ህውሓት/ኢህዴግ በቆፈረው ጉድጎድ ለመግባት አፋፍ ላይ ነው [ከከልለው ኡርጋ]

Woyane  - satenaw news 4በመላው የሀገራችን ክፍል በተለይም በኦሮምያ እና በአማራ ክልል በተቀሰቀስው የመብት እና የማንነት ጥያቄ ዙርያ የሀገራቸው ጉዳይ ስለሚመለከታቸው ፍፁም ሰላማዊ እና በሰለጠነ በሆነ መልኩ ከሕፃን እስከ አዋቂ ላለፉት ወራቶች ኢትዮጵያዊያን

ልዪነታችውን ወደ ጐን ትተው በአንድ ላይ አንባገነን ሥርዓትን እና የአንድ ብሔር የበላይነት አክትሞ ሁሉም ብሔር፣ብሔረሰቦች በእኩልነት የሚኖሩባት ሥርዓት ለመገንባት በሰላማዊ መንገድ ጥያቄቸውን በማቅረብ ላይ የገኛሉ ነገር ግን የቀረበውን ጥያቄ ወደ ጎን በመተው ሀይል ግጭት ሆን ብሎ ወያኔ ስለቀየረው ዜጎች ግንባራቸውን ለጥይት ሰጥተው ለህዝባቸው መሰዋት በማቅረብ የፍርሃት ቆፈን ሳይሽብባቸው በመታገል ላይ አሉ። የነዚህ ግጭቶች ፣አለመግባባቶች ለሕይወት እና ንብረት ውድመት ዋንኛ መንሴ ሆኖ የሚጠቀሰው በማንአለብኝነት ገደብ የለሽ መንግስታዊ ግፍና በደል እየፈፀመ ያለው ሀገሪቶን በመምራት ላይ የሚገኝው ህውሓት/ኢህዴግነው።

ከዚህ በተጨማሪ በሀገራችን እየተካሄደ ካለው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ባሻገር የብሔርና የዘር ጉዳይ ርዕሠ ጉዳይነቱ ተጠናክሯል፡፡ሰሞኑን የመንግሥት ባለስልጣናትና ካድሬዎቹ “የዘረኝነት ጉዳይ በእጅጉ አሳስቦናል” ሲሉም እየተደመጡ ነው፡፡የኢትዮጵያን ፖለቲካ የሚከታተሉ ብዙዎች ግን ለጉዳዩ ዋነኛ ተጠያቂ የሚያደርጉት ራሱን ኢሕዴግን ሲኾን የሰሞኑንም የኢሕአዴግን ጩኸት እንደ አስገራሚ ትእይንት የሚያዩት ብዙዎች ናቸው። አሁን አሁን ከሌሎች ወገኖችም የሚሰነዘሩት የዘርናየጥላቻ ፖለቲካ ምንጩ ኢሕዴግ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በላይ ሲዘራው የኖረው የፖለቲካ ዘር ፍሬ እንጂ ሌላ ነገር መስሎ የማይታያቸው በቁጥር ቀላል የሚባሉ አይደሉም፡፡ የብሔር/ብሔረሰብን መብት በማስከበር ሽፋን የዘር ጥላቻእንዲቀሰቀስ፣ ክፍፍል እንዲካረር፣ አለመተማመን እንዲሠፍን ገዢው ፓርቲ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በላይ እንቅልፉን አጥቶ መሥራቱን የሚገልጹ ወገኖች ኢሕአዴግ ደርሶ ዘረኝነት አውጋዥ መሆኑ አይዋጥላቸውም፡፡ እንዲያውምበሥልጣን ዘመኑ ሁኔታውን በመጥፎ ጎኑ ሲያቀጣጥል የቆየው ገዢው ፓርቲ ባሻው ወቅት ሁሉ ይሕን መሰሉን ክስ ሌሎች ላይ ሲለጥፍ መታየቱም የተለመደ ባህርይው ሆኖም ይወሰዳል፡፡ የኢሕአዴግ መንግሥት በብሔሮች መካከል አለመተማመን

እንዲፈጠር ቅስቀሳ ከማድረግ አንስቶ የአረካን፣ የበደኖንና የአርባጉጉን በመሰሉ እልቂቶች ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንደነበረም የሚያሳጡት ምስክሮችም ይቀርቡበታል፡፡ የብሔር ብሔረሰቦችን መብት “ላስከብር ተነስቻለሁ” በማለቱ ረገድ ኢሕአዴግ የመጀመሪያው የአገሪቱ መንግሥት አይደለም፡፡ እንዲያውም የፌደራሊዝም አወቃቀር ‘እርሾውን’ ከቀድሞው መንግሥት የብሔረሰቦች ጥናት ኢኒስቲቲዩት እንደወሰደው ነው የሚነገረው። “የብሔረሰብ መብት ማስከበርን ከኔ በላይ ላሳር” የሚለው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሐት) ቁጥጥር ስር መቀፍደዱ የፕሮፓጋንዳውን ያህል የሌሎች ብሔረሰቦችን መብት ጉዳይ ትርጉም ባለው ሁኔታ ለማንሳት እንዳላስቻለውም ይገመታል፡፡“…በነጻ ፍላጎትና በሕግ የበላይነት አንድ የፖለቲካ ማሕበረሰብ በጋራ የመገንባት” ሐሳብ እንደያዘ የሚነገርለትን ሕገ መንግስት ይዞም ከሩብ ክፍለ ዘመን በኋላ እንኳ ወሳኝ የሆኑ የሥልጣን ቦታዎችን ለሌሎች ለማካፈል ያለው ፍላጎት አነስተኛ መሆኑም አገዛዙን የሚያሳማው ጉዳይ ነው። “መጪው የጋራ ዕድላችን መመስረት ያለበት ከታሪካችን የወረስነውን የተዛባ ግንኙነት በማረምና የጋራ ጥቅምን በማሳደግ ላይ ነው” የሚለውን በሠነድ እንዲሰፍር ቢያደርግም የጋራ ጥቅምን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን ለማድመጥ ዝግጁ አይመስልም፡፡“…ጥቅማችን፣ መብታችንና ነጻነታችንን በጋራ እና በተደጋጋፊነት ለማሳደግ አንድ የኢኮኖሚ ማሕበረሰብ መገንባት አስፈላጊ ነው” የሚለውም እዚያው ሕገ መንግሥቱ የታተመበት ወረቀትላይ ብቻ እንዲወሰን አድርጎታል፡፡ እነዚህኑ መብቶች በመጠየቃቸው ምክንያትም ዜጎች ይታሠራሉ፤ ይገደላሉ፤ ለእንግልትና ለስደት ይዳረጋሉ፡፡ ኢሕአዴግ ልዩነትን በማስፋት፣ ጥርጣሬና ፍርሃትን በማንገሥ መንገዱ ዘልቆበታል፤ የገዢው ፓርቲማዕከላዊ ኮሚቴ ከሰሞኑ ለአራት ቀናት በዝግ ያካሄደውን ስብሰባ ሲያጠናቅቅ ባወጣው መግለጫም ዘረኝነት የአገሪቱ ሥጋት ነው ብሏል፡፡ ተቃዋሚዎች ግን ዘረኝነትን በማቀጣጠል፣ አየሩ በጥርጣሬና ፍርሃት እንዲሞላ፣ አንድነት እንዲናጋ በማድረጉ ረገድ የኢሕአዴግን ያሕል የደከመም የተሳካለትም የለም ነው የሚሉት፡፡ኢሕአዴግ በሥልጣን ዘመኑ ይህን በተመለከተ የሚነቀፍበት ብዙ ምሳሌዎችም እዚህ ላይ ይጠቀሳሉ፡፡ ብዙዎች ከማይዘነጉት የአክሱም ሐውልት ለወላይታው ምኑነው ከሚለው አባባል ባሻገር በኢሕዴግ ዘመን ከጋራ እሴቶች ይልቅ ልዩነት ላይ ትኩረት እንዲደረግ የተሰሩ ብዙ ስራዎች መኖራቸው ተደጋግሞ ይጠቀሳል። ዩኒቨርሲቲዎችና ከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት የአገዛዙ ልዩነት መፍጠሪያ

ዋና ማዕከላት ተደርገዋል፤ ተማሪዎች ከክልላቸው ውጪ ሃገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ እንዳያተኩሩ ገደብ ይደረግባቸዋል፡፡ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ስለ ሃገራዊ ትስስርና አንድነት ትንፍሽ አይሉም፡፡ በብሔራዊና አብይ በዓላት አከባበር እንኳ የክልል ቴሌቪዥኖችና ሬዲዮ ጣቢያዎች ከክልላቸው አርቀው እንዳይመለከቱ ተደርገዋል፡፡ በብሔር ብሔረሰቦች በዓል ሳይቀር ደም አፋሳሽ ግጭቶች መቀጣጠላቸውም ተስተውሏል፡፡ ኢሕአዴግ በመታወቂያ ካርድ ላይ ብሔር እንዲሠፍር ያደረገበት አካሄድ አደጋ ይደቅናል ያሉ ብዙዎች ነበሩ። አደጋው አሁን በመጠኑ ብልጭ እያለ ነው፡፡ በሩዋንዳ እልቂት ወቅት በመታወቂያ ላይ ብሔር እንዲሠፍር መደረጉ አንዱ የችግሩ ማቀጣጠያ እንደነበር የሚያወሱ ብዙዎች በኢትዮጵያም ይህንኑ ብሔርን በመታወቂያ የመጻፍ አስገዳጅነት በስጋት ያዩታል፡፡ በቅርቡ በአዲስ አበባ ለተቃውሞ ሠልፍ የወጡ የኦሮሞ ተወላጆች በመታወቂያ ካርዳቸው ላይ በሠፈረ የብሔር ማንነት እየተነጠሉ ለጥቃት እንደተዳረጉም ሲነገር ሰንብቷል፡፡ ከሠሞኑ በአዲስ አበባየሚገኙ ሆቴሎችና ፔኒሲዮኖች በተላለፈላቸው ትዕዛዝ ከአማራ ክልል የሚመጡ አዳዲስ እንግዶችን ጠቁሙ የተባሉትም ከመታወቂያ ካርድ በሚገኝ መረጃ ነው፡፡ ዘረኝነትን እያወገዝኩ ነው የሚለው ኢሕአዴግ በተግባር ተቃራኒውን ሲፈጽምም ይስተዋላል፡፡ በጎንደር አካባቢ ተቃውሞ በጀመረ ሰሞን መንግሥት በጸጥታ ክፍሉ አማካይነት ባወጣው መግለጫ… በአንድ ብሔር ላይ ጥቃት ተሰንዝሮ እንደነበር ነው የገለጸው። የአማራ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ኃላፊ በበኩላቸው በተካሄደ ማጣራት በዘር ላይ የተነጣጠረ ጥቃት እንዳልነበር ጠቆሙ፡፡ እንዲህ ያለው አደገኛ ጉዳይ በመንግሥት ሲገለጽ አደጋና ሥጋቱ ከፍ ያለ ይሆናል፡፡ እዚያው ጎንደር አካባቢ ከሕዝቡ ጋር በነበረው ግጭት ላይ ሕይወታቸው ያለፈውን የጸጥታ ሰዎችስማቸውን መግለጽ በቂ ሆኖ ሳለ… ብሔረሰባቸው ጭምር ተዘርዝሮ እንዲጠቀስ የተደረገበት አካሄድም “…የተገደሉት የእከሌ ብሔር ተወላጆች ናቸው” የሚል አቀጣጣይ አጀንዳ እንዲኖር ተፈልጎ ሳይሆን እንዳልቀረ የሚገምቱ አልጠፉም፡፡የኢሕአዴግ ካድሬ መሆናቸው የሚታወቁ ሰዎች ከሰሞኑ በማሕበራዊ ሚዲያዎች “የኦሮሞ ተቃውሞ ትክክለኛ ነው፤ የአማራ ተቃውሞ ሕገ ወጥ ነው” በሚል መልዕክት መጠመዳቸውም ክፍፍል የመፍጠሩ ሌላ አካሄድ እንደሆነ የሚጠረጥሩም አሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ዘር ላይ ያነጣጠረ አሉታዊ ቅስቀሳ እየጨመረ መምጣቱን የሚገልጹ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ሆኖም ግን በተቃዋሚዎች ስም በማሕበራዊ ድረ ገጾች ይሕ ዓይነቱ የዘር ጥላቻ ቅስቀሳ እየተሠነዘረ የሚገኘው ከአገዛዙ ካድሬዎች ሠፈር መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

አሁን የኦሮሞ ሕዝብም ይሁን የሌሎች የመላው ሀገሪቶ ብሔር /ብሔረሰቦች መሰረታዊ እና ዋናኝ ጥያቄ የመብትና ዲሞክራሲ ስለሆነ ስር ነቀል የስርዓት ለውጥ ና ከአንባገነን ነፃ የመሆን የነፃነት ጥያቄ ነው።
ድል ለጭቁኑ ሕዝብ!!
ከከልለው ኡርጋ
kiyu297@gmail.com

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.