የወልቃይት ጠገዴ ኮሚቴ አባላት ጠ/ሚ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ወልቃይት የትግራይ ነው ማለታቸውን ተቃውሙ

welkeit
ኢሳት (ሃምሌ 27 ፥ 2008)

የወልቃይት ጠገዴ ኮሚቴ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ የወልቃይትን አማራነት አስመልክቶ ባህርዳር ውስጥ የሰጡት ምላሽ ተገቢ አለመሆኑንና፣ በገሃድ ህዝብ ያነሳውን ጥያቄ የከዳ ምላሽ መሆኑን አስታውቀዋል።
በኢትዮጵያዊነት በማያምን አካል የተሰጠ ምላሽ ነው ሲሉ የገለጹት የኮሚቴ አባላቱ፣ ህዝቡ ያነሳውን ጥያቄ ምላሽን እስኪያገኝ ድረስ ሰላማዊ ትግላቸው ቀጣይ መሆኑን ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስረድተዋል።
በወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ያነሱ ነዋሪዎች ቀጥተኛ ምላሽ እንዲሰጡ ቢደረግ ጥያቄው ግልጽ መልስን እንደሚሰጥ የኮሚቴ አባላቱ አክለው ገልጸዋል።
የመንግስት ባለስልጣናት በወልቃይት ጠገዴ አማርኛ ተናጋሪ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ እንጂ አካባቢው የትግራይ አካል ነው ሲሉ ምላሽን እየሰጡ ይገኛል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.