ለነገው የባህር ዳር ሰልፍ ዝግጅቱ ተጠናቋል- ‪ግርማ_ካሳ‬

13907113_1239233136109524_1036708007906907527_n

ሀምሌ 24 ቀን እሁድ በጎንደር ከተማ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉ ይታወቃል። ወደ ስምንት መቶ ሺህ የሚሆን ሕዝብ ነበር ከተማዋን ያጥለቀለቀው። ድፍን የከተማ ነዋሪ እና ከጎንደር ዙሪያ የመጡ ነዋሪዎች። ሰልፍ እጅግ በጣማ ስገራሚና ሰላማዊ ነበር። የወያኔ ሜዲያም ሳይቀር በደባባይ የመሰከረለት ሰልፍ ነበር።

በተመሳሳይ ሁኔታ በጋይንትና በደብረ ታቦር እንደ ጎንደር ሕዝብ ድምጻቸዉን ለማሰማት አደባባይ የወጣው ሕዝብ ግን የጠበቀው ጥይት ነበር። ሕዝቡ ሰልፍ የመዉጣት ሕገ መንግስታዊ መብት እንዳለው ቢረጋግጥም ፣ ሕግን እናስከብራለን የሚሉ ሕግ መንግስቱኢን በመናቅ የሕዝቡን መብት ለመገፋት ሞከረዋል። ባዲ እጁን በዱላ በመጣው ሰላምዊ ሕዝብ ላይ ተኩሰው የ79 አመት መምህር፣ ሽማግሌ አባትን ጨመሪ ብዙዎችን ገድለዋል፣ ብዙዎችን አቁስለዋል። በጋይንት በተፈጠረው ግጭት ሕዝቡ ተቆጡ ነፍጥ በማንሳቱም ከተማዋ በሙሉ ከሕወሃት ቁጥጥር ዉጭ ለመሆን በቃታለች። በደቭረ ታቦር እና በጋይንት ህወሃቶች መጥተው ባይተነኩሱን የሕዝቡን ሕገ መንግስታዊ መብት ባይጋፉ ኖሮ፣ እንደ ሐምሌ 24ቱ ሰልፍ ህዝቡ በሰላም ወጥትይ በሰላም ይገባ ነበር።

ነገ በታላቋ ባህር ዳር ሰልፍ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ይደረጋል። ሕወሃት አሁን እጆቹን ከባህር ዳር ህዝብ እንዲያነሳ አስጠነቅቃለሁ።

የባህይር ዳሩን ሰልፍ በተመለከተ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው የሚከትለውን ዘግቧል፡
================
ባሕር ዳር፡- እሁድ ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. በጎጃም እምብርት የሚደረገው የዐማራ ተጋድሎ ሰልፍ ሊጀመር ሰአታት ብቻ ቀርተውታል፡፡ ከቦታው በስልክ ባደረግነው የመረጃ ልውውጥ ሁሉም የባሕር ዳር ከተማና አካባቢው የሚኖሩ ዐማሮች በጠዋት መስቀል አደባባይ ለተጋድሎ ይገናኛሉ፡፡ ባነሮችና ቲሸርቶች ታትመው አልቀዋል፤ የአባቶቻችን ሰንደቅ ዓላማም ተዘጋጅቷል፡፡
በመታተም ላይ የነበረ በርካታ መጠን ያለው ቲ ሸርት በባንዳ ደኅንነቶች ጥቆማ የታሸገ ቢሆንም በቂ መጠን ያለው ታትሞ ወጥቷል፡፡ የባሕር ዳር ሕዝብ በገንዘብና በሞራል ያደረገው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሰልፉን እየመሩ የሚገኙት ዐማሮች በራሳቸው ተነሳሽነት ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሲሆን ከዐማራነት ውጭ የሚነሱ ጥያቄዎችን የሚያስቆሙ ብሎም በእነሱም ላይ እርምጃ የሚወስዱ ኮሚቴዎች ተዋቅረዋል፡፡
=======================

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.