ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ [ግርማ ሠይፉ ማሩ]

ግርማ ሠይፉ ማሩ
ግርማ ሠይፉ ማሩ

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ከዛሬ ጀምሮ ለሚጠፋው የሰው ሕይወትና ንብረት ሃላፊነቱን ለመውሰድ የሚያስችል ትዕዛዝ መስጠትዎን ነግረውናል፡፡ ለነገሩ የያዙት ቦታ ከተጠያቂነት የሚያስመልጥ አይደለም፡፡ ለማነኛውም እስከዛሬ በአልሞ ተኳሽ ግንባርና ደረታችውን እየተባሉ ለተቀጠፉት ዜጎች ሃላፊነቱን ማንም ሊወስደው አይችልም፡፡ ክልሎች ቢሆኑ እንኳን ይህን ማሰቆም ይጠበቅቦታል፡፡ እኔ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የምመክሮ እዚህም እዚያም የሚነሱ ጥያቄዎቹን መለስን በማለት፣ ወይም ደግሞ አግልግሎታቸውን የጨረሱ ሹሞቹን ከፊት አንሰቶ ጓሮ በአማካሪነት ሰም በማስቀመጥ መልስ አይገኝም፡፡ ጥያቄው የነፃነት ነው እና ነፃነታችንን የሚያፍኑ ህጎችን አንሱልን፡፡ ለተፈጠረው ችግር የጋራ መፍትሔ እንፈልግ ለሚለው የመፍትሔ ሃሣብ ጆሮ ይስጡ፡፡ እደግመዋለሁ – በጋራ መፍትሔ እንፈልግ ለሚለው ጥሪ ጆሮ ይስጡ ….


ሁሉም እንደሚያውቀው ክልሎች የፖሊስ ሰራዊት የማደራጀት ስልጣን አላቸው፡፡ ነገር ግን ሁሉም ክልሎች ልዩ ሀይል በማድረጃት ዜጎችን እያፈኑ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ልዩ ሀይሎች በጦር ሠራዊት ደረጃ ተደራጅተው ይገኛሉ፡፡ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አስፈላጊ ከሆነ ድጋፍ እሰጣለሁ ማለቱ አይዘነጋም፡፡ ክብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ብዙ ልማታዊ መንግሰት ችግር ይገጥመዋል፡፡ ደቡብ ኮሪያ ተመሳሳይ ችግር ገጥሟቸው ነበር፡፡ መፍትሔ ያመጡት ግን የጦር ስራዊት እንዲገል ትዕዛዝ በመስጠት አይደለም፡፡ መፍትሔው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በእስር ላይ ያሉትን ዜጎች መፍታት፣ የፖለቲካ ምዕዳሩን ነፃ ማድረግ፣ ሚዲያ እና ሲቪል ሶሳይቲ የሚጠበቅባቸውን ተግባር እንዲወጡ ማድረግ፣ ሞተው ቀባሪ ያጡ ተቋማትን (ለምሳሌ ምርጫ ቦርድን የመሰሉ) መዝጋትና ለህሊናቸው የሚገዙ ሃላፊዎችን መመደብ፡፡ የዚህን ዝርዝር በዚህ አጭር ፅሁፍ ማስቀመጥ አይቻልም፡፡ ወዳጄ ስዮም ከወሊሶ ከኮሪያ ልምድ በጥናት ላይ መስረት አድርጎ አስቀምጦሎታል፡፡ እባክዎትን ያድምጡን፡፡


ክቡር ጠቅላይ ሚኒስት አንድ እውነት ግን ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያዊነት በአሽዋ ላይ የተሰራ ማንነት አይደለም፡፡ ኢህአዴግ ሲወድቅ አትፈርስም፡፡ ካድሬዎቹ ግን ይህን አጉልተው እየነገሩን ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ ደግሞ የከፋው የፓርቲዎ ቀንደኛ መሪ የሆነው የህወሃት ደጋፊዎች የትግራይን ህዝብ ስብዓዊ ጋሻ ለማድረግ የሚያደርጉትን ጥረት እንዲያቆሙ ያድርጉልን፡፡ እስከ ዛሬ የተዘራው የልዮነት መስመር ቆሞ አንድነታችን ይሰበክ፡፡ አንድነታችን – ኢትዮጵያዊነታችን ሲሰበክ በምንም ምክንያት እርሶ ወላይታ መሆኖ ፣ እኔ ኦሮሞ መሆኔ እነ ሃጎስም ትግሬ መሆናቸው ጋር አይጋጭም፡፡ ይህን ጉዳይ አሰፋ ጫቦ ጋሞነቴ ከኢትዮጵያዊነቴ ጋር ተጋጭቶ ለማስታረቅ ሞክሬ አላውቅም ያለውን ያስታውሳል፡፡


ክቡርነትዎ ስብሰባው ይህን ያህል ረጅም ጊዜ ተቀምጦ ይህን ውጤት ለህዝብ ለመንገር ከሆነ አይመጥነንም፣ ለፀጥታ ሀይል ትዕዛዝ በመስጠት ከህዝብ አመፅ የሚዳን ቢሆን ጋዳፊ፣ ሙባረክ፣ ሳዳም ሁሴን፣ ወዘተ ይተርፉ ነበር፡፡


ከማክበር ሠላምታ ጋር
ግርማ ሠይፉ ማሩ

Comments are closed.