የህወሃት ርካሽ ፕሮፓጋንዳ በጎንደር ህዝብ ላይ (ግርማ ካሳ)

Gonderየወያኔው ፋና አንድ ዜና አውጥቱዋል። አስቀኝ ግን የሚጠበቅ ዜና። ተመሳሳይ የሆነ ዜና በአማራው ክልል ራዱዬና ቴሎቭዥን ስለመቅረቡ የታወቀ ነገር የለም።

ይሆን ዘገባ ተራና ፀረ ህዝብ ዘገባ እንደሆነ በመቁጠር እያደረግን ያለውን የበለጠ ማጠናከር ነው ያለብን። መዘናጋትም ሆና መፍራት ከዚህ በሁዋላ አያዋጥም። የነብርን ጭራ ከያዙ አይለቀቅም እንደሚባለው።

አንደኛ ደረጃ የወያኔው ፋና ራዲዬ የብአዴን አቶ ንጉሱ ተናገሩት ብሎ ያቀረበው ያላሉትን ወይንም ያሉትን ለህዋሃት ፕሮፓጋንዳ እንዲመች አድርጎ አጣሞ ዘግቦት ሊሆን ይችላል።

ሁለተኛ የብኣዴኑ ሰወዬ ያን ብለው ከሆነ ደግሞ ፣ ለጎንደሩ ቀውስ ህዋሃቶች ብእዶን ከበስተጀርባ አለበት ስለሚሉ እኛ የለንበትም ለማለት ብለውም ይሆናል።ያው እነርሱ ወስጥም የሕዋሃት አሽከሮች አሉ አይደለም። የትግል ፍትጊያ ስላለ ለስትራቴጁ ተብሎ የሚባል ነገር ሊኖር ይችላላ።

ሶስተኛ ሰልፍ ለማድረግ ፍቃድ ይሰጣል የሚል ነገር ህገ ማንግስቱ ላይ የለም። ዜጎች ሰልፍ የማድረግ ህገ መንግስታዊ መብት አላቸው።በትግራይና ሌሎች ቦታዋች ህወሃት ለርካሽ ፕሮፓግንዳ ብሎ ሺህ ጊዜ ሰልፍ እያደረገ የጎንደር ህዝብ በአገሩ ድምፁን ለማሰማት ፍቃድ የሚጠይቅበት ምንም ምክንያት ሊኖር አይችልም።

አራተኛና ዋናው ነገር ህዝቡ ቄርጡዋል። ከዚህ በሁዋላ ምን ማድረግ እንዳለበት ያውቃል። ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ነው። አስደማሚና ድንቅ ትይንተ ህዝብ ይኖራል ተብሎ ነው የሚጠበቀው። በአገሪቱ ሁሉ የሚያስተጋባ ፣ ከጎንደር የፍትህ የሰላም የመብት የእኩልነት የዲሞክራሲና የኢትዬጵያዊነት ደዉል ይደወላል። ታረክ ይሰራል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.