ቅኝ ተገዥነቱን ያወቀ ሕዝብ  በከፊል ነፃ ነው! [ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት]

ሐሙስ ነሐሴ ፭ ቀን ፪ሺህ፰  ዓ.ም.              ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፳፩

Moresh
የኢትዮጵያ ሕዝብ በትግሬ ወያኔ ቅኝ ተገዥ ከሆነ ድፍን 25 ዓመት ሆነው። በእነዚህ ረጅም ዓመታት፣ የተማሩትም ሆነ ያልተማሩት ዜጎች፣ በቅኝ ተገዥነት መያዛቸውን ያወቁትም ሆነ ለማወቅ የጣሩት በጣም ጥቂቶች ናቸው። እነዚህ በቅኝ ተገዥነት ተይዘናል ያሉት የጥቂቶቹ ድምፅ፣ በብዙኃኑ፣ ከሁሉም በላይ በጎሣ ፖለቲከኞቹ ድምፅ ተውጦ፣ ወያኔ፣ ያላንዳች ሀግ ባይ፣ ሩብ ምዕተ ዓመታት  የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅምና ሉዓላዊነት በእጅጉ የጎዱ ሥራዎችን እንዲሠራ ሠፊ ዕድል ሰጠው። በመሆኑም የኢትዮጵያዊነት አያያዥ ማገርና ወራጅ፣ መሠረትና ጭምጭም የነበሩትን፣ የኢትዮጵያዊነት ዕሴቶቻችን ከሥራቸው ነቀላቸው። ሕዝቡን በነገድ ከፋፍሎ እሣትና ጭድ አደረጋቸው። የኢትዮጵያ ነገዶች ሙጫ በመሆን ከሌሎች ነገዶችና ጎሣዎች ጋር ሰምና ፈትል ሆኖ፣ ኢትዮጵያዊነትን ሲገነባ የኖረውን የዐማራ ነገድ፣ በዘር ጠላትነት ፈርጆ፣ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ፈጸመበት። አምስት ሚሊዮን ዐማራ ከምድረ ኢትዮጵያ እንዲጠፋ ተደረገ። በወለጋ፣ በኢሉባቡር፣ በከፋ፣ በሐረርጌ፣ በጎጃምና በጎንደር ይኖሩ የነበሩትን ዐማሮች በግፍ ሀብት ንብረታቸውን ነጥቀው ለርሃብ፣ ለድህነትና ለአገር አልባነት አሳልፎ ሰጣቸው። ይህ ዓለም በዝምታ እየተመለከተው ያለው የዘር ጥቃት፣ ዛሬ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት ዐማሮች የቅኝ አገዛዙን ሰንሰለት በጣጥሰው፣ ፍፁም ነፃ የሆነ ዐማራዊ ማንነታቸውን አረጋግጠው፣ የኢትዮጵያን ትንሣዔ ለማብሰር ከአፋኙ የወያኔ የስለላና የአፈና መዋቅር ኃይል ጋር የሞት ሽረት ትግል እያደረጉ ይገኛሉ።

የዐማራው ነገድ ዛሬ በትግሬ ወያኔ ቅኝ ተገዥ መሆኑን ከማወቅ አልፎ፣ ለነፃነቱ ቆርጦ የሕይዎት መስዋዕትነት እየከፈለ ነው። በዚህ የሞት ሽረት ትግል ውስጥ፣ እስካሁን በጎንደር ከተማ፣ አዘዞ፣ ቆላድባ፣ አርማጭሆ፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣ ወልቃይት፣ ጋይንት፣ ደብረታቦር፣ ባሕር ዳር ወዘተርፈ ቁጥራቸው ገና በውል ያላወቅናቸው አያሌ ወንድምና እህቶቻችን ባልሞ ተኳሾች የጥይት አረር ወድቀዋል። በርካቶቹ በወያኔ እስር ቤቶች የመከራን ጽዋ እየተቀበሉ ነው። ዐማራውን ለዚህ ግፍ ያበቁት በወያኔ የመከላከያ፣ የፖሊስና የፀጥታ ሠራቶች የተቀጠሩ ብቻ ሳይሆኑ፣ ከሕዝቡ ጋር የሚኖሩት በየኮንዶሚኒየሙ በሰፈራነት የተሰገሰጉት ትግሬዎች መሆናቸውን ስንገነዘብ፣ «ለካ እስከ ዛሬ በጉርብትናም ሆነ በጋብቻ ከእነዚህ ሰዎች ጋር የፈጠርነው ግንኙነት፣ እኛን ለማጥቂያ ውስጣችንን ገልጠው እንዲያዩን ሁኔታዎችን ያመቻቸ ነው፤» ብለን እንድናስብ አስገድደውናል።

ባሕር ዳር እና ጎንደር በጥይት ለተቀጠፉት ሰዎች ገዳዮቹና አስገዳዮቹ በከተሞቹ ነዋሪ የሆኑት የወያኔ የውስጥ አርበኛ ትግሬዎች መሆናቸውን በተጨባጭ አረጋግጠናል። ይህም «ወያኔን እና ትግሬን ለዩ» ለሚሉ የዋሕ ፖለቲከኞችና የሰብአዊ መብት ጠበቆች ነን ለሚሉ ሁሉ የሚያራምዱት ሀሳብ መሠረት የሌለው መሆኑን አሳይቷል። ሕዝብን በሙሉ የክፋት ሥራ ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ አይደለም የሚባለው፣ ሕዝቡ የጥፋት ተባባሪ አይደለም ከሚል መነሻ ሳይሆን፣ ሕዝብን በሕዝብነቱ መወንጀልም ሆነ ለጥፋቱ ተጠያቂ ማድረግ ለችግሮቹ ዘላቂ መፍትሔ አያስገኝም ከሚል መነሻ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል። ዛሬ የትግራይ ሕዝብ በወያኔ አገዛዝ ተጠቃሚ መሆኑ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም። ሌላውን ቁሣዊና ለወዲፊቷ ትግራይ ልማትና ዕድገት የተሠሩትን መጠነ ሠፊ ሥራዎች ትተን፣ በአገዛዙ ባለሥልጣኖች እንደ ዐማራውና ኦሮሞው አይጠረጠሩም፣ አይፈተሹም፣ በሥራቸው የመረጃ ታኮ አይለጠፍባቸውም፣ የመሥራትና የመንቀሳቀስ መብታቸው የተገደበ አይደለም፤ የፈለጉትን  ሠርተውና ተናግረው በሰላም ተኝተው ያድራሉ። ይህ ጥቅም አይደለም የሚል ካለ፣ ይህን መብት ያጡት የዐማራ ልጆች ጥቅሙ ከቁሣዊ አልፎ የኅልውና እና የነፃነት ዋጋ ያለው መሆኑን እየከፈሉት ባለው የደምና የሕይዎት ዋጋ ሊማር ይገባዋል።

ከሁሉም በላይ፣ የትግራይ ሕዝብ፣ ልጆቹ የሁሉም ነገር አድራጊና ፈጣሪዎች መሆናቸውን ስለሚያውቅ፣ በልጆቹ ድርጊት ይመካል። ከመመካትም አልፎ እየኮራ ሌሎችን ሲያዋርድ እያየን ነው። ይህም ለአጉል ትዕቢት ዳርጎት ሌሎችን «ሽንታም፣ ፈሪ» በማለት  በየምርመራ ጣቢያውና በየፓልቶክ ክፍሉ የምንሰማው የዕለት ተዕለት ስድባቸው ነው። ይህ ድርጊት የሌሎችን ነገድ ልጆች አዕምሮ አያነቁርም፣ ደም አያፈላም፣ አያስቆጭም የሚል ካለ «ግሞ ሲሉህ፣ ጥንቦ በለው» ተብሎ ያላደገ የማንነት መገለጫ ዕሴት የሌለው፣ የተዋራጅ ሕዝብ ባህል ብቻ ነው። በመሆኑ፣ ከ25 ዓመታት ትዕግሥትና የአብሮነት ፍላጎት በመነጨ፣ ዐማራው ወያኔ የጣለበትን ዕዳ፣ ያሸከመውን የመከራ ቀንበር ተሸክሞ መቆየቱ ግልጽ ነው።

የዐማራው ሕዝብ ዛሬ ግን ከመከራ አልፎ፣ ማንነቱን በመነጠቁ «አሻፈረኝ፣ መከራው በዛብኝ፣ ሸክሙ ከምችለው በላይ ሆነብኝ፣ ግፉ ከአናት በላይ ወጣ፣» ብሎ ማንነቱን ለማስከበርና ነፃነቱን ሙሉ በሙሉ ለማስመለስ ከአፋኙ የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ሠራዊት ፊት ለፊት በባዶ እጁ እየተጋፈጠ ይገኛል። ይህም ዐማራው በቅኝ ቅዛት መያዙን ከማወቅ አልፎ፣ ለነፃነቱ ቁርጠኛ ውሣኔ ላይ የደረሰ መሆኑን ያሳያል። ካልቆረጡ ከግብ አይደረስምና! በዚህ ረገድ የቁርጠኝነቱን ጉዞ፤ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በከፈተው የጀግንነት ድርጊት፣ ለዐማራው ወጣት አርአያነቱን አሳይቷል። ዐማራው ማንነቱን አስጠብቆ የኢትዮጵያ ትንሣዔ አብሳሪ የሚሆነውም በዚህ መንገድ ብቻ መሆኑን የትግሬ-ወያኔ ባሕሪ አስተምሮናል። ስለዚህ ትግሉ፣ መስዋዕትነትን ቀንሶ፣ ባጭር ጊዜ ውስጥ የድሉ ባለቤት የሚሆንበትን መንገድ መከተል ብልኅነት ብቻ ሳይሆን፣ አዋቂነትም ነው።

ለዚህም የሚረዳው፣ በየቀበሌውና ወረዳው የጎበዝ አለቆችን በመምረጥ የተደራጁ ቡድኖችን መፍጠር ሲቻለው ነው። በየደረጃው የተመረጡ የጎበዝ አለቆች በተመሳሳይ መልክ ከሚደራጁ አቻዎቻቸው ጋር ተያያዥና ተጋጋዥ የሆኑ ሥራዎችን ለመሥራት ሁኔታዎች በፈቀዱት መጠን የግንኙነት ሰንሰለት መፍጠር እጅግ አስፈላጊና ጠቃሚም ነው። ይህ ግንኙነት በአስተማማኝ ሁኔታ ከተመሠረተ በኋላ፣ የወያኔን የስለላና የአፈና መዋቅር ኃይል ለማሳሳት፣ የገንዘብ አቅሙን ለማዳከም፣ በተለያዩ ቦታዎች የሕዝባዊ እንቢተኝነቱ እንቅስቃሴን፥ ሰልፍና የመሳሰሉን፣ ማካሄድ። ለትግሬ-ወያኔ አፋኝ ኃይል፣ የኃይል ምንጭ፣ የሥንቅና የትጥቅ አቅርቦት ክምችት ያለባቸውን ቦታዎች በማጥናት ድንገተኛ ወረራ በማድረግ የሕዝብ ማድረግ የግድ ይላል። ይህ ሁሉ ሲሆን፣ አመራሩ ከውስጥ ከሕዝቡ መሀል ያሉ፣ የንቅናቄው ተሳታፊዎች አምነው የመረጧቸውን እንጂ፣ ከርቀት «መንፈስ ነን» የሚሉ የአየር በአየር የፖለቲካ ሰዎች ነን ከሚሉት ጋር እንቅስቃሴው እንዳይያያዝ ጥንቃቄ መደረግ አለበት። «የአህያ ባል ከጅብ አያድንም» እና በዚህ ረገድ ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው። ወያኔ እንኳን ሰበብ አገኝቶ፣ ራሱ ወንጀል ፈብርኮ፣ ሰዎችን ማሰር መግደሉ ይታወቃልና፣ ከውጭ ሆነው የሚፎክሩ ድርጅቶች፣ ለሕዝቡ መመቻ፣ መረጃ እየሰጡ ናቸውና በወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ባለቤቱ ዐማራው ራሱ እንጂ፣ ሌሎች አለመሆናቸውን በግልጽ ሊያውቁት ይገባል።

በመሆኑም የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ የመላው ዐማራ ጥያቄ በመሆኑ፣ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የወሎ፣ የሸዋ፣ የሐረርጌ፣ የአዲስ አበባ፣ የወለጋ፣ የአርሲ፣ የከፋ፣ የጋሞጎፋ፣ የሲዳሞ፣ የባሌ እንዲሁም በዓለም ላይ በስደት የሚኖረው ዐማራ የትግሉ አካል እንዲሆን፣ የንቅናቄው አስኳል የሆነው የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ የመሪነቱን ቦታ በመያዝ፣ ሕዝቡን መድረስ ይጠበቅበታል። ከሁሉም በላይ የእንቅስቃሴው ባለቤቶች «እኛ ነን፣ እኔ ነኝ» ለሚሉ ወገኖች አቅማቸውንና ቁርጣቸውን እንዲያውቁ፣ የንቅናቄውን ዕለታዊና ሳምንታዊ ዘገባዎች ለዓለም ማኅበረሰብ የሚሰማ፣ ሕዝቡ የሚፈልገውን ርዳታ ተቀብሎ በትግሉ ውስጥ ላሉት አመራሮች ማስረክብ የሚችል ታማኝ ግለሰብ ወይም ቡድን ካለ እርሱን፣ ከሌለ በፍጥነት ተሰይሞ፣ ሕዝቡ እንዲያውቀው ቢደረግ ውንዥንብሩን ያጠራዋል፤ የሰከነ ሥራም ለመሥራት ያስችላል ብለን እናምናለን።

ሌለው፣ ንቅናቄው ሊመራባቸው የሚገቡ ቋሚ መፈክሮች ያሹታል። መፍክሮቹን ማንም እንደፈለገ እንዳይለጥጣቸው ከወልቃይት ጠገዴና ከዐማራ ማንነት ጋር የተያያዙ፣ ይህንም ባጭሩ መልዕክት የሚያስተላልፉ ሊዘጋጁ ይገባል እንላለን። ይህ ሲሆን ጎንደር ላይ የተቀጣጠለው የዐማራ የማንነት ጥያቄ፣ ቅኝ ገዥውን ቡድን ድባቅ መትቶ፣ ዐማራው ማንነቱናና ኅልውናውን አስጠብቆ፣ የኢትዮጵያን ነፃነት ዕውን ለማድረግ የበኩሉን አስተዋፅዖ ያደርጋል ብለን እናምናለን። በዛሬዪቱ ኢትዮጵያ የዕውቀትም ሆነ የሀብት ባለቤቶች እነርሱ መሆናቸው ስለሚታወቅ፣ በዚህ ነፃነት ከማንም ይልቅ ተጠቃሚዎቹ ትግሬዎች ይሆናሉ። ስለዚህ በነገይቱ ኢትዮጵያ ትግሬዎች ያላቸውን ዕውቀትና ሀብት በሥራ ላይ አውለው በነፃነት ለመጠቀም፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ ነፃ መውጣቱ ፍቱን አብነት ነው። ለዚህም ከጠፊው የወያኔ ቡድን ጋር ሳይሆን፣ ከዘላለማዊው የኢትዮጵያ ሕዝብ እና ከታሪክ ጋር መቆም ይጠበቅባችኋል።

ወያኔ ለትግሬም ሆነ ለኢትዮጵያ አጥፊ እንጂ፣ አልሚ አይደለም። የትግራይ ተወላጆች፣ በጊዜአዊ ሥልጣንና ጥቅም ተገብዛችሁ ሊሆን ይችላል፤ ይህ ግን ዘላቂ አይደለም። ከዘላቂ ጥቅም፣ ክብር፣ ማንነትና ከሠፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እንድትቆሙ ጥሪያችን እናቀርባለን።

 

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

የዐማራነት ማንነት በትግላችን ያብባል!

ዐማራነት ነፃነትና ዕኩልነት ነው!                                        

ዐማራነት ፍትሕና ኢትዮጵያያዊነት፣ ጀግንነትና መስዋዕትነት ነው!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.