አሁንም የትግራይ ህዝብ ጠላት የአማራ ህዝብ ነው ይሉናል!!![ናትናኤል አስመላሽ]

somali pres - satena news 04የሶማሌ ክልል ፕረዚደንት አሁን በተፈጠረ ህዝባዊ አመጽ ከአማራ ክልል ለተፈናቀሉ የትግራይ ተወላጆች አስር ሚልዮም ብር ድጋፍ መስጠታቸውን ሰማን። ይህ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለማንም ድብቅ አይደለም!!! በህውሓት ቁጥጥር ስር የነበረው ያለው ለወደፊቱም የሚኖር የሶማልያ ክልል መንግስት በተዘዋዋሪ በህውሓት አቀናባባሪነት የአማራ ህዝብ የትግራይ ህዝብ ጠላት መሆኑን ስልጣን ከያዙ ቦሃላም አረጋግጠውልናል።

.
ትናንት በህውሓት ለተገደሉት የአማራ እና የኦሮምያ ወጣቶችስ ማን ይድረስላቸው። ትናንት የሚያስተዳድራት ባልዋን ያጣች የአማራ እና የኦሮምያ እናት ልጆችዋን ማን ያሳድግላት? ባለፉት ሃያ አምስት አመታት ከመላው ሃገሪቱ በዘራቸው ብቻ ከደቡብ ክልል ለተፈናቀሉ አማሮች፣ አማሮች ናቹ ደቡብን ልቀቁ ሲባሉ የሶማሊያው ክልል አልሰማ ይሆን? በጋምቤላ ለም የሆነው መሬታቸውን ለህውሓት ባለስልጣናት ተሰጥቶ ከመሬታው እና ከቀያቸውለተፈናቀሉት የጋምቤላ ልጆች ማን ይሆን የደረሰላቸው እና የረዳቸው? ሽፈራው ሽጉጤ አማራቾን ከክልሉ ሲያፈናቅል የህውሓት ጭምብል የለበሰው የሶማሌ ክልል የት ነበር?ኢትዮጲያዊነት የሚገለጸው ስልጣን ላይ ለወጣ በማጎብደድ እና በመስገድ ከሆነ አሁን የሚጨቆነው ህዝብም ነገ ስልጣን እንደሚይዝ ቢገባቹ ምን ነበር።
.
ባሁኑ አጣብቅኝ ጊዜ ተለጣፊ የክልል መሪዎች ህውሓት ከሌለ እኛም የለንም በሚል ፖለቲካ ድጋፋቸውን ለማሳየት አሁንም በትግራይ ህዝብ እየነገዱ ይገኛሉ። ከድጋፊ ጀርባ ማን? ማንን አፈናቀለ፣ለምንስ ተፈናቀለ፣ተፈናቃዮቹ ላይ ምን ያህል ጉዳት ደረሰ የሚለው መስቀለኛ ጥያቄ ምን ብለው ይመልሱት ይሆን? የድጋፉ መልእክት አጭር እና ግልጽ ነው፣ መልእክቱ የአማራ ህዝብ የትግራይን ህዝብ አፈናቀለ ገደለ ነው።
.
በየትኛው ታሪክ ህዝብ ከህዝብ ጋር ተጣልቶ አያቅም። ህውሓቶች በስልጣናቸው ለመቆየት ግን የማያደርጉት ነገር የለም፣ የ አማራ ህዝብን የትግራይን ህዝብ እንደበደለ እንደገደለ አድርገው በሶማልያ ክልል መስተዳዳር በኩል ነግረውናል። የትግራይ ወጣት ሆይ፣አሁንም የህውሓትን መሰሪ ተግባር ዉስጡን ልትፈት ሸው እና ልታውቀው ይገባል።በኢትዮ ኤርትራ ጊዜ ከ ኤርትራ ለተፈናቀሉ የትግራይ ልጆች ስም የተሰበሰበ ገንዘብ የት ገባ(ምንስ ተደረገላቸው)። እስካሁን ድረስ በትግራይ ህዝብ የተሰበሰበ ገንዘብ የት ገባ? የትግራይ ልማት ማህበር ለምን እንደድሮዋ መንቀሳቀስ አልቻለችም። አሁን ከገንዘቡ ጀርባ ያለው ፖለቲካዊ ስህተት እና ደም አቃቢ ታሪክ ሰከን ብለን ማየቱ ያስፈልጋል!!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.