የEFE ጉባኤ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያውያን ፎረም በአውሮፓ፣ የመጀመሪያውን ዓለማቀፍ ኮንፈረንስ በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን ባህልና ስፖርትፊስቲቫል በሚካሄድበት አገር ኔዘርላንድስዴንሀግ ያዘጋጀ መሆኑን በደስታ ይገልጻል።

የኢትዮጵያውያን ፎረም በአውርፓ፣ በኢትዮጵያ  ታሪክ፣ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ጉዳዮች፣ እንዲሁም በጊዜው የአለማችን ገዥአስተሳሰቦች ላይ ጥልቅ ውይይቶች የሚካሂዱባቸውን መድረኮች የሚያዘጋጅ የኢትዮጵያውያን ስብስብ ነው። ስብስቡከማንኛውም የፖለቲካ፣ የዘር፣ የሀይማኖት ድርጅቶችና ርዕዮተዓለም ጋር ያልተቆራኘ ነጻ ቡድን  ሲሆን፣ ዓላማውምኢትዮጵያውያን በአገራቸው ታሪካዊና ወቅታዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ተግዳሮቶች ላይ የጋራ ግንዛቤ እንዲያዳብሩ ማገዝነው።

ለዚህ ተልዕኮው መሳካትም ዘንድሮ  ፌዴራሊዝምና የብሄር ጥያቄ  በኢትዮጵያ፣  በሚል አቢይ ርዕስ ላይ ሶስት ታውቂ ባለሙያዎች ጥናታዊ ስራዎቻቸውን እንዲያቀርቡ ጋብዟል። የኮንፈረንሱን ዝርዝር መረጃ የያዘውን ፖስተርከዚህ ደብዳቤ ጋር አባሪ አድርገን የላክን መሆኑን እየገለጽን፣ የዕርስዎ ሜዲያም የዝግጅታችንን መርሀ ግብርእንዲያስተዋውቅልን እና ጥሪያችንንም ለኢትዮጵያውያን እንዲያስተላልፍልን በትህትና እንጠይቃለን፥

ከማክበር ሰላምታ ጋር

ኮሚቴው

poster-revised-1

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.