የወያኔ መንግስት ስንብት አይቀሬ ነው። ከአለም አቀፍ የአገሮች ሁኔታና ፖለቲካዊ አቁዋም ትንተና ሪፖርት [ በዘርይሁን ሹመቴ]

ፖለቲካዊ አቁዋም ትንተና ሪፖርት STRATFOR Global Intelligence

በዘርይሁን ሹመቴ/ከጀርመን

https://www.stratfor.com/analysis/muffled-insurrection-ethiopia

Woyane
የኢትዮጵያ ህዝብ  በገዢው መንግስት (ወያኔ) ላይ  እያሳየ ያለውን  የእምቢተኝነት ተቋውሞ እና መንግስት ባልታጠቁ  ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እየወሰደ ያለው  ወታደራዊ  እርምጃ ለተለያዩ አለም አቀፍ ኩባንያዎች  የአገራትን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ መልክአ ምድራዊ እና ወቅታዊ ሁኔታ  ስልታዊ ትንተና እንዲሁም ትንበያ የሚያቀርቡ ድርጅቶች ትኩረት ውስጥ ገብቷል። ተቀማጭነቱን በአሜሪካ ኦስቲን ቴክሳስ ያደረገው  ስታርትፎር ግሎባል ኢንተለጀንስ (STRATFOR Global Intelligence) ከ175 አገራት በላይ ውስጥ የሚንቀሳቀስ  ፖለቲካዊ አላማ  የሌለው ስለ ተለያዩ አገራት ተአማኝነት ያላቸውን መረጃዎች ስልታዊ ትንተናዎች እና ትንበያዎች ለደንበኞች (አለም አቀፍ ግዙፍ ኩባንያዎች ድርጅቶች ሚዲያዎች ወዘተ) በመስጠት የሚታወቅ  ስመ ጥር አለም አቀፍ የአማካሪ ድርጅት ነው። ስታርትፎር ግሎባል ኢንተለጀንስ (STRATFOR Global Intelligence) በቀን13 ነሃሴ 2008 ዓም  (19 Aug 2016) በአለም ለሚገኙ አንባቢያኖቹ  ባወጣው  ሪፖርት  በሃይለማሪያም  ቁንጮነት  የሚመራው  የወያኔ መንግስት በህዝብ  አመጽ  አጣብቂኝ  ውስጥ  እንደገባ  “A Muffled Insurrection in Ethiopia” (የታፈነው አመጽ በኢትዮጵያ)   በሚል ርእስ አቅርቧል። በዚህም ሪፖርት መሰረት ደንበኞቹ  በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት ወይም ሊያደርጉ  ለሚችሉት  ለማንኛውም  አይነት የንግድ  የማህበራዊ  የጥናት ወይም  የግል ጉዳዮቻቸው  የሚሆን  መረጃን  ትንታኔን እንዲሁም  ትንበያን ለማካተት  ችሏል።

 

ይህ አለም አቀፍ ድርጅት በሃይለማሪያም ደሳለኝ የሚመራው  ወያኔ  በተለያዩ የኢትዮጵያ  ክፍሎች  የተቀጣጠለውን  የህዝብን ተቋውሞ ለማብረድ  የወሰዳቸውን የግድያ እስራትና ድብደባ አጸፋዊ እርምጃ በአለም አነጋጋሪ ከሚባሉት  ርእሰ አንቀጾች ውስጥ መመደቡ እንዲሁም  ገዢው  ፓርቲ የፈጸመው  ኢሰብአዊ ተግባራት  ከአጋሮቹ ከምእራባውያን ቢረፍድም እንኩዋን ትችት ላይ የጣለው እንደነበረ ጠቅሷል። “Ethiopia’s government, led by Prime Minister Hailemariam Desalegn, has contended with protests for nearly a year. The government’s efforts to quell the unrest have made headlines and drawn international criticism of late, but its problems go well beyond humanitarian concerns.” (በሃይለማርያም ደሳለኝ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት አመት ሊያስቆጥር በተቃረበ  የህዝብ ተቋውሞ ተወጥራል። ይህን አለመረጋጋት ለማስከን እየወሰደ ያለው ርምጃ የአለም የመነጋገሪያ ርእስ ከመሆኑም በላይ ለትችትም ዳርጎታል)። ከ1970 እአ አጋማሽ  ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የአመጽ ጊዚያት መሪን ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ርዮቱን  እንዲሁም የመንግስት መዋቅሮችን መቀየር እንደቻሉ፤ በአሁኑ በተቀሰቀሰው ቀውስ የሃይለማርያም አስተዳደር  ከፍተኛ ፈተና በፊቱ እንደተደቀነበት አትቷል። “Since the mid-1970s, Ethiopia underwent several periods of upheaval that changed not just the leaders of the country but also the political system and institutions that govern it. Now, with ethnic discontent reaching a new high and the tendrils of insurgency starting to re-emerge, Desalegn’s administration faces the greatest challenge to its rule yet. “

 

የህዝብ አመጹ በአገሪቷ ሁለት ትላልቅ ብሄሮች በሆኑት የኦሮሞና  የአማራ ህዝቦች እርስበእርስ በመተደጋገፍ እየተደረገ መሆኑ ወደ ፖለቲካ እኩልነት እንዲሁም የትግራይ የበላይነትን ወደ ሚያስቆም ጎዳና አገሪቷን ሊመራት እንደሚችልም  ይህ ሪፖርት ጠቁሟል። “in recent weeks, the Amhara people — another large ethnic group, accounting for 29 percent of the population — joined in, and the focus of the protests shifted to demands for political equality and an end to the Tigray-dominated ruling coalition’s reign.”

 

የመንግስት ታጣቂዎች በንጹሃን ሰልፈኞች ላይ ባዘነበቡት ጥይት በ2 ቀናት ብቻ (በ30ሐምሌ 2008ዓም እና በ1 ነሐሴ 2008ዓም) ከ 100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን በዚሀ ሪፖርት ተካቷል። እንደውም  ከሆስፒታል የሚወጡ  መረጃዎችን  እንደ  ምንጭ በመጥቀስ  በመንግስት ሃይሎች  በአሰቃቂ ሁኔታ  የተገደሉት  ቁጥር  ወደ 200 እንደደረሰ በዚህ ሪፖርት ሰፍሯል። የፕሬስ ነጻነት በወያኔ አገዛዝ እንደ ሃጢያት እንደሚቆጠርም  ስታርትፎር ግሎባል ኢንተለጀንስ (STRATFOR Global Intelligence) ለአንባቢያን በግልጽ አስፍሯል።

 

“Facing mounting dissent from two of the country’s largest ethnic groups, the government has attempted to suppress the unrest through force. During the weekend of Aug. 7, reports emerged that over 100 civilians had been killed in protests, which led to outcry over the Ethiopian security services’ brutal methods to control the demonstrations. Because the Ethiopian government exercises strict control over media activity in the country and restricts internet access, reports of what exactly happened are slow to emerge. But information from local hospitals suggests that another 100 civilians have been killed since that weekend; at least 55 of these deaths have been confirmed.” (በሁለቱ ታላላቅ የአገሪቷ  ብሄሮች  የተወጠረው የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን ተቋውሞ በሃይል ለመቆጣጠር ሞክራል። በነሃሴ ወር  የመጀመሪያ የሰንበት ቀናት ውስጥ ከ100 በላይ ንጹሃን  ጭካኔ በተሞላበት መንገድ በመንግስት የጸጥታ  ሃይሎች መገደላቸውን የሚወጡ ሪፖርቶች ይፋ አውጥተዋል። መንግስት በሚዲያ እና በኢንተርኔት ከፍተኛ አፈና ወይም ቁጥጥር ስለሚያደርግ በትክክል የተፈጸሙ  ድርጊቶች ሪፖርት እጅግ አዝጋሚ ነው። ከክልል ሆስፒታሎች በሚወጡ መረጃዎች መሰረት በተጨማሪ ሌላ 100 ንጹሃን ሰዎች ከነሃሴ 1 በኋላ ባሉት ቀናት ውስጥ ተገድለዋል፤ በትንሹ  የ55 ስቱን ማረጋገጥ ተችሏል።)

 

ህዝቡ የጀመረውን  የእምቢተኝነት  ትግሉን ቅርጹን  በመቀየር ተቋውሞውን እንደቀጠለ ይህ ድርጅት ባጠናከረው ሪፖርት እንዲህ አድርጎ አስፍሮታል።  “Since the bloody Aug. 7 weekend, protesters in some areas have turned to less violent forms of civil disobedience. For instance, in the Amhara city of Gondar — once the capital of an ancient Ethiopian empire — civilians have gone on a general strike, turning the city into a ghost town despite calls from the government to resume business as usual. Some reports even claim that local militia or rebel groups near Gondar have attacked convoys and bases belonging to the security forces.”  (ንጹሃን ሰላማዊ ሰልፈኞችን ከቀጠፈው ከነሃሴው የሳምንት ማገባደጃ ጀምሮ  ተቋሚዎች  የህይወት መጥፋትን የሚቀንስ ሌላ የትግል ዘዴ በአንዳንድ  ቦታዎች ተግባራዊ  እያደረጉ  ያገኛሉ። ለምሳሌ በታሪካዊዋ የቀድሞ የኢትዮጵያ የመንግስት መቀመጫ በሆነችው ጎንደር ከተማ ነዋሪዎቹ  ተቋውሟቸውን  የስራና የመንቀሳቀስ አድማ  በማድረግ  የመንግስትን ጥሪ ችላ  በማለት ገልጸዋል። አንዳንድ  ሪፖርቶች   ስርአቱን  በመቃወም  የትጥቅ  ትግል  የሚያደርጉ በጎንደር አቅሪያቢያ በሚገኝ በመንግስት የጦር ሰፈር ላይ እና  በአንድ  የጦር  መኪና ላይ ጥቃት እንዳደረሱ ያመለክታሉ።)

 

ባሳለፍነው  ሳምንት የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄና  የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግምባር በጋራ በመስራትና በመታገል የገዢውን መንግስት የ25 አመታት ጉዞ ለማስቆም  ስምምነት ላይ መድረሳቸውና  በይፋ  ማሳወቃቸው  በርግጥም  ለሃይለማርያም መንግስት የእንቅርት ላይ  ጆሮ ደግፍ እየሆነበት መሆኑንም  ስታርትፎር ግሎባል ኢንተለጀንስ (STRATFOR Global Intelligence) ሳይገልጽ አላለፈም። “In the past week, two rebel groups announced their alliance. If these groups increase their attacks, or if other groups join the movement opposing the government, the current administration could face a similar fate to the one it brought upon its predecessors.” (ባሳለፍነው ሳምንት  2 ነጻ አውጪ  ቡድኖች ጥምረታቸውን  ይፋ አድረገውል። እነዚህ  ቡድኖች  ትግላቸውን  ካጠናከሩት ወይም ሌሎች ተመሳሳይ ቡድኖች ይህን  መንግስትን  የመቋወም  እንቅስቃሴን ከተቀላቀሉዋቸው አሁን ያለው መንግስት ከዚህ ቀደም  እንደነበረው ተመሳሳይ እጣፋንታ ይጠብቀዋል።)

By Zerihun Shumete/ From Germany

ምንጭ/ Source

https://www.stratfor.com/analysis/muffled-insurrection-ethiopia

https://www.washingtonpost.com/news/monkey-cage/wp/2016/08/05/heres-the-novel-yes-fiction-to-read-to-better-understand-ethiopia/

https://www.hrw.org/news/2016/08/18/ethiopias-bloody-crackdown-case-international-justice