ኡሁሩ ኬንያታ ከኃይለማርያም ባዶ ቀረርቶ ይልቅ ሄግ መሄድ መርጧል

10665985_10202926014652251_1474682044495437513_nየአፍሪካ ህብረት ፕሬዘዳንት የነበሩት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ‹‹አይሲሲ የሚያገለግለው ነጮችን ነው፡፡አፍሪካዊያን የራሳቸውን ጉዳይ በራሳቸው የመዳኘት አቅም አላቸው፡፡ስለዚህ በአይሲሲ በኩል ለሚቀርብ ክስ እውቅና አንሰጥም ወዘተ፣….››በማለት የኡሁሩንና የምክትላቸውን በአይሲሲ መከሰስ መቃወማቸው ፣የኬንያው ፕሬዘዳንትም የቀረበባቸውን ክስ ውድቅ እንዲያደርጉና የአፍሪካ ህብረት አባላት ከጎናቸው እንዲቆሙ ካምፔይን እስከማድረግ መድረሳቸው አይዘነጋም፡፡
ኃይለማርያም በኬንያ 2007 ምርጫ ህይወታቸውን ስላጡ 1500 የሚልቁ ኬንያዊያን ዙሪያ ግን ምንም ለማለት አልወደዱም፡፡
ሄግ የሚገኘው አለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ኡሁሩ በአካል እንዲቀርቡ ላወጣው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ዛሬ ኡሁሩ ቀና ምላሽ በመስጠት ቃላቸውን አስደምጠዋል፡፡አሁሩ‹‹ክሱ የቀረበው በግል በእኔ ላይ በመሆኑ ክሱ ኬንያንም ሆነ አፍሪካዊያንን ክብር አይነካም››በማለት ተናግረዋል፡፡
አሁሩ የኃይለማርያምን ውትወታ ሳይሰሙ ፍርድ ቤት በመቅረብ ቢያንስ ለህግ ያላቸውን ታዛዥነት አሳይተዋል፡፡ሀይሌ ግን አልተሳካላቸውም
በነገራችን ላይ በ2005 የኢትዮጵያ ምርጫ እንዲሁ ብዙዎች በመለስ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ደረትና ግንባራቸውን በጥይት እየተመቱ ተገድለዋል ፣ምነዋ አይሲሲ የኛ ሰዎች ደም ሳይታየው ቀረ ?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.