የአማራ“ “ተጋድሎ” እና የኢህአዲግ “ጥልቅ ተሃድሶ “ ?

7D3DE368-1143-40F7-8ECB-F7274CDA1202_w987_r1_sአማራን ከጥፋት ማዳን ፣ ወልቃይት ፣ፀገዴና ፀለምቲ እንዲሁም ከእንዳመኾኒ ጀምሮ ራያ ዓዘቦ አማራ ነው በሚል በወያኔና ተጋሩን የወያኔ ደጋፊ በማለት የጅምላ ጭፍጨፋ በማካሄድ በታሪካዊትዋ ጎንደር የተጀመረው ጉድ ውደ ጎጃም ተሸጋግሮ ጉደኛው የጅምላ ጭፍጨፋ በተቃወሙ አማሮችም በተመሳሳይ ሲፈፀምና ወሎና ሰሜን ሽዋም ተመሳሳይ ጉድ ባለመፈፀም አተወቀሱና ተደጋጋሚ ጥሪ እየቀረበላቸው መሆኑን እያስተዋልን ነው። የጅምላ ጭፍጭፋው የተቃወሙ አማሮች ለወያኔ ያደሩ ሆዳሞች በሚል ንፁሃን ተጋሩም የውያኔ ሰላዮች በሚል በግልፅ ነፃ እርምጃ የታወጀ አሸባሪነት እያየን ነው።

የአማራ ክልል ከሌላው በተለየ የሕልውና አደጋ ተጋርጦበታልን ? እውን የትግራይ ህዝብ የአማራ ሕዝብ አደጋ ነው ? የወልቃይት ጉዳይ የአማራ ቀዳሚ ጥያቄ መሆን ይችላል? የአማራ ተጋድሎ የአማራ ሕዝብ ጥያቄ ተብሎ ሊወሰድ ይቻላል ? የአማራ ተጋድሎ የተባለው ሰላማዊነትና ዲሞክራሲያዊነትስ ምን ይመስላል? ተቃውሞውስ ከጅምሩ ሰላማዊ ነበር ? ሳምንት ባልሞላ ከሰላማዊ ስም ወደ ተጋድሎ የመቀየሩ ጉዳይስ ? ተቃውሞ በአማራ ተጋድሎ ሽፋን የውጭ ሃይሎች ጣልቃ ገብነትስ ? የቋንቋ ልዩነት የዘር ልዩነት ተደርጎ በተለይ በትግርኛ ተናጋሪው ያነጣጠረ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተብሎ ሊገልፅ የሚችል ውንብድና ሲፈፅም የክልሉ መንግስቱ ማስቆም ካልቻለ የፌደራል መንግስት ሃላፊነት ምን መሆን አለበት ? የአማራ ተጋድሎ ከኢህአዴግ የትሻለ አማራጭ አለው? መደገፍና መነቀፍ ያለበት ተቃውሞ እንዴት ያሉ መሆን አለባቸው? የአማራ ተጋድሎ ከኢትዮጵያ አንድነትና ደህንነት ሲቃኝስ ? የአማራ ተጋድሎ ተወሰዱ ከሚላችው የጎንደርና የጎጃም ….. መሬቶች የሚቆም ይመስላል? ካልሆነስ ….. ጣጣው ??? የአማራ ተጋድሎ አማራን መጥቀም ወይስ አማራን ማጥፋት ?

የኢህአዲግ ጥልቅ ተሃድሶም ከ”የአማራው ተጋድሎ” በተጓዳኝ መደመጡ እንድምታው ምንድነው ? የተሃድሶው ጥልቀትስ እስከምን ድረስ ነው ? ኢህአዲግ የ1993 ተሃድሶ ጥልቅ አልነበረም እያለን ይሆን ? የኣአሁኑ ተሃድሶ ጥልቀትስ እስከምን ድረስ ነው ፣ አሁን ሀገሪቷ ከተደቀነባት ችግር የሚያወጣ ተሃድሶ ይዞአል ኢህአዲግ ? የኢህአዲግ ስራ አስፈፃሚና ምክር ቤት ውሳኔ ከመንግስት ውሳኔና ከ ገዢ የፓርቲ ተግባርና የመንግስት ተግባር ሲቃኝስ ?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.