በዐማራው ሕዝብ እየተከናወነ ያለው ሕዝባዊ ዐመጽ ባለቤት የዐማራው ሕዝብ ነው [ በኮለንበስና አካባቢው በሚኖሩ የዐማራ ተወላጆች የወጣ መግለጫ]

Amhara - satenaw 2

በወለቃይት የዐማራ ማንንት ጥያቄ የተነሳው ሕዝባዊ አመጽ በአማራው ሕዝብ ውስጥ ታፍኖና ተዳፍኖ የቆየውን የነጻነት ጥያቄ በመቀስቀሱ፤ ዛሬ በመላው ጎንደር፡ጎጃም፤ ወሎና ሸዋ ወ.ዘ.ተ ተቃውሞው እየተጠናከረና እየተስፋፋ ይገኛል።
በተመሳሳይ ሁኔታ በኦሮሚያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ሕዝባዊ ተቃውሞና አመጽ እየገፋ በመምጣቱ የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባርን እንደ ማይሽር የጎን ውጋት ሰቅዞ ይዞታል።
አንባ ገነኖች ቁርጠኛውና አስደንጋጩ የ ሕዝብ አመጽ እየገፋ ሲመጣ ይርበተበታሉ። የሚይዙት የሚጨብጡትንም ያጣሉ። ፋታ ያገኙ እየመሰላቸውም አንዱን ክሌላው የማጋጨተና የማናከስ ዕኩይ ሴራቸውን ያውጠነጥናሉ። ስለ አንድነት፤ ስለ ጋራ እድገትና ብልጽግና ሰለ ሰላምና ነጻነት፤ ስለ ዴሞክራሲ ሰባኪና ጠበቃ ይሆናሉ። ነገር ግን የተጠራቀም ጭቆና የወለደው ሕዝባዊ አመጽ የረዥም ጊዜ መክራ፤ ስቃይ፤ መታፈን፤ ነጻንትን መገፈፍና መዘረፍ ውጤት በመሆኑ ለዐንባ ገነኖች ከንቱ ድለላ የሚበገር አይሆንም። የሚራመድበትን ጎዳና ና የዐመጹን መዳረሻ ግብ መክሮ፤ ለክቶና አስልቶ የሚንቀሳቀስ በመሆኑ ለተራ ድለላ፤ስብከትና ቁልምጫ የሚሰጠው ጊዜም ሆነ ቦታ የለውም።
የዐማራው ሕዝብ የማንነቱን ጥያቄ ሲያነሳ የትግራይ ነጻ ዐውጭ ግንባር ክፍጥረቱ ጀምሮ አሁን እስካለበት ደረጃ ድረስ ያደረሰበትን መከራ የፈጸመበትን ግፍና ግድያ በዐይነ ሕሊናው እያየ የተከናወነበትን ኢ-ሰብዐዊ ድርጊት በዕዝነ ለቦናው እያብሰለሰለ፤ የነጻነት ዕጦት ውጤት መሆኑን በማረጋገጥና በመረዳት ነው። ስለሆነም ለነጻነት ዕውን መሆን በሚያደረገው ዐመጽ ላይ ምንም ዓይነት ድርድር አየኖረውም። የ ዐማራ ሕዝብ በትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር አገዛዝ በቃኝ ብሎ ሲነሳ ትላንት የተቀሰቀሰበትን በውጤቱም እስክዛሬ ድረስ ወገኔ ብሎ ባየው ዘንድሁሉ እንድ ጠላት ተቆጥሮ እንዲገደል እንዲሰቃይና እንዲሰደድ የተፈጸመበትን ሁሉ እያሰታወሰ ሲሆን ለወደፊቱም ይህ ዓይነቱ ድርጊት እንዳየፈጽመ የማያወላዳ መስረት ለመጣል ምቹ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ግቡ አድርጎ ነው።
እውነቱ ይህ ሆኖ እያለ፤ ሰሞኑን ላም ባለዋለበት ኩበት ለቀማ እንዲሉ አንዳንድ ብልጣ ብልጥ ፖለቲከኞች የ ወቅቱን የአማራ ዐመጽ እነርሱ እንደሚመሩት፤ትላንት በአማራው ህዝብ ሰቃየና መክራ ያላጋጡ እንደነበር የተዘነጋላቸው ይመሰል፤መታፈኑ፤ ማንነቱን ማጣቱ፤ውገኔ ብሎ ያሰበው ሁሉ በትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር በአማራው ላይ ያውጠነጠነው ሴራና ፕሮፖጋንዳ አርጋቢዎችናቀስቃሾች የነበሩ መሆናቸውን ወደ ጎን በመተው ትግሉ ባለበት ሁሉ አለን፤እኛ እንመርሃልን፤ በሚል የሳይበር አንበሶች የሜዳው ትግል ባዶዎች ለሰላማዊ ሰልፍ ጋጋታና መሰረት ለሌለው ሆይ ሆይታ ሲራወጡ ይታያል።
በመሰረቱ፤
• ትላንት አማራው ሕዝብ በወተር፤ በአርባ ጉጉ ከነነፍሱ ገደል እየተወረወረ ባለቀብት ጊዜ አየዞህ አለን ክጎንህ ቆመናል ፤ ያለው አልንበርም። ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተን መከራና ሰቃይህን ላልስማ እናስማልህ ያለ አልነበረም።
• በቤኒሻንጉል ጉምዝ የአማራው ስግስ እየተመተረ ሲበላ፤ ስው ሰውን አይበላም፤ የሃሰት ወሪ በማሰመስል እውነቱን ሲያስተባብሉ የነበሩ ሁሉ ዛሬ ተቆረቍሪ መስለው ከጎንህ አለን ቢሉ፤ ያለወለዱት ልጅ ቢለኝ አባባ አፌን አለኝ ዳባ ዳባ የሚለው የተረቱ ቢጤ ነው።
• በጉራፈርዳ ሓብትና ንብረቱ ተቀምቶ፤ ለህል ያላነሱ ለስራ ያልደረሱ ሕጻናቶቹን ይዞ በረሃብ አለንጋ ሲቀጣና ቤቱ ፈረሶ፤ ንብረቱ ተወርሶ ሲባረር ችግርሕን እንካፈል፤ ብሶትህን አደባባ አውጥትን እናስማልህ ያለው አልነበረም።
• አማራነቱ እንደ ወንጀል ተቆጥሮ በወያኔ አስተባባሪነት ከወለጋ ተፈናቅሎ ቡሬ ከተማ በኮሌራና በወረርሽኝ በሽታ ሲያልቅ ብሶቱን ለማሰማት አንድም ጥረት ወይም ሙከራ አልተደረገም።
• በወግቃይት፤ በጠገዴና በጸለምት የአማራ ማንነት ጥያቄ ህዝባችን በማነሳቱ በቅኝ ገዥው የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት እየታፈነ የተገደለውን፤ በቀበሮ ጉድጎድ የተረሸነውንና ባዶ ስድሰት ክሚሉት ከመሬት ውስጥ ባዘጋጁት ጠባብ እሰር ቤት ከነነፍሱ አፈር እያለበሱት ያለቀው የዐማራ ተወላጅ በደልህ በደሌ፤ሰቃይህ ስቃዬ፤ ሞትህ ሞቴ በሚል ምንም ያደረጋችሁት እንዳልነበረ ከሕሊናችሁ ጋር ተጠያየቁ።

ክዚህ በላይ የተዘረዘሩት፤ በዐማራው ህዝብ ላይ ከደረሱበት ፍዳዎች በጣም አነሰተኛው ሲሆን ትናንት የዚህ ሁሉ ስለባ የዐማራው ሕዝብ እንደነበር የዘነጉት፤ ጨቆኝ፤ በዝባዥ ዐማራ እንዳላሉት ሁሉ ዛሬ ክያለበት በመጥራራትወገናችን ነህ ክትግልህ ጋር ነን ለሚለው ከንቱ የአፍ ውዳሴን ድለላ የሚታለል አይሆንም። በዕውን ልገነዘቡ የሚገባቸው ዐብይ ቁም ነገር የሕዝብን ትግልና ዐመጽ በማጭብርብር፤ በገንዘብ በመደለል፤በአሉባልታና በወሬ ዘመቻ፤በመኩራራትና ገዝፎ ለመታየት በመሞከር የፖለቲካ ጥምን ማርካት ያለመቻሉን ነው።
የህንን መሰረት በማድረግ እውነቱን አውቅውና ተገንዝበው፤ የዐማራው ሕዝብ እያከናወነ ላለው ዐመጽ ልዮ ልዮ የትግል አጋርነት መግለጫ መንገዶች ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠቡ በጥብቅ እናስታውቃለን። የዐማራው ሕዝብ ያለው ሕዝባዊ ዐመጽና እንቢተኛነት ባለቤቱ የዐማራው ሕዝብ መሆኑን መቀብል ግዴታችሁ ነው። የኢትዮጵያን ስም አንገቦ የማጭበርበሪያ መሳሪያ አድርጎ በህዝብ እንቅሰቃሴና ዐመጽ ላይ መነገድ እንደማይቻል ክወዲሁ እናስገነዝባለን።
የዐምርው ሕዝብ የተያያዘውን የነጻነትና የማንነት ጥያቄ ተግባራዊ እያደረገ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቹና ዕህቶቹ ጋር የወደፊት ኢትዮጵያን ዕጣ ፈንታ ለመወሰን ፍጹም ወንድማዊ፤ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በተከተለ መግባባትን በፅና መሰረት ላይ ኢትዮጵያን ለማቆየት እንደምንችል ጽኑ እምነታችን ነው።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!!

የዐማራ ማንነት በትግላችን ያብባል!!!

ዐማራነት ነጻነትና ዕኩልነት ነው!!!

ዐማራነት ፍትሕነትና ኢትዮጵያዊነት፤ ጀግንነትና መስዋዕትነት ነው!!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.