ሰበር ዜና – ጎንደር እና ጎጃም ህዝባዊ እምቢተኝነቱን አጠናክሮ ተጋድሎውን ቀጥሏል

 

በአማራ ክልል የወያኔ አገዛዝ መሰረቱ እየተናደ ነው፥ 1ለ5 የጠረነፈበት መዋቅር ፈርሷል።
================================================
የአማራ ህዝብ የጎበዝ አለቃውን እየመረጠ መንግሥታዊ ተቋማትን እየተረከበ ነው፥ ፀጥታ የማስከበር ስራና ህዝብ ለማረጋጋት ጉዳይ ቅድሚያ ሰጥቶ በአደባባይ እየመከረ ይገኛል።
በዚህ በዱር ቤቴ ጀግኖች ቪዲዮ ላይ የሚታየው አሰራር በመላው አማራ ግዛት እየተሰራበት ያለ ሞዴል ነው።
ከሰሜን ጎንደር ወልቃይት ቀፍቲያ ጀምሮ፤ ዳባርቅ፣ አምባጊዮርጊስና ዳባት፤ ዓርማጭሆ መተማ፣ ቋራና በለሳ ደርሶ፤ መላውን ጎጃም ተሻግሮ እስከ ሰሜን ሸዋ አንፆኪያ ማጀቴ ወረዳ ድረስ ህዝብ በፍላጎቱ የሚያደርገው ጊዜያዊ የመተዳደሪያ ስርአት ሆኗል።
ደቡብ ጎንደር ከደብረታቦርና ጋይንት ጀምሮ ፣ ከቆላድባ ሀሙሲት እስከ ጎጃምም ቋሪት፣ ፍኖተሰላም እና አገው ምድር ድረስ ብዙ ከወያኔ ነፃ የወጡ ወረዳዎች እየሄዱበት ያለ የሰለጠነ አሰራርና በጊዜያዊ የጎበዝ አለቃ መመራት አስደናቂ ነገር ነው።
በጎጃም እንጅባራ፡ ዱር ቤቴ ዳንግላ፡ ኮሶበር ህዝቡ በአድማና በአደባባይ ተቃውሞ ለህወሀት መንግስት መልዕክት አስተላልፏል ”ከእንግዲህ የራሳችንን አስተዳዳሪ መርጠናል። ህወሀት አይገዛንም።”
ምዕራብ ጎንደር አርባያ በለሳ፥ ሰሜን ጎንደር አርማጭሆ እስከ ወገራ፥ ደቡብ ጎንደር ደብረታቦር፣ ጋይንት፣ ወረታና አዲስ ዘመን ንቅናቄው ተቀጣጥሏል።
ትግሉ ይቀጥላል፥ ሞት ለወያኔ ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ ፦
ሰበር ዜና – ጎንደር እና ጎጃም ህዝባዊ እምቢተኝነቱን አጠናክሮ ተጋድሎውን ቀጥሏል

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.