ሕወሃት የወገኖቻችንን ደም እያፈሰሰ ነው – ግርማ ካሳ

ኢትዮጵያዉያን በተለያዩ አቅጣጫዎች ተቃዉሟቸውን እያሰሙ ነው። ትላልቅ ክልሎች የሚባሉት የአማራው ክልል እና የኦሮሚያ ክልል ነው። በሁለቱ ክልሎች የሚኖረው ሕዝብ የአገሪቷ ቢያንስ 65% የሚሆን ነው። ሕዝቡ በነዚህ ክልሎች ያለው ተቃዉሞ እያሰማ መው።

በትላንትናው እለት ከስምንት መቶ ሺህ በላይ ሕዝብ በጎንደር ከተማ እንዲሁም በሌሎች ሶስት ሌሎች ከተሞችም በሺሆች የሚቆጠሩ የተቃዉሞ ድምጻቸዉን ማሰማታቸው ይታወሳል። በሰልፉ የጎንደር ሕዝብ በኦሮሚያ እየተፈጸመ ያለዉን ግፍ አወግዘዋል። የኦሮሞ ወንድሞቻችን ደም የኛም ደም ነው ፣ በነርሱ ላይ የሚፈጸመው ግድያ ይቆም እያሉ ሲጮሁ ነበር።

በጎንደር ሕዝቡ ተቃዉሞዉን እያሰማ ፣ በኦሮሚያ ግን ሕወሃት የወገኖቻችንን ደም ማፍሰሱን አላቆመም።

በምስራቅ ሀረርጌ ውስጥ በአወዳይ ከተማ በትላንትናው ቀን በአልሞ ተኳሾች (በስናይፐር) በጥይት የተመቱ ሰዎች ቁጥር እስከ አሁን ባለው መረጃ #26 ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ ‪#‎6ቱ‬ ተገለዋል። የትላንቱ‪#‎የአወዳይ_ጭፍጨፋ‬ የተቀነባበረ መሆኑን ለማወቅ ተችሎዋል። እንደ አካባቢው ምንጮች ገለፃ ከሆነ ወታደሮች በአንድ ሰው መደብር ገብተው በውስጥ ያሉትን ሰራተኞች በማናገር ላይ እያሉ የመደብሩ ባለቤት ወደውጪ ወጥቶ እርዱኝ የሚል የእርዳታ ጥሪ ሲያስተላልፍ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች እሱን ለመርዳት እንደተሰበሰቡ ቶክስ እንደተከፈተባቸውና ጥይቱን እንጂ ተኳሹን ግን ማየት እንዳልቻሉ የአይን ምስክሮች ገልፀዋል።

ዛሬ ደግሞ በምስራቅ ሀረርጌ በበዴሳ ፣ዳዳርና ፣በቆቦ ከተሞች ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ በመካሄድ ላይ ሲሆን በቆቦ ከተማ ላይ ዋናው መንገድ ከፊንፊኔ ወደ ሀረርና ድሬዳዋ የሚወስደው ዋናው መንገድ በህዝባዊ የትግል ኃይሎች ሙሉ በሙሉ ተዘግቶዋል።

በበዴሳ በተደረገው ተቃውሞ ህዝቡ እስር ቤትን በመስበር እስረኞችን አስፈትቶዋል።

የአጋዚ አውሬዎች በወሰዱት የሀይል እርምጃ 4 ሰው በጠይት የተመታ ሲሆን አንዱ ወዲያው ሞቶዋል።

ነገሮች እየከፉና ነው የመጡት። በአስቸኳይ ሕወሃት የአጋዚ ጦርን ከኦሮሚያ እንዲያስወጣና ያሉ ችግሮች በፖለቲካ ዉይይት እንዲፈቱ ራሱን እንዲያዘጋጅ እጠይቃለሁ። ከዚህ በኋላ እነርሱ እንደፈለጉ መግዛትና ማዘዝ አይችሉም። ሕዝብ በቃኝ ብሏል። አዲስ የሽግግር መንግስት መኖር አለበት። (እነርሱንም ያካተተ)። አሁን ያለው የክልል አወቃቀር በዘር ላይ ባላተኮረ መልኩ መዋቀር አለበት።

ወጣት ታጁ አህመድ ይባላል። በዲዴሳ የተመታ ወጣት ነው ። ሰልፈኞቹ ደግሞ በበዴሳ ነው።

2q1 2q

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.