ሰልፍ በባህር ዳር ነሐሴ 1 ይደረጋል

Bahir dar

ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ.ም በባሕር ዳር ሰልፍ እንደሚደረግ ተገለጸ። ሰላማዊ ሰልፉን የከተማ አስተዳደሩ ላይፈቅድ እንደሚችል ቢታወቅም፣ ሰልፉ ግን እንደማይቀር ነው አዘጋጆች እየገለጹ ያሉት።

በጎንደር በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ አንዲት ጠጠር ሳይወረወር ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ነው ሰልፍ የተደረገው። የባህር ዳር ከተማም ከዚህ በፊት በተላያዩ አጋጣዊዎች ሰላማዊነቱን ያስመሰከረ ሕዝብ ነው። ከሶስት አመታት በፊት በባህር ዳር የአንድነት ፓርቲ እና መኢአድ በጋራ ጠርተዉት በነበረዉና የክልሉ ም/አስተዳዳሪ የሆነው አለምነህ መኮንን የተወገዘበት ሰልፍ ላይ ከሰማኒያ ሺህ በላይ የባህር ዳር ከተማ ህዝብ ተገኝቶ እንደነበረ ይታወሳል።

አለምነህ መኮንን የአማራዉ ክልል ህዝብ “በእግሩ እየሄደ በባዶ የሚኮራ፣ ልፋጫም የሆነ” ብሎ መሳደቡ ይታወሳል። ህወሃቶች ለሕዝቡ ትልቅ ንቀት ስላላቸውም ይሄ ሰው አሁንም የነርሱ አገልጋይ ሆኖ እንዲቀጥል አደርገዉታል።

አሁንም ነሐሴ 1 ቀን በሚደረገው ሰልፍ ጀግናው የባህር ዳር እና በባህር ዳር ዙሪያ የሚገኘው ህዝብ ድምጹን ያሰማል ተብሎ ይጠበቃል።

ከሶት አመት በፊት የተደረገው ሰልፍ

bahir dar 1

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.