ከተበተነ ገና ሦስተኛ ሳምንቱን ከያዘው ፓርላማ ሹምሽር ይጠበቃል

woyane parlam 34የወያኔ ፓርላማ ሕወሓት የጠላቸውን ሚኒስቴሮቹን ያባርራል … ሕወሓት የቀባቸውን በምትክ ይሾማል ዳኞችን ያባርራል በምትክ ይሾማል ለዚህ ነው የተጠራው፤….ሽፋን ይሆን ዘንድ ግን የሃገር ኢኮኖሚ ዋልታ የሆኑ አዋጆችን የኣጀንዳው ግንባር ኣድርጓል፤….ሕወሓት ሊበላቸው ኣሊያም ከኣጠገቡ ኣርቆ ሊጥላቸው ያሰባቸውን ሰዎች እናያለን።እጅና እግር የሌለው ፓርላማ ኣስቸኳይ ስብሰባ ያስጠሩ ተባራሪ ሚኒስትሮቻቸው………

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የወልቃይት ሕዝብ ጥያቄ የማንነት ጥያቄ ነው ብለህ ተናግረሃል ተብሎ ቁም ስቅሉን በግምገማ ያየው ቴዎድሮስ ኣድሃኖም ደሙን ኣፍልተው ኮሪያዊ ዶክተር ያሰየሙ ሕወሓቶች ኣሁንም ይብስ የዶክተሩን ፊት ቢምቢ የበላው ጭራቅ ኣስመስለውታል። ቆይ ግን ወልቃይት የኣማራ ክልል እንዳይሆን ለምን ተፈለገ ??? የኣማራ ክልል ኣካል ከምትሆኑ ራስ ገዝ እናድርጋቹ ማለት ለምን ኣስፈለገ ???

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች በተጓደሉ ዳኞች ምትክ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርቡ ዕጩ ዳኞች እንደሚሾሙ ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡በሌላ በኩል ደግሞ  ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አስቸኳይ ስብሰባው በተጠራበት ዕለት በምክር ቤቱ ተገኝተው፣ በተወሰኑ ሚኒስትሮች ላይ ያደረጉትን ሹምሽር እንዲፀድቅላቸው ያስደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህንን ዓይነቱ አስቸኳይ ስብሰባ ፓርላማው በቅርብ ጊዜ የጠራው መለስ ዜናዊ ሕልፈት ወቅት መሆኑ ይታወሳል፡፡\

Minilik Salsawi

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.