የትግራዩ ክልል ፕሬዚዳንት አባይ ወልዱ የሕወሓት ደጋፊ አማራውን ለመጨፍጨፍ በተጠንቀቅ እንዲቆም አዘዘ [ከአቻምየለህ ታምሩ]

Abay Weldu - satenaw news 6አባይ ወልዱ የሰው ተፈጥሮ ከሌላቸው ጨካኝ የወያኔ አውሬዎች አንዱ ነው። አባይ ወልዱ የኤርትራ አምባሳደር የነበረውንና ከነስዬና ተወልደ ጋር ከወያኔ የተባረረውን ወንድሙን አዋሎም ወልዱን ሊገድል ብዙ ጊዜ ሞክሯል።

አባይ ወልዱና አዋሎም ወልዱ በረሃ እያሉ ተኽሉ ወልዱ የሚባል የደርግ ባለስልጣን የነበረ ወንድማቸው አዲስ አበባ ውስጥ ይኖር ነበር። የተኽሉ ወልዱ ቤት በአዲስ አበባ የወያኔ ጽህፈት ቤት ነበር። ደርግ «ሞኙ» ከነተኽሉ ወልዱ ጋር አዲስ አበባ ውስጥ ስለ ወንበዴዎች ሲወያይ ይውል የነበረው ነገር ሁሉ አንድም ሳይቀር በበነጋታው ወያኔ እጅ ይገባ እንደነበር አያውቅም ነበር። ከነ ጭራሹም ደርግ ተኽሉ ወልዱ አባይና አዋሎም ወልዱ የሚባሉ ወንድሞች እንዳሉት አያውቅም ነበር። የተኽሉ ወልዱ ቤት ግን ከትግራይ በረሀ የገጠር ልብስ ለብሰው ወደ አዲስ አበባ የሚገተሙ የወያኔ ታጋዮች ምሽግ ነበር።

አባይ ወልዱ የ«ባዶ ስድሽተ» ወይንም «ዜሮ ስድስት» ማለት ኮድ ስድስት የሚባለው የትግሉ ጠባቂ ወይንም የእስር ቤት ሀላፊ ሳለ በርካታ የወልቃይት አማሮችን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል። ለነገሩ ለወንድሙ ያልተመለሰው ጨካኝ አውሬ ለሚጠላው አማራ ይመለሳል ተብሎ አይጠበቅም። ይህ የሰው ተፈጥሮ የሌለው ጨካኝ አውሬ ባለፈው እንዲህ ሲል ለትግራይ ወጣቶች ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር፤
«በእናቶቾቻችሁ፣ በአባቶቻችሁ፣ በእህት፣ ወንድሞቻችሁ ደምና አጥንት ማንነታቸሁ ተከብሯል። ደርግ ወንበዴ እያለ ሲጨፈጭፈን መስዋዕትነት ከፍለን በሰላም የምትኖሩበት፥ የምትማሩበት፣ የምትሰሩበት እና በክብር ወጥታችሁ የምትገቡበት ናጽነት አግኝተናል። አሁን ግን የጥፋት ኃይሎች በሻእቢያ እና ግብጽ በመታገዝ ደርግን መልሰው ሊያመጡብን ትግራዋይ ላይ ግልጽ ጦርነት አውጀዋል። ስለዚህ ይህን የመመከት ኃላፊነት በእናንተ ወጣቶች ላይ ተጥሏል። ወላጆቻችሁ ትምክህተኞችን ጠባቦችን ደምስሰው በኢትዮጵያ ሰላም ልማት እና ዲሞክራሲ አንዳሰፈኑት ሁሉ እናንተም አኩሪውን ታሪክ የመድገም ግዴታ አለባችሁ። አለበለዚያ የተጋሩ ህልውና አደጋ ላይ ይወድቃል ብሎም ከላይ የሻእቢያ ከታች የትምክህተኞች ጥቃት መፈንጫ ሆኖ እንደ ሕዝብ የመቀጠል እድል የማይታሰብ ይሆናል። በተለይ በ አሁኑ ሰዓት በአማራ ክልል ሁከት በተጋሩ ላይ የተፈጸመው ጥቃት ይህንኑ ያመላክታል። ይህን አውቃችሁ ህወሓትንም ትግራይንም ከጥፋት በማዳን የተጋሩን ቀጣይነት አረጋገጡ። ባለራዕዩ መሪያችን መለስ ዜናዊ የጣለብንን አደራ እንወጣ::በእናንተ ፍጹም እምነት አለን።

ይህ የአባይ ወልዱ መልዕክት ከአርባ አንድ አመታት በፊት ወያኔዎች፤
«ገረብ ገረብ ትግራይ፣
መቃብር አምሃራይ!»
«ጎበዝ ተኻወት ተጋዳላይ ትግራይ፤
አርኪብካ በሎ ንዚ-ሃሻ አምሃራይ!»

በማለት የትግራይን ወጣቶች ከቀሰቀሱበት ዘፈን ጋር አንድ አይነት። አባይ ወልዱ ዛሬም የትግራይን ተራሮች የአማራ መቃብር ስለማድረግ የትግራይን ወጣቶች ይቀሰቅሳል። በርግጥ አባይ ወልዱ ትናንት ያስተላለፈው ተጠንቀቅ ከዛሬ አርባ አንድ አመታት በፊት ወያኔ ጫካ ውስጥ እያለ ማኒፌስቶው ላይ ካሰፈረው አማራን የማጥፋት ፕሮጀክት የተለየ አይደለም።

ትናትና ማታ ደግሞ «ወልቃይት በታሪክም የትግራይ ስለሆነ፤ የወልቃይት ህዝብ ለትግሬነቱ ሲታገል የኖረ ህዝብ ስለሆነ፤ በኢሀፓ የተጨፈጨፈ ህዝብ ስለሆነ፤ ትምክህተኞችን ልካቸውን ለመስጠት» የትግራይ ህዝብ ከመንግት ጋር ጎን እንዲቆም ጥሪ አርቧል።

ወያኔዎቹ እነ አባይ ወልዱ ከጫካ ቢወጡም ከሰው አውሬነት ሊወጡ አልቻሉም። ዛሬም አማራን ስለመቅበር ለወጣቶች ያስተምራሉ። እነሱ እንደዚህ በአደባባይ ወጣቶቻቸው አማራን ለመጨፍጨፍ ትዕዛዝ ሲሰጡ አማራ ዝም ብሎ የሚጠብቃቸው ይመስላቸዋል። ከአሁን በኋላ ግን የዘሩትን ያጭዳሉ። ታሪክ ምስርክ ነው። ግብዞቹና ግዝቦቹ ካወጁብን ጦርነት ራስን መከላከል ያባት ነው!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.