በሀብታሙ አያሌው- ህወኃቶች የመጨረሻዋን የእብሪት ጠብታ በግፍ ጽዋው ጨመሩ

ሀብታሙ አያሌው በጠና ታሞ በሆስፒታል
ሀብታሙ አያሌው በጠና ታሞ በሆስፒታል

ሕወኃት ስለአገር አንድነትና ሰላም አማራጭ ኃሳብ ያላቸውን ፖለቲካ ድርጅት መሪዎችና አባላት፣ በነጻ ሃሳብን የመግለጽ መብታቸውን ተጠቅመው ስለአገራቸውና ኢትዮጵያዊያን ያላቸውን ራዕይ የገለጹ ጋዜጠኞች፣ የሰብዐዊ መብት ተሟጋቾች፣ አክቲቪስቶች . . . በፈጠራ በመንጀል፣ በማሰር፣ በማሰቃየት፣. . .በህገመንግስታዊ መብታቸው የእምነት ነጻነት በህዝብ ተወክለው የጠየቁትን የሙስሊሙ ተወካዮችን በማሰቃየት፣ ዜጎችን በአደባባይ በመግደልና በጎጡና መኖሪያው በማፈናቀል . . . ከዕለት ወደ ዕለት በግፍ ጽዋው ላይ እየቸመረ ቆይቷል፡፡

መብቱንና ክብሩን ማንነትና ነጻነቱን . . . የአገሩን አንድነትና ሉዓላዊነት ለጠየቀው የኢትዮጵያ ህዝብ በቂም በቀል፣ በእብሪትና ጉልበት፣ በከፋፍለህ ግዛ መሰሪ አካሄድ በሴራ የተሸፈነ ምላሽ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ የኦሮሞ ህጻናት፣ ወጣቶች፣ አዛውንት እናቶች ጭምር በአደባባይ በጥይት እየደፋ፣ የሃመር ወጣቶችን፣ የኮንሶ ህዝብን፣ የወልቃይት ጠገዴ/አማራን፣ እየገደለ፤… ጽዋውን አፋጥኖ እየሞላ ነው፡፡
ዛሬ ደግሞ በሃብታሙ አያሌው ላይ ያሳለፈው የእብሪት ውሳኔ የመጨረሻውን የበቀል ደረጃ ያመለክታል፡፡
ህወኃት ሆይ የመግቢያህ ቀን እየደረሰ ባለበት የቀብሩን ጉድጓድ በጣም አርቀህ እየቆፈርክ ነው፤ የልብ በል- ምክራችንን አልሰማህምና … በደንብ ቆፍረው ሥራ እያቀለልክ ነውና 
በቸር ያገናኘን፡፡

ሃምሌ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.