ለ3 ቀን የታወጀው ከቤት ውስጥ መቀመጥ ዛሬ በ3ኛ ቀኑ ባህር ዳርን ይህንን አስመስሏታል

Bahir Dar 56 -satenawበባህር ዳር ለሶስተኛ ቀን የሥራ ማቆም አድማ ዛሬም በተሳካ ሁኔታ ቀጥሎ ዉሏል። በተመሳሳይ ሁኔታ በደንቢያ ወረዳ እና በአለፋ ጣቁሳ ስር ባሉ ቀበሌዎች የተጠራዉም የሥራ ማቆም አድማ ቀጥሏል። በቆላ ድባ፣ ጯሂትና ጎርጎራም እንደዚሁ የሥራ ማቆም አድማ በተጠናከረ መልኩ ቀጥሏል፡

ዛሬ በደባርቅ የስራ ማቆም አድማ ተጀምሯል። በታጣቂዎችና በህዝብ መካከል በተፈጠረ ግጭት ጉዳት ደርሷል። ከነገ ነሐሴ 19 2008 ዓ.ም ጀመሮ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የሥራ ማቆም አድማ በጎንደር ከተማን በአምባጊዮርጊስ ከተማ ተጠርቷል።

በጎንደር እና በጎጃም ሕዝባዊ ተቃዉሞ ከመቼዉም ጊዜ በላይ በተቀናጀና በተጠናከረ መልኩ እየተደረገ ሲሆን በወሎና በሸዋም ድርጅታዊ ስራዎችም እየተሰሩ ነው

ባህር_ዳር‬

ከ140 ሺህ በላይ ጎብኝ (ከ70 ሺህ በላይ የውጭ ዜጎች) እርሷንና አካባቢውን ይጎበኘዋል
300 ሚሊዮን ብር ገደማ ከቱሪዝም ገቢ አስገኝታለች።የአለም ምርጥ ከተሞች ዝርዝር ውስጥ የምትመደበዋ ውቢቱ ባህር ዳር ላለፊት ሳምንታት ሀዘን ላይ ነች።ብዙ እንቁ ልጆቿን ደም በተጠሙ አይናዋጃሞች ተነጥቃለች።

ሀዘኗም መሪር ነው።የአማራ ተጋድሎን ምንነት ፍንትው አድርጋ የነገረችን ባህር ዳር ዛሬ በአደባባዮቿና በተንጣለለው የእግረኛ መንገዶቿ እንዲሁም በተሽከርካሪ መንገድ ባጃጅ፣ ብስክሌት፣ታክሲ….በእግራቸው ጥንድ ጥንድ ሁነው የሚንሸራሸሩ ነዋሪዎች እና ጎብኝዎች አይታዩም።

14095913_1225955730769840_8641792884456565925_n

demma2

 

dema3

14046040_1225955734103173_3009765556753566663_n

124

123

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.