ህብር ሬዲዮ ነሐሴ 8 ቀን 2008 ፕሮግራም

Habtamu-Assefaኮ/ል ደመቀ ዘውዱን ለሕወሓት አሳልፈን አንሰጥም ያሉ በጎንደር የብአዴን አመራሮች ከስልጣን ተነሱ፣ አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄና የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር የሕዝቡን የለውጥ ፍላጎት ተግባራዊ የማያደርግ የተናጠል ድርድር እንዳማይቀበሉ ገለጹ፣ዶ/ር አረጋዊ በርሄ፣ጋዜጠኛ አብርሃ በላይን ጨምሮ የትግራይ ብሄር ተወላጅ ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች የሕወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ወርዶ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ጠየቁ፣የሕወሓት/ ኢህአዲግ አገዛዝ ሁለት የአሜሪካ ዘጋቢዎችን ጨምሮ ሶስት የውጪ ሚዲያ ጋዜጠኞችን ሰሞኑን አሰረ ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ  ነሐሴ 8 ቀን 2008 ፕሮግራም

< …እነሱ እሳትና ጭድ የሚሉት ለዓመታት እርስ በእርሱ አደባድበው ስልጣናቸው ላይ ለመቆየት የወጠኑት ሴራ ከሽፎ ዛሬ ጎንደር ላይ ባህር ዳር ላይና ደብረ ማርቆስ ላይ በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ የሚፈጸመውን ግፍ እንቃወማለን ብሎ የአማራ ሕዝብ መነሳቱ በኦሮሚያም በተደረገው ተቃውሞ ላይ አማራ ወገናችን ነው ማለቱ እንቅልፍ ነስቷቸዋል ።የተባበረ ትግላችን ይቀጥላል …> አቶ ሌንጮ ባቲ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ከፍተኛ አመራር ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጋር ድርጅታቸው ስላደረገው አብሮ የመታገል ስምምነት ተጠይቀው ከሰጡት ምላሽ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

<…ይሄ ለውጥ ለሁሉም የሚመጣ በዚያች አገር ላይ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲገነባ የምናደርገው ትግል ነው… የኦሮሞና የአማራ ሕዝብ መተባበር ስርዓቱን እንቅልፍ መንሳቱን እያየን ነው። ትብብሩና የጋራ ትግሉ ለሁሉም ነጻነት የሚያመጣ ነው…> አቶ ነአምን ዘለቀ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ከፍተና አመራር ከኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ጋር ድርጅታቸው ስላደረገው ስምምነት ከአቶ ሌንጮ ባቲ ጋር በጋራ ከሰጡት መግለጫ የተወሰደ(ቀሪውን ያዳምጡት)

<…ተቃዋሚዎች አሁን አጣዳፊ የሆኑትን እና ወደፊት ሊነሱ የሚገባቸውን ጉዳዮች በመለየት በጋራ መምከር መነጋገር አለባቸው…> አክቲቪስት ገረሱ ቱፋ በወቅታዊው ሁኔታ ላይ ለህብር ሬዲዮ ከአክቲቪስት መስፍን አማን ጋር ከሰጠው ቃለ መጠይቅ(ክፍል አንድ)

<…ተቃዋሚዎች በጋራ መነጋገር መጀመር አለባቸው። የተናጠል የድርድር ጥያቄ ራሳቸውን ለማዳከምና ስርዓቱ ዕድሜ እንዲገዛ የሚያደርግ በመሆኑ አማራጩ የሕዝቡን የለውጥ ጥያቄ የሚፈታ ሁሉን አቀፍ ድርድር ማድረግ እንዲደረግ መግፋት አለባቸው ሌላው ግን መረሳት የሌለበት…> አክቲቪስት መስፍን አማን በወቅታዊ ጉዳይ በጋራ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ቀሪውን ተከታተሉት)

<…ሕዝቡ እዛ አገር ላይ እየተባበረ ነው እኛ እዚህ በውጭ አገር ሕዝቡን መከተል አለብን። ኦሮሞና አማራ በጋራ መቆም አለብን። የሚደረገው ትግል የትኛውንም ብሄር የሚያገል አይደለም። ኦሮሞ አያገልም…> አቶ ንጉሴ ርቂቱ በቬጋስ የኦሮሞ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር በከተማው የሕወሃሀት ደጋፊዎች የጠሩት ስብሰባን ለመቃወም በወጡበት ወቅት ከሰጠን ማብራሪያ (ቀሪውን ያድምጡት)

<…በቬጋስ የምንገኝም ተቃዋሚዎች በጋራ ተባብረን ይሄ ስርዓት የሚፈጽመውን ግፍ መቃወምና ተባብረን መቆማችንን ማሳየት ጭምር አለብን …> አቶ እንዳልካቸው ካሳሁን በቬጋስ የጎንደር ሕብረት የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ኦገስት 24/2016 በቬጋስ ስለተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ከሰጠን ማብራሪያ(ቀሪውን ይከታተሉ)

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በብራዚሉ/ሪዮ ዲጄኔሮ ኦሎምፒክ ላይ ሰሞኑን ያሰመዘዘገቡት አሰገራሚ እና አሳፋሪ ገጠመኞች በአለማቀፋዊ የዜና አውታሮች እይታ (ልዩ ጥንቅር) ሌሌችም

ዜናዎቻችን

ኮ/ል ደመቀ ዘውዱን የሕዝብ አደራ አለብን ለሕወሓት አሳልፈን አንሰጥም ያሉ በጎንደር የብአዴን አመራሮች ከስልጣን ተነሱ

አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄና የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር የሕዝቡን የለውጥ ፍላጎት ተግባራዊ የማያደርግ የተናጠል ድርድር እንዳማይቀበሉ ገለጹ

የሕወሓት/ ኢህ አዲግ አገዛዝ 2 የአሜሪካ ዘጋቢዎችን ጨምሮ ሶስት የውጪ ሚዲያ ጋዜጠኞችን ሰሞኑን አሰረ

ዶ/ር አረጋዊ በርሄ፣ጋዜጠኛ አብርሃ በላይን ጨምሮ የትግራይ ብሄር ተወላጅ ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች የሕወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ወርዶ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ጠየቁ

ምዕራባዊያኖች ዜጎቹን በመግደል እና በማሸበር ላይ ለሚገኘው የሕወሓት/ኢህአዲግ መንግስት ጭካኔ ጆሮ ዳባ ልበስ በማለታቸው ተብጠለጠሉ

በእስራኤል ውስጥ አንድ ኢትዮጵያኖችን የሚያገል ዘረኛ ማስታወቂያ ታላቅ ቁጣ ቀሰቀሰ

የአሜሪካው እጩ ፕ/ት ዶናል ትራምፕ “ፕ/ት ባራክ ኦባማ አሸባሪው አይሲስን ፈጥረዋል”በማለታቸው ብርቱ ትችት ገጠማቸው

ስዊዘርላንድ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ድንበሯን አልፈው አንዳይሻገሩ አገደች

አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባውያን ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በሚል ብቻ ሕወሓት ኢህአዴግ በሕዝቡ ላይ የሚፈጽመውን ግፍ እያዩ እንዳላዩ መሆኑን እንዲያቆሙ ተጠየቀ

በሕቡ ስታገል ቆይቻለሁ ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሄራዊ ፓርቲ ተቃዋሚዎች በጋራ እንዲተባበሩ ጥሪ አቀርባለሁ አለ

ሰሞኑን በልብ ህመም ሞቱ የተባሉት የቀድሞው የደ/አፍሪካ ፕ/ት ታቦ ኢምቤኬ አ/አ ውስጥ በሽምግልና ላይ መሆናቸው ተገለጸ ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radioወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.