እንዴት ነው ታዲያ ነቃ ነቃ አዲስ አበባ! ነቃ ነቃ መላው ኢትዮጵያ! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

ምዕራፍ አንድ !

113ምንም እንኳ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ማሳወቅ እንጅ ፈቃድ መጠየቅ ሕጋዊነት ያለው አሠራር ባይሆንም ይህ ታላቅ ሰልፍ የተደረገው በወያኔ ፈቃድ ሆኖ ቢሆን ኖሮ ምንም ሊሰማኝ የሚችል ነገር ባልነበረ ነበር፡፡
ነገር ግን የጎንደር ሕዝብ ንቅል ብሎ በመውጣት ይሄንን ታላቅ ታሪካዊ ሰልፍ ያደረገው ወያኔ ይሄንን ሰልፍ ሕገ ወጥና ፈቃድ ያልተሰጠው ብሎ ባወጀበት ሁኔታና የተቃውሞ ሰልፉን ለማስቀረት ለማክሸፍ ለማሰናከል ከባባድ ማስፈራሪያዎችን ጨምሮ ሌሎች የአፈና እርምጃዎቹንና ስልቶቹን አሟጦ ተጠቅሞ እያለ ሕዝቡ ለዚህ የወያኔ አንባገነናዊ የአፈና እርምጃና ማስፈራሪያ ቅንጣት ታክል ሳይበገር ነቅሎ በመውጣት ለአንባገነኑ የወያኔ አገዛዝ ግፍና በደሎቹ ያለውን መራር ተቃውሞ የገለጸበት፣ ብሶቱን ያሰማበት፣ በደሉን ያስታወቀበት፣  ብሔራዊ ስሜቱን ያስተጋባበት፣ ባለአደራነቱን ያረጋገጠበት፣ የበቃኝ መልዕክቱን ያስተላለፈበት ታላቅ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ በመሆኑ ኩራት የሚሞላ ጀብድ ነው፡፡
1388ነገር ግን ይህ ልናደርገው ከሚገቡን እርምጃዎች አንዱ እንጅ በራሱ የመጨረሻ ግብ ባለመሆኑ በዚህ ስኬት ሳንዘናጋና ወያኔ በዚህ ታላቅ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ እንዲፈጽም፣ እንዲያሟላ፣ እንዲያስተካክል ለተላለፉለት ጠንካራ ሕዝባዊ መልዕክቶችና ጥያቄዎች ጆሮ ሰጥቶ ይስተካከላል ያሟላል ይፈጽማል ተብሎ ስለማይታሰብ ስለማይጠበቅና ከነ ችግሮቹ በደሎቹና ግፎቹ ከመክሰም ከመጥፋት በስተቀር የመስተካከል የማሟላት የመፈጸም ዕድል ፈጽሞ ስለሌለው ይህን አንባገነናዊ አረመኔ አገዛዝ በተቻለን ፍጥነት ከስሩ ነቅለን ለመጣል የሚያስችሉንን ቆራጥ እርምጃዎች በሙሉ አከታትለን ማድረግ የግድ ይጠበቅብናል፡፡
ይህን የተቀደሰ ብሔራዊ ተልዕኮ ለስኬት ከማብቃት አኳያ እስከ አሁን ይህ እየተደረገ ያለውን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ያልተቀላቀልከው የተቀረኸው የኢትዮጵያ ሕዝብም በዝምታ እንድትመለከት ሊያደርግህ የሚገባ አንዳችም ምክንያት የለምና በዚህ አንገብጋቢ የሞት ሽረት የትግል ወቅት ዝምታ የሀገር ክህደት ነውና ጊዜ የለም በቶሎ ተቀላቀል!!!
በተለይም አዲስ አበባ! እንዴት ነው አዲስ አበባ??? ነቃ በይ እንጅ!!! ይሄው አዲሱን ምእራፍ ጎንደር ባርካ ጀምራልሻለች አንች ተቀብለሽ በአስደናቂ አጨራረስ ቤተመንግሥቱን ከተባይ አጽድተሽ ግሩም ስኬት እንደምታስመዘግቢ ተስፋ አደርጋለሁ!
እንዴት ነው ታዲያ ነቃ ነቃ አዲስ አበባ! ነቃ ነቃ መላው ኢትዮጵያ!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

13883700_1172727749415944_1800914399_n

13900394_1172695232752529_754692305_n

13686494_10157500545625354_4456691172760173583_n 13754512_634113086744462_3344297064830953903_n 138826 4613876395_10157500545630354_3984602988133288247_nmassive-protest-currently-underway-in-gondar-146994254984gkn

138826
massive-protest-currently-underway-in-gondar-146994254984gkn

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.