ዐማራ ‹‹ዐማራ›› ነው፤ [ሙሉቀን ተስፋው]

Amhara - satenaw 2ሁሌም የሚገርመኝ ነገር አለ፤ እርሱም ወያኔዎች ችግር ሳይፈጥሩ ችግር ለመፍታት አለመቻላቸው ነው፡፡ ሃያ አምስት ዓመት ቀላል ጊዜ አይደለም፡፡ ይህን ያክል ጊዜ አገርን ያክል ነገር የመራ አገዛዝ አይደለም ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ተወልዶ ያደገ ሰው እንዲህ አያስብም፡፡ የወያኔዎች ችግር አፈታት ዘዴ በጣም ጥንታዊ እና ከዘመኑ አስተሳሰብ ጋር የማይሔድ (Classical) ነው፡፡ ለነገሩ ምን ያድርጉ? የወያኔ አመራሮች ያረገዙትን ተንኮል እንደያዙ አንድም ቀን እንኳን በአእምሮ ሳይጎለምሱ አርጅተዋል፤ ልጆቻቸው ደግሞ አገር ዘረፋ ላይ ናቸው፡፡ ኮንትሮባንዱን፣ ሕገ ወጥ የሰው ዝውውሩን፣ መጠጥና ድሪያውን፣ ማጭበርበሩን፣ በፎርጅድ ሰነድ ኮንትራክተር መሆኑን፣ … ሁሉንም ሕጋዊና ሕገ ወጥ የሆነውን ሁሉ ‹‹የባለ ጊዜ›› ልጆችና እቁባቶች በመቆጣጠር ላይ ስለተጠመዱ ከአሁኑ ወጣት የማሰብ አቅም ጋር የሚሔድ አመራር እንደሌላቸው ለማንም ስውር አይደለም፡፡

ይህን እንድጽፍ ያደረገኝ በዚህ ሳምንት የትግሬ ሕወሓት አባላትና ለእነርሱ ያደሩ ባንዶች የዐማራውን ሕዝብ ከብረት የጠነከረ አንድነት ለመረዳት ተስኗቸው ለመከፋፈል ሲሮጡ በማየቴ ነው፡፡ እንዴት ዐማራ ‹‹ዐማራ›› መሆኑን ማወቅ ተሳናቸው? ቢያንስ እንኳ በየቦታው እያፈናቀሉና እየገደሉ መሬታቸውን በኢንቨስትመንት ስም የሚቀበሉት የዐማራውን ሕዝብ ንብረት እንደሆነ መገንዘብ አልቻሉም? እንዲህ ያለ ‹‹የነፈዘ›› አስተሳሰብ በዚህ ዘመን መስማት ይደንቃል፡፡

ብቸና ላይ የተሰበሰቡ ዐማሮችን ‹‹እናንተ ስለ ጎንደር ምን አገባችሁ?›› አለ አሉ ዛሬ አንዱ የነፈዘ ወያኔ፡፡ ደሴና ወልድያ ላይ ደግሞ ‹‹ከጎንደርና ከጎጃም ጋር ስላላበራችሁ የጎንደርና የጎጃም ትህምከተኛ በንግድ ሊጎዳችሁ አሲሯል፤ ከመንግሥታችን ጎን በመቆም ሁሉንም ነገር እናስተካክላለን!›› ተባለልኝ አሉ፡፡ ጋይንት ደግሞ ‹‹ስለ ሰሜን ጎንደር እናንተ ምን ሆናችሁ ነው የምትታገሉት?››፤ አፈርተ ቢሶቹ የአርማጭሆን ዐማራ ‹‹ወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት ለእናንተ ምንድን ነው?›› አሉ፡፡ አንዳንድ ‹‹ጸሐፍት›› ነን ያሉ ትግሬዎች ደግሞ ‹‹የዐማራ ዋና ከተማ ጎንደር ወይም ደብረ ማርቆስ መሆን አለበት›› የሚል ትግል ተነስቷል እያሉ እንዳሳሰባቸው እየገለጹ ነው (ሃሃሃ)፤

ለነዚህ ሰዎች ይህን የዐማራ ተረት ላስታውሳቸው እፈልጋለሁ፤ ቀይ፣ ነጭና ጥቁር በሬዎች በአንድ ላይ ሲኖሩ ጅብ ነጣጥሎ ሊበላቸው ፈለገ፡፡ ቀዩንና ጥቁር በሬም አላቸው ‹‹እናንተን እኮ በጨለማ ምንም መለት አልችልም፤ የምመጣው ይህን ነጭ በሬ አይቼ ነው››፤ ሁለቱ የዋኆች ነጩን በሬ ከሕብረታቸው ነጠሉትና ብቻውን በጅብ ተበላ፡፡ አያ ጅቦ አሁን ድጋሚ ሔደና ጥቁሩን በሬ ‹‹አንተ ከጨለማ ጋር በምንም አትለየኝም ነበር፤ ግን ይሔ ጓደኛህ በቀላሉ እለየዋለሁ›› አለው፡፡ ሁለቱንም ነጣጥሎ በመጨረሻ በላቸው፡፡ ዐማራ ከእልፍ ዓመታት በፊት ይህን የተረተው ለእንዲህ ያሉ ነፈዝ ወያኔዎችና የወያኔ አሽከሮች ነው፡፡

ወያኔ ዐማራውን ‹ትምህምከተኛ ዐማራ›፣ ‹የሸዋ ዐማራ› … ወዘተ ማለት የለመደው አሁን አይደለም፤ ድሮም ግብሩ ይኼው ነው፡፡ የዐማራ ሕዝብ አንድነት ከአለሎ የጠነከረ እንደሆነማ እኮ ደጋግመው አይተውታል፡፡ ወሎ ምንድን ነው? ሸዋ ምንድን ነው? ጎንደር ምንድን ነው? ጎጃም ምንድን ነው? እያልን ብንጠይቅ መልሱ የቦታ ስም ነው የሚል ነው፡፡ ወያኔዎች የተጋድሏችን መጀመሪያ መሆኑን አላወቁም፤ ይህን መገንዘብም አይችሉም፡፡ ደጋግመን እንደገለጽነው የዐማራ ሕዝብ ትግል እኮ ገና ያንቀጠቅጣል፡፡ በጅምሩ ብርክ ውስጥ የገቡት ወያኔዎች ያኔ በመጨረሻው ጊዜ ምን ሊሆኑ ነው? ስል አዝንላቸዋለሁ፡፡

ይህን ዓይነቱን የትግል ማዘናጊያና አጀንዳ ማስቀየሪያ ጊዜ ያለፈበት መሆኑን አሁን አለመረዳት የወያኔዎችን ‹‹የአእምሮ ምጡቅነት›› ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረስ ያሳያል//
ለማንኛውም ግን ደጋግሜ ልንገራችሁ፤
ይህ ሁሉ የመጨረሻው መጀመሪያ ነው፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.