በቅርቃር ጠገዴ ከሃያ ሺህ በላይ ህዝብ ሰልፍ ወጣ

ወልቃይት ላለፉት ሺህ ዓመታት በትግራይ ስር ተዳድራ አታውቅም-የታሪክ ማስረጃዎችበቅርቃር ጠገዴ ከሃያ ሺህ በላይ ህዝብ ሰልፍ ወጣ ‪#‎ግርማ_ካሳ‬

ጋዜጠኛ መሉቀን ተስፋው እንደዘገበው ዛሬ በቅራቅር ከተማ ከመላው ጠገዴ የመጡ ዐማሮች የተጋድሎ ሰልፍ አካሒደዋል፡፡ መጠኑ ከሃያ ሺህ በላይ የሚሆነው የተጋድሎ ተሳታፊ ወልቃይት ጠገዴን የዐማራ ማንነት ጥያቄ ለማዳፍ የሚደረገው ጥረት ሁሉ እንደማይሳካ ሲገልጽ ውሏል፡፡

የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ትግሬ አማራ ሳይባባል ለዘመናት በሰለም የኖረ ህዝብ ነው። ብዙዎች ከትግራይ ተከዜን ተሻግረው ፣ ከሕዝቡ ጋር ተዋልደው ነው የኖሩት። ከትግራይ ጋር ካላቸው ጉርብትና የተነሳ በርካታ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ እንደ አማርኛም ትግሪኛንም ይናገራል። ሕዝቡ ሲያሻው ጎንደር ሲያሸው ሽሬ ሄዶ ይሸጣል።

በዚህ ህዝብ መካከል ያለውን ፍቅርና መዋደድ በማደፍረስ፣ ትግሬ አምራ የሚል መርዛም ፖለቲካ በማምጣት፣ ሕዝቡ ትግሪኛ ተናጋሪ ስለሆነ ብቻ፣ “ትግሬ ናችሁ” በሚል ከበጌምድ ግዛት ተወስዶ ወደ ትግራይ እንዲጠቃለል ተደረገ። የምእራብ ትግራይ ዞን የሚል ስማዬ መጣ። ገበሬዉን ከመሬቱ እየፋናቀሉ፣ ቁጥራቸው እጅግ በጣ ብዙ የሆኑ የቀድሞ የሕወሃት ታጋዮችን አሰፈሩ። ወልቃይት ጠገዴን ሲስተማቲክ በሆነ መንግድ እንደ ሌሎቹ የትግራይ አካባቢዎች እንድትሆን መስራቱን ተያያዙት። ሆኖም ግን ህዝቡ ሊቀበላቸው አልቻለም። የራሱን ኮሚቴ አቋቁሞ ፣ “እኛ ወደ ጎንደር መቀላቀል አለብን፣ ትግሬነትን በሃይል አትጫኑብን” ብለው አቤቱታቸዉን ሕጋዊ በሆነ መልኩ ለፌዴራል መንግስት አቀረቡ።

በሕወሃት ቁጥጥር ስር ያለው ፍዴራል መንግስቱ የሕዝብን ጥያቄ ለመስማትና ለማስተናገድ ፍቃደኛ ሳይሆን ቀረ። ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌዴሬሽን ጉዳዩች ሚኒስቴር ካሳ ተክለማሪያም እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስቴር ባይ ነኝ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ወልቃት የትግራይ ናት ሲሉ ገለጹ።
ህወሃት የሚቆጣጠረውን ሜዲያ በመጠቀም በርካታ ጊዜያቶች በባስ ከትግራይ እያመላለሰ “የወልቃይት ህዝብ ትግሬነቱን ገለጸ” የሚል ፕሮፖጋንዳ ብዙ ጊዜ ሰራ። ወልቃይት ትግሬ ናት ለማስባል ብዙ ሰላማዊ ሰልፎች ተደረጉ ሲባል ሰልፍቹም እውቅና አግኝተው በትግራይ ክልል ሜዱያ አይደለም በኢቢሲ ሰፊ ሽፋን ተሰጣቸው።እውነተኛ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ግን ሰልፍ እንዳያደርግ እየተከለከለ፣ የተጠሩ ሰልፎች ሕገ ወጥ እየተባሉ የወልቃዩትን ጥያቄ ለማፈን ተሞክሯል። ለወልቃቶች ሶሊዳሪቲ ለማሳየት የተደረጉ የጎንደር እና የጎጃም ስለፎች በአገዛዙ ሽብርተነት ተደረገው ተወሰዱ።