ሰበር ዜና: የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ተቀባ ተባበል እና የሰሜን ጎንደር የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊው አቶ ዋኝው ዋዋ ከስልጣናቸው በሕወሓት ሰዎች ተነሱ

Gonder Jegna Ihitየጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ተቀባ ተባበል እና የሰሜን ጎንደር የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊው አቶ ዋኝው ዋዋ ከስልጣናቸው በሕወሓት ሰዎች አማካኝነት እንደተነሱ መረጃ ደርሶናል ። ምንጫችን እንደገለፁት ሁለቱ ባለስልጣናት በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጉዳይ ለዘብተኛ አቋም በመያዛቸው ህወሓቶችን ጥርስ ውስጥ ገብተው ሰንብተዋል። በዚህም ምክንያት በስልት ለሌላ ስራ እንደታጩ በማስመሰል ከስልጣናቸው እንዲወርዱ ተደርጓል ። በምትካቸው ፀረ አማራ አቋም ያላቸው የህወሓት ስራ አስፈፃሚዎች ውስጥ ለውስጥ እንደተሾሙም ምንጫችን አያይዘው ገልፀዋል። በመሆኑም የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል።በማንኛውም ሰአት ከጎንደር አፍነው ሊወስዱት ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል። የአርማጭሆ የጠገዴ እና የወልቃይት ገበሬዎች ከጎንደር ህዝብ ጋር ሆነው ሃምሌ 6 ቀን 2008 ዓም ኮለኔል ደመቀ ዘውዱን ለአቶ ተቀባ እና ለአቶ ዋኘው በአደራ መስጠታቸው ይታወሳል ።