ሙካታር ከድር ሰልፍ ማድረግ አይቻልም ነገር አለ – ግርማ ካሳ

MUKTAR 5

አዲስ አበባና በድረዳዋ እንዲሁም በኦሮሚያ ባሉ ትላልቅ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደረግ የኦሮሞ ሜዲያ ኔትዎርክ ገለጸ። በኦሮሚያ ትላልቅ ከተሞች ከተባሉት ዉስጥ፣ አዲስ አበባን ሳይጨመር፣ ከአንድ እስከ አሥር ያሉትና ከ50 ሺህ በላይ የሚኖርባቸው ትላልቅ ከተሞች የሚከተሉት ናቸው፡

አንደኛ አዳማ፣ ሁለተኛ ጂማ፣ ሶስተኛ ሻሸመኔ፣ አራተኛ ደብረ ዘይት/ቢሾፍቱ፣ አምስተኛ ነቀመቴ፣ ስድስተኛ አሰላ፣ ሰባተኛ ቡራዮ፣ ስምንተኛ አምቦ፣ ዘጠነኛ ሰበታና እና አሥረኛ ወሊሶ ናቸው።

ሌሎች ከ50 ሺህ በታች ህዝብ የሚኖርባቸው እንደ መቱ፣ ጎሬ፣ ጭሮ፣ ጊምቢ፣ ፍቼ፣ ዶዶላ፣ ሮቢ፣ ዝዋይ..የመሳሰሉም ከተሞች አሉ።

ከነዚህ ሁሉ ከተሞች የትኞቹ ጋር ህዝብ በብዛት እንደሚወጣ የሚታወቅ ነገር የለም። የዞኑ አደራጆች “በመላው ኦሮሚያ” ከማለት ዉጭ ከተሞቹ ከአዲስ አበባ እና ድረዳዋ በስተቀር አልተጠቀሱም።

እስከ አሁን የተደረጉ ተቃዉሞዎች በብዛት የነበሩት በምእራብ ሽዋ ዞን፣ በምስራቅ እና ደቡብ ሃረርጌ ዞኖች፣ በምስራቅ፣ ምእራብ እና ቀለም ወለጋ ዞኖች፣ በምእራብ አርሲ ዞን ፣ በባሌ ዞን እና በቦረና ዞን ነው። በመሆኑም ቢያንስ በነዚህ ዞኖች ባሉ ከተማዎች በቀላሉ እጅግ በጣም ብዙ ህዝብ ሊወጣ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።

የኦሮምያው ክልል ፕ/ሬ ሙክታር ከድር በኦሮምያ ክልል እውቅና የሰጠነው ስልፍ የለም በማለት የሕዝብን ጥያቄ በመናቅ የማስፈራሪያ ዘመቻዉን ከፍቷል። ሕዝብ ድምጹን የማሰማት ሙሉ መብት አለው። በሕገ መንግስቱ የተደነገገ ነው። ሕዝብን ከማዳመጥ ይልቅ ከሕዝብ ጋር ለመታገል መመኮር ደግሞ የሽንፈትና የዉድቀት ምልክት ነው።

በኦሮሚያ የተጠራው ሰልፍ የሚከተሉትን ሶስት ጥያቄዎችን ነው ያነገበው፡

1) የታሰሩት የፖለትካ እስረኞች በአስሸኳይ እንዲፈቱ፣
2) በኦሮሚያ ዉስጥ የሚደረገዉ መጠነ ሰፊ ግድያ እንዲቆምና ገዳዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ 3) 3) ኦሮሚያ ራሱን የማስተዳደር መብቱ እንድጠበቅለት እና የህዝቦች መብት እንዲከበር ።

ኦሮሚያ ራሷን የማስተዳደር መብት ይጠበቅላት በሚለው አላማ ላይ ጥያቄዎች ብዙዎች ይኖራቸዋል። በተለይም በኦሮሚያ፣ በተለይም በትላልቅ ከተሞች የሚኖረው እጅግ በጣም ብዙ “ኦሮሞ” ያልሆነው ማህበረሰብን ጥያቄዎች ባላስተናገደ መልኩ አሁን ባለው የኦሮሚያ ሕግ መንግስት ኦሮሚያ ራሱዋን በራሷ ታስተዳደር ማለት ለብዙዎች ምቾት የሚሰጥ አይደለም። አዘጋጆቹ ይሄን ጥያቄ ባያስገቡት ጥሩ ነበር።

ሆኖም ግን በአንደኛና በሁለተኛ ተራ ቁጥር ላይ በቀረቡ አላማዎች ዙሪያ ግን ከኦሮሞ ማህበረሰብ ዉጭ ያለው ህዝብም የሚደገፈው እንደመሆኑ የዚህ ሰልፍ አካል ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

ያሉ ልዩነቶች ይሄ አፋኝና ዘረኛ ስርዓት ከተወገደ በኋላ በዉይይትና መገባባት የማይፈታ ነገር የለም። እኛ ድሮም ተከባብረንና ተዋልደን የኖርን ነን። የከፋፈሉን፣ እርስ በርስ እንዳንተማመን ያደረጉን ህወሃቶች ናቸው፡ በጋር እንዳንቆም አደርገዉን በተናጥል እየገደሉን ያሉት ህወሃቶች ናቸው። ያንን ማስቆም የምንችለው ሁላችንም አንድ ስንሆን ነው። ወደድንም ጠላንም በአንድ ላይ ካልተጓዝን የትም ልንዘልቅ አንችልም።

ቅዳሜ በኦሮሚያ ሰልፍ በሚደረግበትም ጊዜ በእሴተ ከተማና በደብረ ታቦርም ተመሳሳይ ሰልፍ ይደረጋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.