በጡረታ የተገለሉ የህወሃት የጦር መኮንኖች በአዲስ አበባ ሚስጢራዊ ስብሰባ እያደረጉ ነው

TPLF-generals-1አንድ ሺ ያክል ቁጥር ያላቸው በጡረታ የተገለሉ የህወሃት አባላት የሆኑ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በአዲስ አበባ ከትናንት ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሚስጢራዊ ስብሰባ በማድረግ ላይ መሆናቸው ታውቋል። ጥሪው የተላለፈው ለትግራይ ተወላጅ የጦር መኮንኖች ብቻ መሆኑ በሰራዊቱ ውስጥ ያለው አለመተማመን እየሰፋ መምጣቱን ያሳያል በማለት የመረጃው ምንጮች አስተያየታቸውን ገልጸዋል።

የስብሰባው አላማ ግልጽ ባይሆንም በጎንደር በመካሄድ ላይ ካለው ህዝባዊ አመጽ፣ በመላ አገሪቱ ከሚታዬው አለመረጋጋት እንዲሁም ከኤርትራ ጋር በተያያዘ ሊፈጠር ስለሚችለው ጦርነት ለመነጋገር ሳይሆን እንደማይቀር ምንጮች ይናገራሉ።

አንዳንድ በጡረታ የተገለሉ መኮንኖች ወደ ሰራዊቱ እንዲመለሱ ጥሪ ሊቀርብላቸው እንደሚችልም ይጠበቃል።

ዜና – በነፃነት በቃሉ