በአገር ስላለው ሁኔታ አጭር ዘገባ – ‪#‎ግርማ_ካሳ‬

13876663_10209904936370799_8304940350771992382_n

ሐምሌ 4 ቀን 2008 ዓ.ም

– በዛሬ እለት በጎንደር ኮሎኔል ደመቀ ፍርድ ቤት መቅረብ ነበረበት። ሆኖም በፍርድ ቤቱ ብዙ ሺህ ስለነበረ ዳኞቹ ፈርተው፣ ዛሬ ሳያቀርቡት ቀርተዋል።፡በጎንደር የደብረጹዮን ቴሌ ኔትዎርክ ዘግቷል።

– በአርማጭሆ ታጣቂዎች እሰር ቤቶችን አጋይተው በዚያ የነበሩትን እስረኞች አስፈትተዋል። በገጠር ዉዲያው ቢቀንስም በአነስተኛ ደረጃ እንደቀጠለ ነው።

– በአማራው ክልል ገጠሪቷ ክፍል ከታቦት ጀርባ በመሆን ወያኔዎች ሕዝቡን ለማግባባት እየሞከረሩነው። ጳጳስም ማስታረቅ፣ “አንተም ተው ፣ አንተም ተው” በማለት ብሄራዊ እርቅ እንዲኖር መስራት ሲጠበቅባቸው፣ በቴሌቭዥን ቀርበው ቆብ የደፉና መስቀል የይዙ ጌታቸው ረዳ ነው የሆኑት። ሕግ ያለ ይመስል፣ ሕዝቡ ለሕግ መገዛት አለበት ሲሉ አስጠንቅቀዋል። በንጹሃን ዜጎች ላይ ሰይጣናዊ የጭካኔ ሥራ የሰሩትን ወንጀለኞች ማውገዙ ግድ የለም ይቅር ፣ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እንኳን ማሳሳቢያ እኝህ ጳጳስ ለመስጠት አልደፈሩም። የካቶሊኩ ፖፑ ያኔ ለፋሺስት ጦር ቡራኬ ሰጥተው ነበር።፡ህዝብ እንዲጨፈጨፍ። አሁንም እኝህ ጳጳስ ለአጋዚ ቡራኬ በመስጠት ከዚያ ያልተናነሰ ነገር ነው ያደረጉት።

በዚህ አጋጣሚ ዉጭ አገር ያለው ትክክለኛው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ለሕዝቡ ንግግር ቢያደረጉ ጥሩ ነው እየተባለም ነው።

– በጎጃም ለሶስተኛ ቀን ሥራ የለም፣ ሱቅ የለም፣ ሁሉም ነገር እንደተዘጋ ነው።

– የፊታችን ቅዳሜ እና እህዱ በተለያዩ መርሃ ግብሮች የተለያዩ ሰልፎች ታስበው ነበር። ይህ መርሃ ግብር አንዳንድ ለዉጦች ተደረገዉበታል። ሰልፎቹ በሙሉ የሚሆኑት ነሐሴ 8 ቀን እሁድ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ከተማን ሰልፍ ይደረጋል።

ሸዋ- አዲስ አበባ፣ ደብረ ብርሃን፣ ሸኖ፣ አንኮበር፣ ደብረ ሲና፣ ሞላለ ና ሸዋ ሮቢት
ጎጃም – ደብረ ማርቆስ፣ ዳንግላ፣ ደጀን፣ኮሶ በር፣ ቡሬ፣ ሞጣ፣ዴት
ወሎ -ከሚሴ፣ ኮምቦልቻ ፣ ደሴ፣ወልዲያ፣ መቄት፣ላሊበላ፣ ሰቆጣ፣ ቆቦ፣ አላማጣ

– የሚደረጉ ሰልፎችን ለማጨናገፍ በወሎችና በጎጃም ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ ወያኔዎች እያደረጉ ነው። ወጣቶች ማፈስ የመሳሰሉትን ….

– አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ምን ደረጃ ላይ እንዳሉ እስከአሁን በግልጽ የታወቀ ነገር የለም። አቶ ገዱ መፈንቀለ መንግስት እንደተደረገባቸው የሚያመለክት ዜና ከወደ ህወሃት ደጋፊዎች መስማታችን ይታወሳል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.