ዜና ወሎ (ቆቦ)

የራያ ጀግና
የራያ ጀግና

ራያ ቆቦ ሚሊሻዎች እንዲለብሱ የተደረገውን የፌደራል ልብስ አውልቀው በ1000 ብር አበል መሸኘታቸውን ተከትሎ ተቃውሞዋቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ
በያሬድ አማረ

ባለፈው እሁድ ሊደረግ የታሰበውና በከፍተኛ የመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ሀይል ሚዛን እንዳይካሄድ የተደረገውን ህዝባዊ ንቅናቄ እና ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ የሚገኙ የሚሊሻ አባላትን ለአስቸኩዋይ ስብሰባና ስልጠና ትፈለጋላችሁ በሚል ጥሪ እንደደረሳቸው እና በጥሪው መሰረት በቦታው ቢገኙም የፌደራል ፖሊስ ልብስ ታድሎዋቸው ከፌደራል ከመጡ ፖሊሶች ጋር በማሰባጠር በጥበቃ ስራ ላይ ተመድበው ቢቆዩም የፌደራል ፖሊሶቹ ወደመጡበት መመለስን ተከትሎ ሚሊሻዎቹ የተሰጣቸውን የፌደራል ፖሊስ ልብስ እንዲያሰረክቡ እና በጥበቃ ስራ ላይ ለቆዩባቸው ቅናት ለእያነዳነዳቸው የ1000 ብር የውሎ አበል እንዲውስዱ በመታዘዛቸው በሚሊሻዎችና በባለስልጣናት መካከል ከፍተኛ አለመግባባት መፈጠረን እና ሚሊሻዎቹ ባለስልጣናቱን “ባልገባን አላማ አሰማርታችሁን ከህዝባችን ነጠላችሁን ይሄ ሳያንስ የተሰጠንን የደንብ ልብስ እንድናወልቅ መደረጋችን ለኛ ያለችሁን ክብር እንድናውቅ አድርጋችሁናል ። እስከመጨረሻ እንፋረዳችሁዋለን” ማለታቸውን ስሙ እንዳይገለፅ የፈለገ የሚሊሻ አባል ገልፆልናል።

እንደመረጃ ምንጫችን ገለጻ ሚሊሻዎችን ለስብሰባ ትፈለጋላችሁ በሚል ጥሪውን ያስተላለፈው አበራ ያዩ የሚባል ሚሊሻ እንደነበርና በስልክ ከፍተኛ ዘለፋና ዛቻዎች እየደረሱበት በመሆኑ የተደወለለትን ቁጥሮች በመያዝ፣ ከባለስልጣናት ጋር በመሆን ከቴሌ የቁጥሮቹን ባለቤት ስም ዝርዝር ለማግኘት ጥረት እያደረጉ መሆኑንም አያይዞ ገልፆዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.