ሰላማዊ ሰልፍ በባህር ዳር – የቴዎድሮስ ልጆች (ዋልያዎቹ) ወደ ባህርዳር

ሰላማዊ ሰልፍ በባህር ዳር። እንደ ጎንደሩ ሰልፍም ሰላማዊ ነው የሚሆነው። ህዝቡ ድምፁን የማሰማት መብቱ ማንም በልግስና የሰጠው ሳይሆን በህገ መንግስቱ የተደነገ መሰረታዊ መብት ነው

“ባህርዳር
ላይ ተወልደህ
የፈራህ እንደሆን!!!

እናትክን ጠይቃት
ሽል ቀይራ እንደሆን!!!…

Bahird dar

በባህር ዳር ሰላማዊ ሰልፍ ታሪክ ሊሰራ ከጫፍ ደርሷል!

በኦሮሚያ ትግሉ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ቁጣው ሊበረታ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ የወልቃይት ጠገዴ ሰሜን ጎንደር ሕዝባዊ የድል ችቦ እየተቀጣጠለ በመላው አማራ ምድር እየተስተጋባ መሄዱን ቀጥሏል፡፡ የወንዱ ሀገር የበላይ ልጆች እግሮች ሁሉ ወደ ባህርዳር ጉዞ ሊያመሩ ቀጠሮ ከወዲሁ ተይዟል፡፡ ጎጃም..ክተት እየተጠራ ነው፡፡ በየወረዳው በጎበዝ አለቃ እየተመራ ጥሪው እየተበተነ ይገኛል፡፡ እሁድ ነሐሴ1/2008 ታላቋ ደሴት ባህርዳር በሕዝባዊ ቁጣ አደባባዩ ይሞላል መልዕክቱ በሁሉም አቅጣጫ እየተላለፈ መሆኑ ከጎጃም ተሰምቷል፡፡

በሳምቱ መጨራሻ ወጣት ልጅ አዋቂው አርሶ አደሩ ባህርዳር ይገባሉ፡፡ ሀገር ወዳዱ አርበኛ የአማራ ሕዝብ ዘንድሮ ምን እንደሰማ እንጃ..ሁሉም በቁጭት ተቆጥቶዋል፡፡ ከሀገሩ ቄዬው ከወንዙ ያፈናቀለው ዘሩን የማከነው ከሁለት አስር አመታት በኃላ ዘግይቶም ቢሆን ጠላቱን የተረዳው ይመስላል፡፡ ከምስራቅ ጎጃም..ደብረኤልያስ-የጁቤ መቻከል አንበር እነማይ ሸበልበረንታ ሞጦ መርጦረማሪያም እናርጅናውጋ ሉማሜ ምስራቁ ወደ ምዕራብ ጎጃም ዋና መዲና ባሕርዳር ተያይዘው ይጎርፋሉ፡፡ ባህርዳር ዙሪያ ደንበጫ ዳንግላ ቡሬ ፈረስቤት ዱርቤቴ ኮሶበር እዛው ይገናኛሉ፡፡

እንደ ጀግናው ወንድሙ የጎንደር ሕዝብ ስለማንነቱ በአደባባይ ይናገራል፡፡ ሽለላው ፉከራው በጎጃም ምድር ደምቆ ይታያል፡፡ የአማራ ሕዝብ በአንድነት ስለኢትዮጵያዊነቱ ይዘመራል፡፡ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ የድንበሩ መዳረሻ በጎጃም እምብርት ባሕርዳር በመቶ ሺህ በሚቆጠር ሕዝባዊ ማዕበል ይሰተጋባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በተመሳሳይ በመላው ኦሮሚያ ታሪክ ሊሰራ የፊታችን ቅዳሜ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በሁሉም አካባቢ ተጠርቷል፡፡


(…ጉድበል የሀገሬ ሰው!

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.