እንጅ አበባ እየነሰነሱ የያዙ ይመስልዎታል እንዴ ሰውየ?

ለመሆኑ ሁሌታዎች ግድ ባሉ ቁጥርና የወቅቱ ዓለማቀፋዊ የአሥተዳደር ዘይቤ ሆኖ ይፈጸም ዘንድ ግድ ሆኖ በገዥዎች የተፈጸመን ግፍና በደል እናውራ ከተባለ የአማራን ያህል ግፍና በደል የተፈጸመበት አንድ ብሔረሰብ ኢትዮጵያ ውስጥ ሊጠቅሱልኝ ይችላሉ? በበርካታ ሽዎች የሚቆጠሩ ሕፃን ሽማግሌ ወንድ ሴት ሳይለይ በጎጆዎች እየታጎረ ከነነፍሱ እንዲቃጠል የተደረገ ሕዝብ ከአማራ ሌላ ማን አለ? እከሌ ብለው ሊጠቅሱልኝ ይችላሉ ሰውየ ሆይ?

ገዥዎች አማራ መሆናቸው የአማራን ሕዝብ ከጥቃት፣ ከመናቅ፣ ከመገፋት፣ ከውርደት ታድጎታል ወይ? ሀቁ ይሄ በሆነበት ሁኔታ በደልን፣ ጥቃትን፣ መገፋትን እንዴት በብሔረሰብ ልንፈርጅና ሒሳብ ማወራረድን ልንጠይቅ እንችላለን? ከማንስ ነው የሚጠየቀው? የምጣዱ እያለ የእንቅቡ መንጣጣት አይሆንም ወይ? እንዲያው ግን ትንሽም እንኳ ሐፍረት ኅሊናና ማገናዘብ የሚባል ነገር አልፈጠረባቹህም? ሀገሪቱን የማታውቋት ከሆነ በማታውቁት ጉዳይ ላይ ከመፈትፈት ምናለ አርፋቹህ ቁጭ ብትሉ?

ዘውገኞች አንድ ያልተረዱት ነገር ምን አለ መሰላቹህ ዜጎች በአሐዳዊ ዲሞክራሲያዊ (መስፍነ ሕዝባዊ) የአሥተዳደር ሥርዓትም በዲሞክራሲያዊ (በመስፍነ ሕዝባዊ) ምርጫ ራሳቸውን በራሳቸው ማሥተዳደርን፣ በራስ ቋንቋ መማር መተዳደርን ሌሎች ፖለቲካዊ (እምነተ አሥተዳደራዊ) እና ማኅበራዊ ጥቅሞቻቸውን ሊያስጠብቁ እንደሚችሉ የሚያውቁ አልመሰለኝም ወይም ለጥፋት ዓላማቸው ስለማይመቻቸው አውቀው ገሸሽ አድርገውታል፡፡

እዚህ ላይ የጎሳ ወይም ቋንቋንና የብሔረሰብ አሰፋፈርን መሠረት ያደረገ ፌደራሊዝም (የራስ ገዝ) ሥርዓት ለኢትዮጵያ መፍትሔ ነው ለሚሉ ሰዎች አሁንም አበክሬ ላስገነዝበው የምሻው ጉዳይ ቢኖር ይሄንን የሚሉ ሰዎች በተሳሳተ ግንዛቤያቸው የራሳቸው ጎሳ ወይም ብሔረሰብ ተጠቃሚ የሚሆን መስሏቸው አስተሳሰቡን ያራግቡታል እንጅ ይህ ሥርዓት በትክክል ለሁሉም ብሔረሰቦችና ጎሳዎች ተፈጻሚ እንዲሆን፣ ለአስተዳደር ሥርዓቱ መፈጸም ታማኝ ሆነውና ኢትዮጵያም ውስጥ ሊተገበርና መፍትሔም ሊሆን የሚችል መሆኑን አውቀውት ተረድተውትና አምነውበትም እንዳልሆነ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

3 ዋና ዋና ማሳያዎችን እንጥቀስ፡-

  1. በሀገራችን ከሰማንያ በላይ ብሔረሰቦችና ጎሳዎች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ እንደወያኔ የይስሙላ ፌደራሊዝም ሳይሆን ትክክለኛ ፌዴራሊዝምን ተግባራዊ እናድርግ ቢባል ከሰማንያ በላይ የራስ ገዝ የመንግሥታት አሥተዳደሮች እንዲኖሩ ማድረግ እንደምንገደድና ከብዙ የተወሳሰቡ ችግሮች አኳያ ይሄንን ማድረግ ፈጽሞ እንደማይቻል አልተስተዋለም፡፡ ወያኔም ስለቸገረው ነው የራስ ገዝ ሥርዓትን በተጻረረ መልክ ከሃምሳ በላይ የተለያዩ ብሔረሰቦችን በአንድ ጨፍልቆ ደቡብ ሲል ሰይሞ የተወሳሰበውን ችግር ለመገላገል የሞከረው፡፡ ከደቡብ ውጭ ያሉት የሌሎች የራስ ገዝ አወቃቀርም በርካታ ጉድለቶች ተቃርኖዎችና ችግሮች ያሉበት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ለምሳሌ የራስ ገዝ ሥርዓት በትክክል ተግባራዊ ይሁን ቢባል ትግራይ ራሱ ከአምስት መከፈል ነበረበትና፡፡
  2. በርካታ ተመሳሳይ ብሔረሰብ ወይም ጎሳ ያላቸው ብሔረሰቦች ወይም ጎሳዎች በተራራቀና የአሠፋፈር ተያያዥነት በሌለው በመሀል በሌላ ብሔረሰብ ወይም ጎሳ በተከፈለ በተነጠለ ወይም በተሰባጠረ አሰፋፈር ላይ ያሉ በመሆናቸውና በዚህም የተነሣ ተመሳሳይ ብሔረሰቦች የአሰፋፈር አንድነት የሌላቸው በመሆኑና የራስ ገዝ ክልልን ከፋፍሎ መስጠት እንዳይቻል ስላደረገ ቋንቋና የብሔረሰብ አሠፋፈርን መሠረት ያደረገ የራስ ገዝ ሥርዓትን በኢትዮጵያ ላይ አሰፍናለሁ ለችግራችንም መፍትሔ ይሆናል የሚለውን አስተሳሰብ የማይቻል እንዲሆን አድርጎታል፡፡
  3. ከኢትዮጵያ ሕዝብ እያንዳንዱ ዜጋ “እኔ ምንም ምን ቅልቅል ደም የሌለብኝ እከሌ የሚባል ብሔረሰብ ተወላጅ ነኝ!” ብሎ አፉን ሞልቶ መናገር የሚችልና ያልተቀላቀለ ደም የሌለው ዜጋ የሌለ በመሆኑና የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲህ በሆነበት ሁኔታ በተጨባጭ ሀቁ ላይ ያልተመሠረተን የብሔረሰብ ልዩነትን መሠረት ያደረገ የራስ ገዝ ሥርዓትን ሥራ ላይ ማዋል ፍጹም ስሕተትና የማይጠቅም የደነቆረ አጥፊ በመሆኑ፡፡ ከአመክንዮ አንጻርም ትክክል ባለመሆኑ፡፡

በመሆኑም በዛሬ ዘመን በተፈጠረው ዓለማቀፋዊ ፖለቲካዊ (እምነተ አሥታዳደራዊ) ኢኮኖሚያዊና (ምጣኔ ሀብታዊ) ማኅበራዊ ነባራዊ ሁኔታ ውሕደት በቀጠና ደረጃ (የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን) በሚታሰብበትና ህልውናን ለማስቀጠል ይሄንን ማድረግ ግድ ባለበት ዘመን ጭራሽም ይህች ሀገር ተገነጣጥላ የሚገነጠሉት ክፍሎች እንደሀገር መቆም የሚችሉበትን አቅምና ሌሎች ተጓዳኝ ሁኔታዎች በምንም በልኩ ቢሆን አግኝተው እንደ ሀገር ለመቆም በማይችሉበት ሁኔታ መገነጣጠልን መመኘት ማለምና ለዚህም መጣር ይሄ ሌላ ምንም ሳይሆን ለባራዊውና ለመጻኤው ፖለቲካዊና ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችን እርጥብ መሀይም መሆን ነው፡፡

ዘውገኞቻችን ግን እነኝህን እውነታዎች አያውቁም እንዳንል ደጋግመን ተናገርን፡፡ ከሰሙ ካወቁ ዘንዳ መለወጥ ይኖርባቸው ነበር፡፡ እነሱ ግን ጭራሽ እንዲያውም እየባሰባቸው ሔደ እንጅ በፍጹም ሊሻላቸው አልቻለም፡፡ እስከ ዱክትርና (ሊቀ ጥብና) የተማሩት ትምህርትና የምንሰጣቸው ምክር አላነቃ አልመልስ ሲላቸው ብንመለከት ጊዜ፤ ተምረው ተመክረው ባይመለሱ ተሳቀው ይመለሱ ይሆናል ብለን ዘለፋና ተግሳጽ ብናዘንብባቸውም እነሱ ግን “ወይ ፍንክች የአባ ቢላዋ ልጅ” ቅምም የማይላቸው ሆነው ስለተገኙ የቀረን አማራጭ በዚህ የጥፋት ዓላማቸው ገፍተው በመሔድ ሳያጠፉን በፊት በመቅደም እነሱን በያሉበት ለቅሞ ማጥፋት ነውና ያለን አማራጭ እስኪያጠፉን ድረስ ቁጭ ብለን እጅና እግራችንን አጣምረን እየተቁለጨለጭን መጠበቅ አይኖርብንምና ሳያጠፉን በፊት በመቅደም በወያኔና በሁሉም ጠባብ ዘውገኛ የጥፋት ኃይሎች ላይ ሠይፋችንን ፈጥነን እናንሣ!!! እላለሁ፡፡

ከዚህ በኋላ ወያኔንና የወያኔ ቢጤ የጥፋት ኃይልን በሀገራችን በፍጹም በፍጹም ማየት አይኖርብንም፡፡ ሊገለጽ ከሚችለው በላይ በድህነት የማቀቀ ሕዝብ ነው ያለን፡፡ በዚህ ድህነቱ ላይ ሌላ የማይወጣው የቀውስ ማጥ ውስጥ ገብቶ ይባስ እንዲማቅቅ ፈጽሞ መፍቀድ የለብንምና ጠላቶቻችን ያሰማሩብንን የእልቂት የድህነት የችጋር ጠበቃና ምሽግ የሆኑትን ጠባብ ዘውገኞችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አጥፍተን ሙሉ ፊታችንን የወደቀች ሀገራችንን በማንሣቱ ላይ በመመለስ ችጋራችንን ቀብረን የእፎይታ አየር መተንፈስ ይኖርብናል፡፡ ለዚህ የሞት ሽረት ትግል የተቀደሰ ዓላማ ስኬት በፍጹም በፍጹም አንድም ዜጋ ቢሆን ታዛቢ ወይም ዳር ቆሞ ተመልካች ሊሆን አይችልምና ሁሉም በያለበት ሠይፉን በጥፋት ኃይሎች ላይ ፈጥኖ በማንሣት የራሱንና የሀገሩን ህልውና ያረጋግጥ!!!

በዘውገኝነት የተመረዙት ተፈውሰው ወደ ትክክለኛው የአንድነት አስተሳሰብ ከመጡ እሰየው የሚያሰኝ ነው፡፡ ዘውገኞች የተመረዘውን አስተሳሰብ እንደያዙ ወደ አንድነት ኃይል ለመቀላቀል የሚደረግ ጥረት ካለ ግን ይሄ አደገኛ ስሕተት ነውና የአንድነት ኃይሎች ከዚህ ስሕተት መቆጠብ እንደሚኖርባቸው አጥብቄ ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com

 

 

 

 

 

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.