አጫጭር አስታያየት ፣ ይደረስ ለኢህአደግ  ፓርቲና መንግስት [ከአስገደ ገብረስላሴ መቀለ]

Asgede
ከአስገደ ገብረስላሴ መቀለ ።

27 /12 /  2008 ዓ ም መቀለ

ስንት ጊዜ መታደስ ? መንን ነውስ የሚታደስ?
ይህ ገዥ ፓርት 25 አመት ሙሉ በውስጣዊ ብለሽት በሙሱና ፣
በወገናወነት በኪራይ ሰብሳቢነት ፣በጸረዲሞክራሳዊነት  ከጭንቅላቱ
እስከ እግሩ  ተባላሽተናል በማለት ምክንያት በመፍጠር ፣ብልሽውነቱ
በከፍተኛና መካከለኛ አማራር እያሉና  በታችኞው ደረጃ ላሉ አካላትና በህዝብም
ስለታም ጫፍ  ነቃፊ ሆነው የተገኙ አርሶ አደሮችና የከተማ ነዋሪ ፣የመንግስት
ሰራተኞች፣ ወደ ከፍተኛ መሪዎች አታንጠራራ ራስ ፈትሽ እየተባሉ ስህቶቶችን በጊዜው እንዳያስተካክሉ  ተቀጥቅጠው ከስራ የተባረሩ የታሰሩ ሞራላቸው የተነካ ሆነዋል
እንደማይነሱ ተደርገዋል ።ህዝቡን ከቀጠቀጡ በኃላ አንገቱ ደፍቶ ለጊዜው
ዝም ብሎ ቢቆይም ፣ የመንግስት ባለስልጣናት ከህዝብ ትክሻ ተጭነው የሀገራችን ሀብት
መሬት፣የንግድ ተቋማት ተቆጣጥረው እንደፈለጉ ጨፍረዋል ።
እነዚህ አንባገኖኖች ረጅም ሳይጓዙ በሰበሰን በውስጣችን ቦኖ ፓርቲዝም ተፈጥረዋል
ከውስጣችን እንታደስ አለን በማለት የታሀድሶ መድረክ በሚል ለዋናው ወራሪ ቡዱን
በመቃወም አቋም ለያዙና ለወደፊትም አንጻራችን ይሆናሉ ለሚሉዋቸው
መነጠሩዋቸው ።ከ10አመት በላይ በውሼት ተሀድሶ ሁሉም ክልሎች ተናጡ
ለውጥ ግን አልመጣም ። በአንጻሩ ድህነት ተንሰራፋ ።
በኃላ  የኢህአደግ በለስልጣናትና ዘርመንዘራቸው እንዲሁም ሽሪኮቻቸው ለ15
አመት ያህል ያለአንዳች ተቃውሞ ሀገራችን በዘቦዛት ፣ተዝናኑባት፣ በሁሉም ክልሎች
እነሱን የሚቃወሙ ወይ ራሳቸው ያቀኑ ተቀጠቀጡ ።
መላው ህዝባችን ወደ ድህነት አረንቋ ገባ ተሰደደ በስደትም ተሳቃዬ ተገደለ እንደ ባሪያ
ተሸጠ ፣በሳሀራ ታረደ ። ለዚሁ ሁሉ ግፍ መፍትሄ ለመፈላለግ የተነሱ ሰለማዊ ፓለቲካ ሃይሎች
ታሰሩ ፣የግል ሚድያዎች ደብዛቸው ጠፉ ፣አሳታሚዎችም ታሰሩ፣በቃ ኢትየጱያ የዜጎቻ ወህን ቤት
ሆነች ።ህዝቦች መፋናፈኛ አጡ ። ባለስልጣናትና አጋሮቻቸው የዝች ድሀ ሀገር ንጉሶች ሆኑ ።
ግን ህዝብ ሀያልነውና አሁንም ሲመረው ሲመረው ተነሳና በሁሉም አቅጣጫ ተነሳባቸው ።
አሁንም እንደልማዳቸው ሀይለማርያም ደሳለኝ ራሳቸው የህዝብ እሳት ሲያቃጥላቸው ሳይወዱ በግድ ።
አሁን ላለው ብልሽት ተጠያቂዎች ኢህአደግና አጋር ፓርቲዎች እንዲሁ  እነሱ የሚመሩት መንግስት
ነውተጠያቂ ወደ ማንም አናስጠጋውም፣ በመሆኑም ከላይ እስከታች ያለ አመራር እናጠራለን በመለት በምዲያ ተናዘዙ ።በተግባር ግን
ውሀ ቢወግጡት እቡጭ ሆነ ።እንዳው ካለፉት አመታት በባሰ በሰበሱ ። ህዝብም አወቃቸው ጠላቶቹ
ገዥዎችና መዋቅራቸው መሆናቸው አወቀ ።የሚያነሳቸው ጥያቄዎች መላሽ እንደሌለ ተረዳ ።

በመሆኑም በኦሮም፣ በጋንቤላ ፣በኮንሶ ፣በአፋር ፣በቅማንት ፣በወልቃይት በነበለት  የማንነት
ጥያቄ ተነሳ ፣በሁሉም ክልሎች እስከጎጥ ሳይቀር ፣የመልካም አስተዳደር ፣የፍትህ ፤የዲሞክራሲና
የናጽነት  ጉዳይ የ90 ሚሊዬን ህዝብ ጥያቄ ሆነ ።ይህ ስርአት በፈጠረው ብሶት የኦሮሞ ህዝብ አመጸ ።
ለዘጠኝ ወር ያህል ስርአቱም አርበደበደ ።ብዙ ወገኖች አለቁ ታሰሩ የጠፉም ያሉበት ቦታም ታጣ  ።
በቅርብ ጊዜ ደግሞ በወልቃይት የማንነት ጥያቄ  መነሻ በማድረግ አማራ አቀፍ ተቃውሞ ተቀጣጠለ ።ይህ ተቃውሞ መነሻው የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ብቻ አይደለም ። ዋናና አንኳር ምክንያት በሀገራችን ያለው ችግር ቢሄር ሀይማኖት ፣ክልል ወዘተ ሳይለይ የከፋ ችግር ስላለ ነው። በሌላ በኩል የሁለም ጠንቅ የሆኑት የኢህአደግ አባል በርቲዎች የፈጠሩት  ዜጎችን ወደ ግጭት የሚመራ ሴራ ነው ።ስለዚህ በዘመነ ኢህአደግ ስርአት ፣የዜጎች ሀሳብና ነጻነት መከበር የሚባል አልነበረም  ።በሬድዮ በተለብዥን ፣በራሱ ጋዜጣ ፣በየመንደሩ ያሉ ኤፍ ኤም በወሸት የልማት ፣ የእድገት ዳታ በመደናገር ለመላው ህዝብ የውሼት ምግብ መግበውታል ።
ከራሳችን በላይ ለህዝብ ከሚል መንፈስ በጥልቀት መታደስ አለብን ፣
ጠቅላይ ምኔስቴር ሀይለማርያም ደሳለኝ ፣
ጠ/ ም ሀይለማርያ አመት መሉ የህዝብ ጥያቄ እንዳይመልሱ ጆሮ ደባ ብለው ከርመው የከፋና የተባላሽ
ቆይተው ስርአታቸው የፈጠረው ህዝባዊ የተቃውሞ ማእበል ካርበደበዳቸው በኃላ የኢህአደግ  ስራስፈጻሚና ምክር ቤት ግምገማ ውጤት ሲነግሩን  የመንግስት ሰልጣን ተጠቅመው ከሸሪኮቻቸው ጋር ሆነው የመንግስት ስልጣናቸው ተጠቅመው ቡዙ ሽግር በመፍጠራቸው ስርአታችን አደጋ ላይ ነው ።በመሆኑም ስርአታችን ለመታደግ በመጭው ጥቅምት ወር መጀመሪያ የመዋቅር ለውጥ ፣ሪፎርም እናደርጋለን ብለውናል ።
እኔ እሚገርመኝ አቶ መለስ በተዳጋጋሚ ተናግሯል  ።ውጤቱ አላየንም ። ባዶ ሆኖ አልፋል። እኒህ  ሰውዬም ለጋሲው እየተከተሉ ነው ።ታድያ የዚህስርአት ቡልሽውነት ከቁንጮዎች እስከቀበሌ ፣ቤተሰብ  ፣ትጃሮች በመተሳሰርና በመሻረክ የሀገራችን ወሳኝ ሀብትና መወቅር በቁጥጥራቸው ነው  ስለሆነ ይህ  የተጠናከረ ሀይል ሆነዋል እና ፣ጓድ ሀይለማርያም እንዴት ብለው ሊያስተካክሉት ነው ። በእኔ እምነት  ፈጽሞ አይቻልም እንዴት ሲጨኩኑ ነው  ባለስልጣኖች በአንገታቸው ገመድ እሚያስገቡ?
በበኩሌ ዛሬ ዛሬ እንኳን እጠራጠራለሁ ፣በመሰረቱ ግን በፓርቲዎና መንግስትዎ ያለው መጨማለቅ ፍርጥርጥ አድርገው ያለመሸማቀቅ ማውጣት ምንም እንኳን በተግባር ባዶ ቢሆን ንግግርዎ ለሁሉ ሰው ይመቸዋል ። በመለስ ጊዜ ሁሉም ነገር የሚነገር በኳልኩለሽን ነበር ።
ስለዚህእርሶ በሚያስቡት በመዋቅር ወይ  ሪፎርም በማድረግ ስርአትዎ አይስተካከልም ።ኦሮሟይ ።አብቅቷል ።መፍትሄው ከበሰበሱ መዋቅሮ መጨቃጨቅ ትርጉም የለውም መፍትሄው የሚገኜው ከህብረተሰቡ ካሉት ሊሂቃን መላው የህብረተሰብ ክፍል መመካከር ያሻል ።ካለበለዚያ ከራስህ በላይ ለህዝብ ብለህ በጥልቀት መታደስ የሚል ቦታ የለውም ።እንታደስ ስትሉስ ስንት ጊዜ ነው የምትታደሱት ?
ተሀድሶስ ምንድነው ?ማንም ሰው ታሀድሶ ሲባል እች አገር ከሁሉ መጥፎ ነገር የፀዳች ሁሉም ዜጎች በእኩልነት ተከባብረውና ተፋቅረው የሚኖሩባት ፣የሀገራችን ሀብት እኩል ተጠቃሚነት ኑሯቸው ነጻ ሆነው የሚንቀሳቀሱባት አገር ስትኖር ነው ። አሁን ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ግን እች ሀገር ለገዥዎችና መዋቅራቸው ገነት ለ90ሚሊዮን ህዝቦቻ ሲኦል ወይ ኩርችት ወይ አቃቅማ ሆናችባቸው አለች ።
የወልቃይትየማንነት ጥያቄየተዋሳሰበ ያደረጉት የአመራና የትጎራይ ክልሎች መሪዎች ናቸው ።
                ጠ/ም /ሀይለማርያም ደሳለኝ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
የተከበሩ ምኔስቴር የተባላሹ የትግራይና የአማራ ክልሎች አማራር ብቻ ናቸው ብለዋል ?የኦሮሞስ?የደቡብ አማራርስ ? አጋሮቹስ ? በኔ እምነት ከሆነ የኢህአደግ ስርአት ከራሱ እስከ እግሩ ጋንግሪን ቦልቶቷል ።በመሆኑ ይህ ስርአት ከእንግዲህ ወዲህ ተጠግኖ ስለማይጠገን ስልጣኑ ለህዝብ ቢያስረክብ ይሻለዋል ።
ለመሆኑ በኦሮሞ ከ600 በላይ ያለቀው አካሉ የጎደለው ቡዙ ነው ይህ አሀዝ ባለፉት አመታት የጠፉ ወገኖች አይጨምርም ።በጋንቤላ ፣በቅማንት በዶቡብ በአፋር ያለቀው ህዝብ ተጠያቂ ማነው ? ስለዚህ 25 አመት በህዝባችን የደረሰው በደል የኢህአደግ የሚባል መንግስት ገዥ የፈጸመው ስህተት ነው ተጠያቂም እሱ ነው ።
ኢህአደግ ተጠያቂ ነው ስል ግን ለሁለቱ ክልሎች ነጻ በማድረግ አይደለም ።እንዳውም እነዚህ የሁለቱ ክልል መሪዎች እኔም በቅርብ ተግባራቸው እማወቀው በለፈው ወራትም ለህዝብና ለስርአቱ እየነገርነው እንደከረምን ፣አሁን ወደዘረኝነት ደረጃ አሻጋግረውት ያሉ የአማራና የትግራይ ህዝብ ያቃቃረ ፈጣሪዎቹ አባይ ወልዱና ገዱ አንዳርጋቸው ከነመዋቅራቸው ናቸው ።ይህ ማለት ግን ሀይለማርያም ደሳለኝ ፣የእርሶ አማካሪዎችም ኒስትሮች ፣ፓርላማ ፣ፈደረሽን ምክርቤት አያውቁም ነበረ ማለት አይደለም   አበጥረው ያውቃሉ ። ምክንያቱም የወልቃይት የማንነት ጥያቄ  ለ20  አመት ያህል አየተንከባለለ  የኖረ ነው ። ። ጥያቄው በትግራይ ክልል አስተዳዳሪዎች ታፍነው የነረው ሲሆን  ፣በአማራ ክልል አማራርም ዘርፈ ቡዙ ሴራ ይሰራ ነበር ።በመሰረቱ የሀገራችን ህገመንግስት የዜጎች የራስህን እድል በራስህ መወሰን የሚለው ሸአብያን ለመገንጠልና ሉኡላዊ ሀገራችን ለመድፈር ታሳቢ ያደረገ ነበር ያጸደቀው ።ሀግ መሆኑ መራጋገጫ በትግራይ በአፋር ሽከት በአማራ አፋር በባቲ በኦሮሞ ቡዙ ቦታዎች ፣በደቡብ እንደ ኮንሶና ሌሎች ጥያቄዎች በተመለሱ ነበር ። ስለዚህ ይህ ሰርአት የዜገች ጥያቄ ባጸደቀው ህገመንግስትም እንኳን አልሰራበትም ።
የነውጡ ጠንቅ የውጭ ሀይሎች ጣልቃ ገብነትና ተላላኪዎቻቸው ሴራ ነው ።
…………………………………………………………………………………………………..
ጠ/ምንስቴሩ በኦሮሞ በአማራ ያለው ብጥብጥ የጥንት ጠላቶቻችን ለማታችን ለመደናቀፍ በጆኖያ ብር እየተቀበሉ በተላላኪዎቻቸው አድርገው ነው ሀገራችን እንድትተራመስ እያደርጉ ያሉ ብለዋል ፣
በእኔ እምነት በሀገር ውስጥ የተሟላ ዲሞክራሲ ነጻነት ቢኖር ንሮ ፣ሀብታችን በባለስልጣናትና ሸሪኮቻቸው እጅ ባይወድቅ ንሮ ።ግልጽነትና ተጠያቂነት የህግ በላይነት ቢረጋገጥ ንሮ ፣ስራ ፈጣሪ ልማት ቢኖር ንሮ ፣ፍትሀዊ የሀብት ተጠቃሚነት ቢኖር ፣ስርአቱ ለዘር ልዩነትና የከፋፍለህ ግዛ ስርአቱ ለመራዘም ተንኮል በመፍጠር ግጭቶቹን ባያቃጣጥል ንሮ ፣ የዜጎች ጥያቄ በተገቢና በወቅቱ ቢመልሷቸው ንሮ፣ የህዝቦች አንድነት እንዲኖር ታክቶ ቢሰራ ንሮ ፣ አሁን ተፈጥሮ ያለው ብጥብጥ አይፈጠርም ነበር ።እነዚህና ሌሎች ከተማሉ  ህዝብ ከረካ የውጭ ሀይሎች በየተኛው መስኮት ይገባሉ ምክንያቱም ህዝቡ ተጠቃሚ ከሆነ ጥቅሙ አሳልፎ አይሰጥምና ።ይህቺ የህዝብ ጥቅም ኢህአደግ አበጥሮ ያውቃል ።17 አመት ሲታገል ህዝቡ ከታጠቀ ሰራዊት ፊት ተወርዋሪሆኖ ከደርግ ሰርጎ ገቦች ዘበኛ ሆኖ ይጠብቀው ነበር ስለዚህ የኢትየጱያህዝብ ለባእዳን አይቀበልም ።እንዳውም የውጭ ሀይል መጣብህ ሲባል ታሪካችን እንደሚነግረን በውስጡ ያለው ሉዩነት ወደጎን በመተው ቆፈው እንደተሰበረ ንብ ፈርሶ ነው ጠላቱን ለማጥቃት የሚዘምተው ።
በሌላ በኩሉ የውጭ ሀይሎች  ጥገኛ የሆኑ ሚዲያዎች የሻአብያ ጥገኛች በአማራና ትግራይ ህዝቦች በገዥዎች የተፈጠረው ቅራኔ ተጠቅመው  የሚነዙት ያሉ የዘረኝነት መርዝ አሁንም በገዥ ፓርት አባል ፓርቲዎችፍግ ወይ መዳበሪያ ስላገኙ ነው ።ይህ ደግሞ የኢህአደግ ወስጣዊ ሁኔታ በመባላሸቱ ነወ
በሌላ በኩል ሁሉም ኢትዮጱያዊ አውቆ መኮነን ያለበት በውጭ ያሉ የተለብዥንና የረድዮ ጣብያ  ባለንብረቶች  ለ5000000 የትግራይ ህዝብ  በመላው የኢትዮጱያ መሬት ወይገጽ እየተለቀመ እንዲጠፋ እያሉ የሚነዙት መርዝ  እጅጉን አሳፋሪና ምን ያህል ቅጥሮኞች  መሆናቸው ያራጋግጣል ።እነዚህ ሰዎች የተግራይ ህዝብ ከገጽ መሬት አጥፍተው የትግራይ መሬት ለማን ሊሰጡት ነው ።ነገደሞ ኦሮሞ ይጥፋ ፣ከነገ ወዲያ ደቡብ ወይ ሌላ ቢሄርም ይጥፋ ይሉን ይሆናል ።ለመሆኑ እነዚህ የሚድያ በለንብረቶች ኢትዮጱያውያን ናቸው ወይ ?አእሙሯቸውስ ይሰራል ወይ ?በእኔ እምነት  እነዚህ ሰዎች ለውጥ ፈላጊዎች ከሆኑ አገሪቱ በዘረኝነት ከተላለቀች ስልጣን ይዘው ማንን ሊያስተዳድሩ ነው ።በመሆኑ መኮነን አለባቸው።
፣በህዝባችንና በሀገራችን መካከል ገብቶ አይጫወትብንም ነበር ። በመሆኑም አሁን በኦሮሞና በአማራ ጠፈጥሮ ያለው እልቂት አንባገነኑ የኢህአደግ ስርአት ።ብቻነው ተጠያቂ ።
   የዘረኝነት ጠንቅ ገዥዎች እንጅ በህዝቦች መካከል የዘር ልዩነት ቦታ የለውም ፣
……………………………………………………………………. ………………………………
ዘረኝነት በሀገራችን ትርጉም የሌለው መሆኑ ለማስረጃነት ያህል ፣በትግል ወቅት ኢህደንና ህወሀት አብረው ይታገሉ ነበር በዛን ጊዜ ህወሀት ወደማኸል አገር ሲንቀሳቀስ  የድሮ ኢህደን ፣የዛሬ በአዴን አብረው ነበሩ  በወቅቱ ህወሀት ግዙፍ ሀይል ነበረው ኢህደን ግን በመቶ የሚቆጠር ሰራዊት ነው የነበረው ። በዛን ጊዜ ከሰሜን ጎንደር ደባርቅ አውራጃ ወረዳዎች ፣ከአገው ወግና ላስታ ፣ከጸገዴ አርማጭሆ ራያ ቆቦ ፣ወጣቶች ወደ ትግል ሜዳ ሲመጡ  ።ኢህደን የአማራ ድርጅት ስለሆነ ወደ አማራው እንሰለፍ አላሉም  ከ99% በላይ ወደ ትግራዋይ ድርጅት ህወሀት ነበር የተሰለፉ ፣የደርግ ሙርከኛ ወታደሮችም ከሁሉም ቢሄሮች ለማለት ይቻላል  ወትግራዋይ ፓርቲ ነበር የሚሰለፉ ።
ሀወሐትና ኢህደን ወደማኸል ሀገር ሰሜን ወሎ ፣ሰሜንሽዋ ፣የገንደር አካባቢ ቀበሌዎች ፣ጋይንት ፣ንፋስ መውጫ ፣ድብረታቦር ፣ፈርጣ ፣በለሳ ፣አባይ አቋርጠው ከጎጃም ይመጡ የነበሩ በአስር ሽ የሚቆጠሩ ወጣቶች ኢህደን እየተው ወደ ህወሀት ነበር የሚሰለፉ ። የገጠር ምልሻዎችም ከህወሀት ጋር ነው ሊታጠቁ የሚፈልጉ የነበሩ ።
ይህየሚያሳው በህዝቦች መካከል የዘር የቢሄር የሀይማኖት ልዩነት እንደሌለነው የምንገነዘበው  ።
ያሁሉ ወጣት በህወሐት ወታደራዊ ማሰልጠኞ ሲገቡ ኢህደን ለማሳደግ ወደ ኢህደን ሰራዊት ሂዱ ተብለው ሲለመኑ የሚሄዱ አልነበሩም  ።በመሆኑም ህዝብ ዘረኛ አይደለም ።ዘረኝነት የሚቀሰቅሱ የብዝበዛ ስርአታቸው  አንደመጠናከርያ ከፋፍለው ዜጎች እርስ በእርሳቸው በማጣረስ እድሚያቸው ለማራዘም የሚጠቀሙበት ስልት ነው ።
አሁን በአገራችን ያለው የዘር ግጭትም  የድሮ ገዥዎች ያሳለፉበት ተጽእኖ ቢኖርም የአሁኑ ችግር ፈጣሪና አስፋፊ ኢህአደግ ነው ። ምክንያቱም መጀመሪያ ትክክል ያልሆነ የፈደራሊዝምን አወቃቀር የፈጠረው ነው ።የዚሁ ወጤት ደግሞ በመላው ሀገራችን ያለው የቢሄር የቋንቋ ግጭት  ቡዙ ሂወት አልፋል ንብረት ወድሟል ።በተለይ ደግሞ በአማራና በትግራይ ተፈጥሮ ያለው ፣አማራ ትግራይ የሚል ልዩነት ተፈጥሮ ለረጅም ጊዜ አብሮ የኖረ ፣በጋብቻ ፣በንግድ ፣በማህበረ  ኢኮኖሚ የተሳሰረ ህዝብ በአዴንና ህወሀት በፈጠሩት መቃቃርና መናናቅ ፣ ህዝቡ ለየግላቸው ለድጋፍ ሊጠቀሙበት ብለው የሚያጫሩሱት ያሉ ነው ።ይህ ህዝብ ከጥንት ጀምሮ በክፉና በበጎ አበሮ እተሳሰበ የመጣ በሀገር ሉአላውነት ወራሪዎች ለመከላከልና ለማጥቃት አብሮ በአንዶ መቃብር እየተቀበረ  የኖረ ነው ።

በአራት ወረዳ የወልቃይት የማንነት ጥያቄ  በቀላሉ ሊፈታ እየተቻለ አማራ አቀፍ ጸረ ትግራይ ቢሄር ሊነሳ አይችልም ።ይህ የሆነበት ምክንያት በውስጡ የፓርቲዎች አመራርና ተላላኪ ከድሬዎች የፈጠሩት ቅስቀሳ ነው ።ይህ ደግሞ ትልቅ  ወንጀል መሆኑ ያመለክታል ።
እጅጉን አዛኝ የሆነው ደግሞ በገጃም በጎንደር የተፈጠረው ጸረትግራዋይነት የዘር እንቅስቃሴ  ስንመለከት በጎጃም በገንደር ያሉ ሙሁራኖች ያገር ሽማግሌዎች ፣የሀይማኖት መሪዎች ፣ተማሪዎች ፣ማህበራት  የተደረገው ጸረትግራያዊነት  ዘረኝነት ለመቃወም በቻሉ ነበር ። ግን አለደረጉትም ።ለምን ትላንት ጸረ የአገር ውስጥና የውጭ ወራሪዎች አብሮ የተከላከለ የተሰዋ ዛሬ በገዥዎችና ጸንፈኞች ተገፋፍቶ ወንድም ለወንደም መፋጀቱ ምን አመጣው ?  አሁንም የኢትየጱያ ህዝብ በተለይ ደግሞ የአማራና የትግራይ ህዝብ ሁኔታውን ማገቻ ማድረግ አለበት ።

ኢህአደግ አማራርም ከ1985 ጀምሮ በህወሀትና በአዴን በነበረው የመሬት ቅርምት ፣በጊዜው ግጭቱ ባለመፍታታቸው  ።እንሆ ዛሬ ለጥቅማቸው ሲሉ ወደ ህዝብ እንዲስፋፋ  በማድረጋቸው የዘረኝነት እሳት አቃጣጥለውታል  ።ይህ አደጋ በአስቸካይ ህዝብ ባሳተፈ መንገድ ካልፈቱት እች አገራችን አደጋ ለይ እየወደቀች መሆኑ መገንዘብ አለባቸው የሁለቱ ህዝብም የዘረኝነቱ አሳት ለማጥፈት መዝመት አለበት።ከህወሐትና በአዴን አመራር ፍትህ መጠበቅ የለበትም ።እነዚህ አማራሮች የውስጣቸው ችግር ለህዝበ የደበቁት አላቸውና ።

ሁሉም የሀገራችን የጸጥታ ሀይሎች እርምጃ እንዲወስዱ አዝዤለሁ!!!!! 
         ጠ/ ምኒስቴር ሀይለማርያም ደሳለኝ   
…………………………….  ……………….
ወታደራዊ አዋጁ ለማን?አስከአሁን ባልታጠቀ ሰላማዊ ህዝብ ላይ ወታደራዊ አዋጅ ሲያውጁ አላየንም  ።
ጠ/ሚኒስቴሩ የህዝቦችጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ፣ከሁለም የህብረተሰብ ክፍል ተመካክረው ግጭቱ እንደማርገብ  100%ተመረጥኩ ለሚለው የራሳቸው ፓርለማ እንኳን አቅርበው ሳያስወስኑ በአማራና በኦሮሞ ወታደራዊ ፍርድ እንዲፈረድባቸው ፣አንባገነናዊ የሆነ ወታደራዊ አዋጅ ትእዛዝ ማወጃቸው ፣የኢትዮጱያ ህዝቦች ሀገራችን ፣ከደርግ ፋሽሽታዊ ስርአት የተሻለ ዲሞክራሲ ነጻነት የህግበለይነት ልማት ያለው ስርአት እየተመኙ በሞቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ልጆቹ ለመስዋእት የዳረገ ዲምክራሲያዊ ሰርአት ለማንገስ ነበር አሁንከ25 አመት በኃላ ፈሸሰታዊ ስርአት ማገርሼቱ አጅጉን ያሳዝናል ።
በተጨማሪ ሀገራችን በሻአበያና በሌሎች የባእድ ሀይሎች ዳርደንበሯና ሉኧሏውነታ በወታደራዊ ዘመቻ ስትደፈርና በትግራይ በጋንቤላ በሽዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎችተገድለዋል ።ታፍሰው ተወስደዋል  ።ተገድለዋል ብዙ ሀብት ተዘርፈዋል ወድመዋል ቡዙ የጸጥታ ሀይሎች  የመካላከያ ሰራዊት ሳይቀር አየተገደሉ ነው መንግስት ግን  መስታገሻ ፣ተመጣጣኝ እርምጃ እንወስዳለን በማለት ሲለማመጡ ፣በያልታጠቀ ህዝብ ላይ ቀጭን አገር አቀፍ ወታደራዊ አዋጅ ማወጃቸው ደግሜ እቃወማለሁ ።
በአማራ ያለው የዘረኝነት ማእበል ንቃተህሊናቸው ዝቅ ያሉ አርሶ አደሮችና ፣ወጣቶች ድሩዮዎች እየነዱ በተለይ ለ5 ሚሊዮን የትግራይ ቢሄር ህዝቦች ያናጣጠረ የዘር አጥፋ መርዛቸው በተለያዩ ቅጥረኛ ሚዲያዎችና በህዝቡ ወስጥ የተሰገሰጉ ቅጥረኛ ታጣቂዎች በመነጠል በፓሊስ ፣በምልሻ ፣አስፈላጊ ከሆነ ደግሞ በፈደራል ፖሊስ ጸጥታ ማስከበርና መረጋጋት እየተቻለ በሀገሪቱ ሁሉም አቀፍ የጸጥታ ሀይሎች አስፈላጊ እርምጃ እንዲወስዱ  ምኔስቴሩ በግብታውነት ማወጃቸው ትልቅ ውድቀት ነው ።በተጨማሪ ይሀ ስርአት ወታደራዊ አዋጅ በማወጁ የደርግ ፋሽሽታዊ ወታደራዊ አዋጅ መድገመቸው  ትልቅ ወድቀት ነው ።
ይህ አዋጅ ወደ ወታደራዊ አገዛዝ እንዳይሸጋገር መላው የኢትየጱያ ህዝበች ከወዲሁ በአትኩሮ መከታተል (መጠበቅ) አለበት ።
ሌላ የኢህደግ ስርአት ሀቀኛ ከሆነ አሁን ያለው የዘረኝነት እልቂትና የሀብት ውድመት ዋና መንስኤ ምንድነው ? ከጅምሩ ጠንሳሾች እነማን ነበሩ ? በየተኛው የስልጣን እርከን ያሉ ናቸው ? ጨክኖ እርምጃ መውሰድ አለበት ።
ለዛሬ እዚህ ይብቃኝ ፣
ከአስገደ ገብረስላሴ መቀለ ።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.