ሕወአት/ወያኔዎች በባሕር ዳር ብዙ ዐማሮችን ገድለዋል (ሙሉቀን ተስፋው)

bd1ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. 

(ይህ ጽሑፍ የዐይን ምስክሮችን በማናገር የተዘጋጀ እንጅ በፍጹም ዐማሮች በትግሬዎች ላይ በበቀል እንዲነሳሱ ለማድረግ ታስቦ አይደለም፤ ይልቁንስ የትግራይ ተወላጆች በሕዝባችን ላይ የሚያደርሱትን ግፍ ባበዙት ቁጥር ወደየት እየሔድን እንደሆነ ቢያቁት መልካም ነው)
ባሕር ዳር እንዲህ ሆነ፡፡ በዕለተ መባቻ ነሃሴ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. ዐማሮች ለተጋድሎ ሰልፍ በባሕር ዳር ከተማ ወጡ፡፡ ሰልፉ በሰላም እየተከናወነ እያለ ዘንዘሊማ አካባቢ ከጎንደር የመጡ ገበሬዎች በወታደሮች መታገዳቸው ተሰማ፡፡
ሕዝቡ በቁጣ ወደ ዓባይ ማዶ ገሰገሰ፡፡ የዓባይን ድልድይ እንደተሻገሩ ባዶ እጃቸውን ባሉ ዐማሮች ላይ ከየት እንደሆነ እንኳ ሳይታወቅ የጥይት ዝናብ ተርከፈከፈ፡፡ ኮበል ግቢ ውስጥና ፊት ለፊት ካለው ኮንዶሚኒየም ወደ ሕዝቡ ጥይት ይተኮሳል፡፡ ፊት ለፊት የነበሩ ዐማሮች ደፋ ደፋ አሉ፤ አንዳንዶች ለዘለዓለም አሸለቡ፤ ለወገኖቻቸው ሰማእት ሆኑ፡፡ ሰውን ለማዳን የሰው ደም ፈሰሰ፡፡ የብዙ ዐማሮች ሕይወት እንደዋዛ ተቀጨ፡፡ አንዳንዶች በቀይ መስቀል አምቡላንስ ወደ ሆስፒታሎች ተወሰዱ፡፡
ይህ ከሆነ ከቀናት በኋላ ብዙ ጉዶች ብቅ እያሉ ነው፡፡ ዛሬ ከወደ ባሕር ዳር የሰማነው መረጃ ግን እጅግ ያማል፡፡ ያማል የሚለው በራሱ ገላጭ አይደለም፡፡ ብቻ ምን ልበላችሁ? ይሆናል ተብሎ የማይታሰብ ጉድ ነው፡፡ ሰልፉ እንደሚደረግ የሚያውቁ በባሕር ዳር የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ዐማሮችን ለመጨፍጨፍ አስቀድመው ተዘጋጅተው ኖሯል፡፡ ይህን የሞት ድግስ ገቢራዊ ለማድረግ ደግሞ በዓባይ ማዶ ኮንዶሚንየሚ የሚኖሩ ትግሬዎች በተጠንቀቅ ላይ ሆኑ፡፡
ዐማሮች በሰላማዊ መንገድ የሕልውናቸውን ጉዳይ እያሰሙ ከዚህ ሰፈር ሲደርሱ ትግራውያን የሥርዓቱ ደጋፊዎች ከኮንዶሚንየም ፎቆች ላይ ከሚገኙ ቤቶቻቸው ውስጥ ሆነው መስኮቶቻቸውን ከፍተው ወደ ታች መሪ የነበሩ ዐማሮችን ጭንቅላት በጥይት ያፈርሱ ጀመር፡፡ እነርሱ ዳንኪራ እረገጡ የዐማራ እናቶች አስለቀሱ፡፡ ማንም እነርሱን የጠረጠረ አልነበረም፡፡ ግን እንደህ እንደሆነ በየሕንጻዎቹ ኮሪደሮች ከማን ቤት ጥይት ይተኮስ እንደነበር ያዩ ሰዎች እነዚህ ትግራውያን እንደሆኑ ዛሬ በግልጽ መናገር ጀመሩ፡፡ ስለምስክሮቼ ደኅንነት ባልጨነቅ ኖሮ ማን ማነን እንዳየ እራሱ ብናገር ደስ ባለኝ፡፡ ግን ጊዜው አይደለም፡፡
የአንደኛዋን ነፍሰ በላ ትግሬ ታሪክ በዚህ መልኩ ያነጋገርኳቸው ሰዎች ገለጹልኝ፡፡ ሲ/ር ንግሥት ትባላለች፡፡ በባሕር ዳር ነዋሪ ትግሬ ስትሆን የክልሉ ጤና ቢሮ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ ትሠራለች፡፡ በቅርብ ጊዜ ወዲህ በምን እንደሆነ በማይታወቅ መልኩ ግን ቢሮ ገብታ አታውቅም፡፡ ይህች ሴት ባለቤቷም የሥርዓቱ ቀንደኛ ደጋፊ ነው፡፡ እነ ሲ/ር ንግሥት ቤት መሣሪያ በየዓይነቱ አለ፡፡ ሽጉጥ፣ ክላሽንኮፍ ሌላም ሌላም፡፡
የእነዚህ ወያኔዎች ልጅ በእናት አባቱ መሣሪያ ወዳጅነት የተነሳ ያለ አበሳው ሕይወቱን አጥቷል፡፡ የሆነው እንዲህ ነው፡፡ የአክሽን ፊልሞችን በዲሽ እያሳዩ ያሳደጉት ልጅ አንድ ቀን ሲ/ር ንግሥት ያስቀመጠችውን ማካሮቭ ሽጉጥ ፊልሙ ላይ እንዳለው ለማስመሰል ሲሞክር ሕይወቱን ለዘለዓለሙ አጣው፡፡ ይህች ሴት እንኳን ጠላቴ ናቸው ለምትላቸው ዐማሮች ቀርቶ ለገንዛ ልጇም አልራራች፡፡ ቀጥታ ባትገድለውም እንዲሞት ምክንያቷ እርሷ ነች፡፡
ዓባይ ማዶ ኮንዶሚንየም የሚኖሩ ትግሬዎች በእሁዱ ሰልፍ በተለይ ደግሞ ኮበል አካባቢ ያለቁትን ዐማሮች እነርሱ ገድለዋል፡፡ ከሌላ ቦታ የሚኖሩ ትግሬዎችም ዓባይ ማዶ ኮንዶሚንየም ከሚኖሩ ትግሬዎች ቤት ተስብስበው በንጹሐን ዐማሮች ላይ ይተኩሱ ነበር፡፡
ይህ የለየለትን አረመንያዊ ጭፍጨፋ ተሳታፊ የነበሩ ሰዎችን ስምና ታሪክ በምንችለው ሁሉ ለሕዝብ ለማሳወቅ እንጥራለን፡፡
ለተጋድሎ የወጣው ሕዝብ ወደ ዓባይ ማዶ ሒዶ በጥይት እንዲቆላ ከመሆኑ ጀርባ ምን አለ? አሽራፍ አካባቢ ለምን የመካለከያ ካምፕ በአስቸኳይ ተዘጋጀ? ከነዚህ ሁሉ ጀርባ ምን አለ? ወደ ፊት የሚመልስ ይሆናል፡፡
እኔ ግን ይህን ስሰማ ብዙ ነገሮች ወደ አእምሮየ መጠብኝ፡፡ ዛሬ በስሜትና በንዴት የምጽፈው አይጠቅምም፡፡ ብቻ ለዐማራ ወጣቶችና የነጻነት ታጋዮች ብዙ ትምህርት የሰጠ ይመስለኛል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.