የዐማራ ተጋድሎ የዛሬ (ሀምሌ 12 ቀን 2008 ዓ.ም.) ውሎ

13731995_10155000351975744_1963673570378500360_o

1. በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ላይ ክስ ተመስርቷል፤ ሐምሌ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. ሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይቀርባል፡፡ የቀረበው ክስ ‹‹ሰው በመግደል የተጠረጠሩ›› የሚል ሲሆን ከሐምሌ 5 ቀን በፊት ባለ ጉዳይ ይሁን ወይም ሐምሌ 5 ቀን ራሱን ለመከላከል ባደረገው ጥረት የታወቀ ነገር የለም፡፡ ሐምሌ 22 ቀን ከሳሽ ማን እንደሆነም ይለያል ተብሏል፡፡

2. ኮሎኔል ደመቀን በየቀኑ የሚጠይቀው የዐማራ ሕዝብ ብዛት እስከ 1000 (አንድ ሺህ) ይደርሳል፤ በወያኔ አዋጅ አሸባሪን የጠየቀ አይደለም በቅርብ ርቀት አብሮ ሻይ የጠጣ አሸባሪ ነው፤ ምን እንደሚሉ አይታወቅም፡፡ በነገራችን ላይ ኮሎኔል ደመቀን ከጎጃም፣ ከሸዋም፣ ከወሎም እየመጡ የሚጠይቁት (ጀግናውን የሚያዩት) ሰዎች ብዛት አላቸው፡፡
3. ዐማሮችን በመወከል 22 ሽማግሌዎች ድርድራቸውን ቀጥለዋል፡፡ እስካሁን አሸናፊ ናቸው፡፡ ሐምሌ 5 ቀን ራሱን ለማዳን ባደረገው ተኩስ በሞቱት የወያኔ ፖሊሶች ኮሎኔል እንደማይጠየቅ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ኮሎኔል ደመቀ በምንም መልኩ ወደ ፌደራል (የትግራይ መንግሥት) ተላልፎ አይሰጥም፡፡ የታሰሩ የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴዎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጥረት ላይ ናቸው፡፡
4. የትገሬ ቤቶችንና ዜጎችን ለመጠበቅ ጎንደር ገብተው የነበሩ የመከላከያ ሠራዊትና የፌደራል ፖሊስ አባላት ከከተማው እንዲወጡ ተደርጓል፤ በቅርብ እርቀት ላይ ሰፍረዋል፡፡ ጸጥታውን የዐማራ ልዩ ኃይልና ሲቪል ፖሊስ ተረክቧል፡፡ የጎንደር ዐማሮች እናንተ ጠብቃችሁ አታድኗቸውም፤ እኛ ጋር ካልተጣሉ ችግር የለብንም የሚል መልስ በተመረጡ ሽማግሌዎች ተላልፏል፡፡
5. ነገ በጎንደር የአጼ ፋሲል ስታዲዮም የፋሲል ከነማና ኢትዮጵያ መድን ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፤ የከተማው ሕዝብ እኛ ከተጫዋቾች ሳይሆን ችግራችን ከወያኔ ቅጣ ያጣ አገዛዝ ጋር ነው በማለታቸው ጨዋታው በተያዘለት መርሀ ግብር መሠረት ይሔዳል፡፡ የፋሲል ከነማ ነገ ካሸነፈ የኢትዮጵያን ፕሪሜር ሊግ ይቀላቀላል፡፡
6. ዐማሮችን የሚያወግዙ ሰልፎች በየከተሞቹ እንዲደረጉ ወያኔ ያመጣው ሐሳብ ለሁለት ተከፍሏል፡፡ እንዲያወግዙ ታስበው የተዘጋጁት ሰልፎች በዐማራና በአዲስ አበባ ወደ ተቃውሞ ይዞራሉ የሚል ስጋት በመምጣቱ ሰልፉ መቅረት አለበት ወደሚል ተደርሷል፡፡ እብሪተኛው ሕወሓት ግን ከሰልፈኞች እኩል ብዛት ያለው የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ ጋር መውጣት አለባቸው የሚል ግትር አቋም ይዟል፡፡ ወያኔ በዚህ አቋሙ ገፍቶ ከቀጠለ የሚፈጠረውን መገመት አይከብድም፡፡
7. የዐማራ ብሔር በሆኑ የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ ከፍተኛ ክትትል መኖሩም ታውቋል፡፡ የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ አባል የሆኑ ዐማሮች በምንም መልኩ ወገኖቻቸው ላይ አይተኩሱም፡፡ ወያኔም ይህን ስለሚያውቅ አቋሙን እያለሰለሰ እንደሆነ ተገምቷል፡፡
ሌሎች መረጃዎች ሲኖሩ በየሰአቱ እናደርሳለን፡፡
የዐማራ ሕዝብ ትግል ያሸንፋል!!

Gondar Ethiopia

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.