ብዙ የሕወሃት ታጣቂዎችም እየረገፉ ነው ….

13934

ዛሬ ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ ም ከጎንደር ሰቲት ሁመራ መንገድ ደበዝ ላይ በኦራል ሙሉ የወኔ አጋዚ ጦር ሰራዊትመደምሰሱን እና 58 የአጋዚ ጦር መገደላቸውን 2ቱ መማረካቸውን የሚገልጹ ዘገባዎችን እያነበብን ነው።

ጎንደር ከተማ የሰነበተው የአጋዚ ጦር በአርማጭሆ አቋርጦ ወደ ሁመራ ለመሄድ ፈረስ መግሪያ ሙሴባብ ከተማ ሲደርስ ጥቆማ የደረሰው አርሶ አደር ሕዝባዊ ሰራዊት ደበዝ ወንዝ ላይ ጠብቆ ተኩስ በመክፈቱ ነው ሙሉ በሙሉ ሊደመሰሱ የቻሉት።

ደበዝ በአርጭሆ ወረዳ ከጎንደር ከተማ ወደ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሙሴባምብ እና ኩርቢ ከተማ መካከል የሚገኝ ወንዝ ነው።

በዚህ ሰዓት ከኋላ የመጣ ሌላ ረዳት ጦር ጋር ፈረስ መግሪያና ሙሴባምብ ዙሪያ ከቦ እያሸው ይገኛል፥ ከፍተኛ ሕዝባዊ ጦር ወደ ጎንደር ከተማ እየተጠጋ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ሕወሃት የመገናኛ ዘዴዎችን ሁሉ በማቋረጥ የሚወጡ መረጃዎች በተቻለ መጠን ለመቆጣጠር እየሞከረ ነው። በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየተኮሱ የሕወሃት ታጣቂዎች ብዙ ዜጎችን እየገደሉ ቢሆንም በአማራው ክልል ግን እነርሱም በብዛት እየረገፉ ነው። ይሄ ማለት ደግሞ በአማራው ክልል የለየለት የጦርነት አወድማ ሆኗል ማለት ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.