የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ሰራተኞች ጎንደርን እንዲያወግዙ ለማስገደድ የተጠራው ስብሰባ ተካሄደ [ቱባ]

በውጪ ሀገር የሚገኙ የቀድሞ የመስሪያ ቤቱን ባልደረቦች የግንቦት ሰባት አባላት ሲሉም ፈርጀዋል፡፡

ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር 2

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ሰራተኞች የህወኃት የበላይነት ይቁም በሚል የተነሳውን የጎንደርን አልፎም የአማራን ህዝብ ለማውገዝና ከሥርዓቱ ጎን መቆማቸውን ለማሳየት በሚኒስትር ዴኤታዋ በወይዘሮ ታደለች ዳለቾ የተጠራ ስብሰባ ተደርጎ ነበር፡፡ ወይዘሮ ታደለች ዳለቾ የአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የሀገር ሰው እና የእምነት አምሳያ በመሆናቸው ከአስራ አምስት ዓመት በላይ ያለ ለውጥ የኢትዮጵያን ቱሪዝም ሲመሩ የቆዩ ናቸው፡፡

የሚያቀነቅኑለት ሥርዓት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን የውሸትም ቢሆን ያጎናጸፋቸው ስልጣን ተጠቃሚ ያደረጋቸው ወይዘሮ ታደለች ዳለቾ ከዚህ በፊት አቶ ሙሐሙዳ ገአስን ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታነት አስባረው ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ያስደረጉ፡፡ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ኢሳት ላይ ጭምር ቀርበው ያጋለጡትን ሱማሌውን አቶ ዳውድን ያስባረሩ፤ በአቅም ማነስ ምክንያት ጠብ ውስጥ ሲገቡ ሚኒስትሩን አቶ አሚን አብዱልቃድርን ከሀገር ያስወጡና ከሚኒስትርነት አስነስተው ወደ አምባሳደርነት፣ ሚኒስትር ዴኤታውን አቶ ሙሉጌታ ሰይድን ከሚኒስትር ዴኤታነት ወደ አንድ ድርጅት ስራ አስኪያጅነት ያስፈነጠሩ ማን አለብኝ ባይ ሴት ናቸው፡፡

ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር - gonder

አሁን ደግሞ የጎንደርና የአማራ ህዝብ በህወኃት የበላይነት ላይ ያወጀው የበቃን አብዮት ጥቅማቸውን የሚነካ በመሆኑ ይህንን እንዲያወግዙ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ሰራተኞች ሰብስበው ሲደሰኩሩ ውለዋል፡፡ አንዳንድ ሆዳም አማሮችም ቢሆን ሰላም ይሻለናል በሚል ስብከት ወገናቸውን ሲኮንኑ የዋሉበት ስብሰባ ነበር፡፡ የባህልና ቱሪዝም መስሪያ ቤት በህወኃት የበላይነት እየታመሰ እንኳን ሀገሪቷን መታደግ ያልፈለጉ ለሆዳቸው ያደሩ አማራ ነን ባዮች አብረው አላዝነዋል፡፡ እውነታው ግን፡-

  1. ወይዘሮ ማዓዛ ገብረ መድህን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የዋግና የትግራይ ዘር ያላቸው የእነ አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን ቡድንና እነ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን የሚሰልሉ የህወኃት ሰላይ፤
  2. አቶ ሰለሞን ታደሰ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አሜሪካን ሀገር የታክሲ ሹፌር የነበሩ የህወኃት አባል፤
  3. አቶ ጀማል- የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የህወኃት አባል በአክሱምና በላሊበላ የአለም ባንክ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ ብዙ ገንዘብ የዘረፉ፤ ለማረጋገጥም ወደ አክሱምና ላሊበላ መደወል እና አንዱን ነዋሪ ማነጋገር በቂ ነው፡፡
  4. አቶ ዩናስ ደስታ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር፤ የህወኃት አባል ቀድሞ በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተራ የቆዳ ባለሙያ የነበሩ በድንገት ተነስተው የሀገሪቱ ቅርስ ልማት ላይ የተሾሙ፤
  5. አቶ ሃብተ ስላሴ ኪዳኔ የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ማዕከል ምክትል ዋና ዳይሬክተር፤ የህወኃት አባል፤
  6. አቶ ሃይላይ-የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን የአጠቃቀም ዳይሮክተሬት ዳይሬክተርና የህወኃት አባል እንዲሁም የስሜን ፓርክን ለአንዲት የህወኃት አባል ሸጠው ደባርቅ ህዝብ ህዝባዊ አመጽ በማኬድ እንዲቆም ያደረጉ፤
  7. አቶ ካህሳይ-የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን እንዴት በኦሮሞ ይመራል በሚል ህወኃቶችን የሚያሳምጹ ብዙ ገንዘብ በሚገኝበት የጥናትና ምርምር ዳይሮክተሬት በሃላፊነት የተመደቡ አምባገነን፤ እነዚህ ከብዙ በጥቂቱ የሀገሪቱ የቱሪዝም እና ባህል ዘርፍ ላይ ብርቱ ክንዳቸውን እያሳረፉ ያሉ የህወኃት ጋሻ ጃግሬዎች ናቸው፡፡