መቀሌ ውስጥ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ የሆኑ 650 የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች በትግራይ ገዥ እየሰለጠኑ ነው

መቀሌ ውስጥ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ የሆኑ 650 የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች በትግራይ ገዥ እየሰለጠኑ መሆኑ ስናውቅ የሌላው ዞን ተመራቂ ሣይጠራ ወልቃይቴ ብቻ መሆኑ አላማው ምን እንደሆነ ብናውቅም “ካሁን በኋላ ወደ ወልቃይት ጠገዴ እንደ ክኒን civil cervant ከትግራይ አይላክልንም ማለት ነው?” ብለው የጠየቁ የዋሃን ነበሩ ። ተሣስተዋል ። ተማሪዎቹ በ8/12/08ዓ/ም እሁድ እለት መቀሌ እንደ ገቡ ፦

  1. የመቀሌ አስተዳድር በእንኳን ደህና መጣችሁ ዝግጅት የብሉልኝ ጠጡልኝ ግብዣ እንዳደረገ
  2. የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ዓድ ሓቂ ግቢ አንድ ትልቅ ህንፃ ለምኝታቸው እንደሰጠና ቁርስና ምሳ ስልጠናቼው እስኪ ጨርሱ ለ10 ቀናት እየቻለ እንደሆነ
  3. በ16 ቡድን እያንዳንዱ ቡድን 40 ሠውና ከዛ በላይ ከፋፍለው ማታ ግቢ ውስጥ በውይይት ፣ ቀን ሓወልት አዳራሽ በጋራ እንደሚነዘንዟቸውና ከከተማ ሠው ጋር እንዳይገናኙ እረፍት እንደሚነሷቸው
  4. ለስራ ስልጠና ብለው ጠርተው የህወአት ፖለቲካዊ ታሪክና ከዘመነ ጃንሆይ እስከ ዘመነ ኢህአዴግ ዶክሜንታሪ ፊልም እንደ ሰጧቸው ስናውቅ  የወልቃይት ጠገዴ እንቅስቃሴ ለማዳከም መሆኑ የበለጠ እርግጠኛ እንድንሆን ያደርገናል ።

ተማሪዎች እንድታውቁልኝ የምፈልገው ቢኖር እኛ የወልቃይት ጠገዴ ልጆች ከህወአትና ቡድኑ በቀር ሌላ ጠላት እንደለለን ነው ! ።e1

e2

ገብርየ ገብርየ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.