የማላቀውን እንዳምንህ የማቀውን አትዋሸኝ ― በጋዜጠኛ ቶማስ ሰብስቤ

haile Mariam - satenawውሸት በብዙ ቢመዘንም በምታውቀው ነገር ከተዋሸህ በማታውቀው ነገር ማንንም አታምነውም።ምንም እንኳን የማታውቀው ነገር እውነት ቢሆንም የምታውቀውን ሰለዋሸህ ማብቻ እውነታን መቀበል ከባድ ነው።የዛሬ የጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለ ማሪያም መግለጫ ሰከታተል ለራሴ ያልኩትም ይሄን ነው «ክቡር ሃይለ ማሪያም የማላውቀውን እንዳምኖት የማውቀውን አይዋሹኝ» ብያለው።እኔም ከሀገር ውጪ ፤ እሳቸውም ከቤተ መንግስታቸው ሆነው ያየናቸው የጎንደር ቪዲዪዎች ተመሳሳይ ናቸው።ለምን እንዲ አልክ እንዳትሉኝ።መቼም የእሳቸው ሚዲያዎች የህዝቡን አመፅ እና እንቢታ ሰላልቀረፁላቸው እሳቸውም ልክ እንደ እኔ ከማህበራዊ ሚዲያዎች ነው ያዮት።ታዲያ ምን ይጠበስ ካላችሁኝ በጋዜጣዊ መግለጫ የተናገሩትን ስሰማ አቶ ሃይለ ማሪያም በጎንደር ነዋሪዎች እጅ ያዪት ባነሮች አማራን ለአማራ ፣ሻቢያ አማራን እንዲመራን እንሻለን ፣ አፅ ምንትስ ይምጡልን ፣ይቺ ሀገር የአማራ ናት ፣አንድ ህዝብ ፣አንድ ሀገር ፣አንድ ቋንቋ ፣አንድ ሀይማኖት የሚሉ ባነሮችን ነው እንዴ ያዪት አልኩኝ ስለ ሰልፉ ሲያወሩ።እንዲ ከሆነማ ኑ የእኛ መነፅር ውሰዱና እያዩ እንዳላዪ ያደረጎትን የኢህአዴግ መነፅር ያሰቀምጡ እላለው።

የጎንደር የህዝብ አመጽ ወቅት የታዮት ፅሁፎች ፣ መልክቶች እና ጥያቄዎች አሁን ያለው የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር አይገናኝም ብለዋል።በአጭሩ የህዝቡ ጥያቄ መልካም አሰተዳደር እና ኪራይ ሰብሳቢነት ብቻ ከሆነ ትክክል ነው ሌላው ለሌላ ማለቶ ነው።እስቲ ጎንደር በነቂስ ለአለም ህዝብ ያሳየው መልዕክት ኢህአዴግ የወለደው ፖለቲካ እንደሆን ማየት ይቻላል።

የፖለቲካ እሰረኞች ይፈቱ!
ይህ የኢህአዴግ ዋነኛ ሰራ ነው።እስር ቤት አየማቀቁ ያሉ ብዙ ሺ ፖለቲከኞች አሉ።ማንኛውም ሰው በየትኛም ፆታ ፣ አድሜ ፣ሃይማኖት ፣ዘር ይገኝ የኢህአዴግ አካሄድን ከተቃወመ እስር ቤት ቅርቡ ነው።በተለይ አንድ ግለሰብ በተቃውሞው ብዙ ተከታይ ካለው ስም በሚያበላሽ ታርጋ እስር ቤት ይማቅቃል።ነጋዴ ከሆን የገቢ ምንትስ አጭበርብራል በሚል ስም ፣ ጋዜጠኛ ከሆን ሸብርተኛ ነው ፣ፖለቲከኛ ከሆነ ከወዳጄ ሻቢያ ጋር ወዳጅ ነው ፣ የሀይማኖት አባት ከሆነ አክራሪ ነው ፣ ኦሮሞ ከሆነ ኦነግ ፣አማራ ከሆነ ግንቦት ሰባት ፣ የእራሱ ባለስልጠን ሆኖ ኢህአዴግ የሚሰራው ሰራ ካልተመቸው ሙሰኛ ነው በሚሉ ሽፋን ብዙ ሰዎች ታሰረዋል።አሁንም እየታሰሩ ነው።ታዲያ ይህ እውነታ እየሰራ ያለው ኢህአዴግ ሲተገብረው ያልደበረው ጎንደር ሲናገር ለምን ኢህአዴግ አመመው።በሰልፉ ላይም የታሰሩ እና በሽፋን ግፍ ብቻ በእስር ቤት ወገኖቻችን ባይኖሩ ኖሮ አዎ ይህ ስህተት ነው።ግን ያው ኢህአዴግ አይደለህ ያልተመቸህን አታይም።ከጫካ ስትመጣም ኤርትራ ሰላልተመቸችህ ቆረስካት ።ኤርትራን ለባዳ የሰጠ ዛሬ ወልቃይትን ለአማራ መመለስ ለምን ወልቃይትን ለደቡብ ሱዳን የምትሰጥ አሰመሰልከው?

ወያኔ እንጂ የሻቢያ ተላላኪ አማራ አይደለም!
ይሄ ሀቅ ነው።አማራ በታሪክ ታካላኪ ሆኖ አያቅም።ወያኔ አና ሻቢያ በጫካ ብቻ ሳትሆን በስጋ ዝምድና ያላቸው ናቸው።አማራ እንደ ወያኔ እና ሻቢያ ቢሆን ኢህዴን በሚል አይታገልም ነበር።የትግራይ ነፃ አውጪ ብሎ በግርግር ስልጣን የወጣ የኢትዮጵያ ህዝቦች ዴማክራሲያዊ ግንባር ብሎ ሲታገል የነበረው አማራ ዛረ ሀገር ልትሸጥ ነው ብትለው ያስቀዋል የሀገሬን ሰው።ገንጣይነት ፣ ተላላኪነት ፣የፖለቲካ ዘር ፣የህዝብ ንቀት ፣የተወሰኑ ሰዎች ምቾት የፈጠረ እያላ ጣት ወደ ሌላ።ይህም ጣት ቀሳሪውን ይበላዋል።

ነፃነት ለሀገራች!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.