ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ፍርድ ቤት ዛሬም አልቀረቡም

ዛሬ ሀምሌ 25 ቀን 2008 ዓም ፍርድ እንደሚቀርቡ የተገለጸው ኮሎኔል ደመቀ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ውለዋል።

የወልቃይት ዐማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴ አባላት ለምን መቅረብ እንዳልቻለ ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን “አሁን ባለው ሁኔታ ፍርድ ቤት ቢቀርብ ሕዝቡ ችግር ሊፈጥር ይችላል” የሚል መልስ ተሰጥቷቸዋል።

ኮሎኔሉን የከሰሰ አካል አለመኖሩም ፍርድ ቤት ላለመቅረባቸው እንደ ሁለተኛ ምክንያት ቀርቧል። አስተባባሪ ኮሜቴዎቹም ከሳሽ ከሌለ ለምን ይታሰራል? የሚል ጥያቄ አቅርባው መልስ አልተሰጣቸውም። በጥቂት ቀናት ውስጥ ሁሉም የኮማቴ አባላት ካልተፈቱ በሁሉም የዐማራ አካባቢዎች ተጨማሪ የተጋድሎ ሰልፎች ይካሄዳሉ።

138q

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.