ሰበር ዜንና. . . . የትግራይ ነጻ አዉጪዉ ቡድን የብሔራዊ መረጃ የመጨረሻዋ እድሉን በመሞከር ላይ እንደሚገኝ የዉስጥ ምንጮች ገለጹ

Getachew Assefa  - Satenaw

የትግራዩ ነጻ አዉጪ ቡድን የአፈናዉ ድርጅት! የጌታቸዉ አሰፋ ሐላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባኒያ! ብሔራዊ መረጃ! ለህዝባዊ እንቢተኝነት መፋፋም ምክንያት ይሆናሉ በሚል መላ ምት ብቻ አርበኞች ግንቦት ሰባት በስነ ምግባር ጉድለት ያሰናበታቸዉን እና ህወሃት ፖለቲካዊ ትርፍ አገኝበታለዉ ብሎ በእቅፍ አበባ የተቀበላቸዉ ግለሰቦች ላይ ቀድሞ ከነበረዉ በላይ ዉስጣዊ ክትትል ምርመራ ተጠናክሮ እንዲካሄድ ወስኖአል።

በከተማ ዉስጥና ከከተማ ዉጭ የሚገኙ የመከላከያ ካምፖችን፣ የፖሊስ ጣቢያዎችን፣ የደህንነት መረቦችና መዋቅሮችን፣ የፖለቲካ አራማጅና ፕሮፓጋንዳ ይዘቶችን፣ ቀንደኛ ህወሃታዊ ተቁዋማትና የግለሰብ ድጋፍ አድራጊዎችን ባጠቃላይ የህወሃትን ህልዉና የሚፈታተኑ መረጃዎች በነዚህ ሰዎች አማካኝነት ለአርበኞች ግንቦት 7 ተላልፎአ በሚል ግምት አንድ አነስተኛ አፋኝ ቡድን አቁዋቁሞአል።
በመፈራረስ ላይ የሚገኘዉ የጌታቸዉ አሰፋ የግል ድርጅት ብሄራዊ መረጃ
1. ማስረሻ ቢረዳ
2.ወንዶሰን አሸኔ
3. የሽታ
እና ሌሎች ሁለት ግለሰቦች ላይ ከማነጣጠሩ በተጨማሪ በአሁኑ ወቅት እየተፋፋመ የሚገኘዉን ህዝባዊ እንቢተኝነት በዋነኛነት በመረጃ ደረጃ ይመራሉ የሚል ተጨማሪ የክስ ሰነድ እያዘጋጀ እንደሚገኝ ታዉቆአል።
የጌታቸዉ አሰፋ አፋኝ ቡድን ለማሕበራዊ ድህረ ገጾች እና ለሚዲያ አዉታሮች መረጃ ይሰጣሉ የተባሉ 9 የመረጃ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን፡ በጎንደር የብአዴን ከፍተኛ አመራሮችም የጥቃቱ ሰለባ እንደሚሆኑ የተናገሩት ምንጮች በተለይም ገዱ አንዳርጋቸዉ የአፈናዉ ኢላማ መሆናቸዉ ሲያረጋግጡ የመረጃዉ ጽንፍ ቡድን ገዱ ላይ ምንም አይነት ጥቃት ከማድረስ በፊት ከሐላፊነቱ የሚወርድበት የራሱ ፍቃድ እንዲመጣ ጫና እንዲደረግበት ዉሳኔ ተላልፎአል።

ዜና በ ልዑል አለም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.