በጎንደር ለሦስተኛ ቀን ከቤት ያለመውጣት አድማ ዛሬም ቀጥሎ ከተማዋን ጭር አድርጓታል

ከወር በፊት በጎንደር ከተማ የጀመረው ተቃውሞ ሰሞኑን እየተረጋጋ መሆኑን የክልሉ መንግስት ገልጾ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ዛሬ ደግሞ መልኩን ቀይሯል፡፡ አሁን እየተከናወነ ስላለው ከተማ አቀፍ አድማ መንግስታዊ አካላት እስከአሁን ያሉት ነገር ባይኖርም ትናንትና የተጠራው ከቤት ያለመውጣት ተቃውሞ ሶስት ቀናትን የሚቆይ እንደሆነ በከተማዋ ውስጥ የተሰራጨው የአድማ ጥሪ ወረቀት ይገልጻል፡፡ ዛሬም ጎንደር ለሁለተኛ ቀን ጭር ብላ መዋሏን ምንጮቻችን ከስፍራው ገልጸዋል፡፡
የከተማዋ የንግድ ተቋማት ተዘግተዋል፡፡ በፒያሳም ሆነ በአራዳ የሚገኙ የንግድ ሱቆች ዝግ ሆነዋል፡፡ የመንግስት ሰራተኞችም ወደ ስራ ገበታቸው እንዳልገቡ ነው ከስፍራው ያገኘንው መረጃ የሚጠቁመው፡፡ በተለየ መልኩ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አድማውን መቀላቀላቸው ከተማዋን ጭር አድርጓታል፡፡


go 1 go2 go4 go6

13939608_10209957233958206_7978359749589309455_n