ሁላችንም ነፃ እስክንወጣ እንቁጣጣሽን ከአእምሯችን እናውጣ!! ሀዘን ላይ ነን!!!

14322757_1190219394369069_3853230140470559572_n

።።።።የሰውየው ትዝብት በዘመነ 2008።።።።።
፩ኛ/ አሸባሪ ህግ እንጂ አሸባሪ ሰው የለም።
፪ኛ/ የስኳር በሽታ እንጂ የስኳር ምርት የለም።
፫ኛ/ ስጋት እንጂ ስጋ የለም።
፭ኛ/ ወጪ እነጂ ትርፍ የለም።
፮ኛ/ ማዕረግ እንጂ እውቀት የለም።
፯ኛ/ እስር ቤት ውስጥ ምሁር እንጂ ታራሚ የለም።
፰ኛ/ ወሬ እንጂ ተግባር የለም።
፱ኛ/ ቧንቧ እንጂ ውኃ የለም።
፲ኛ/ ቆጣሪ እንጂ ኤሌክትሪክ የለም።
፲፩ኛ/ ሃብታም ባለስልጣን እንጂ ሃብታም ህዝብ የለም።
፲፪ኛ/ አናዳጅ እንጅ ነዳጅ የለም።
፲፫ኛ/ ግብር እንጂ ገቢ የለም።
፲፬ኛ/ ሃሳብ እንጂ አሳ የለም።
፲፭ኛ/ ያገባ እንጂ የተግባባ የለም።
፲፮ኛ/ ቅዠት እንጂ ራዕይ የለም።
፲፯ኛ/ ወላጅ እንጂ አሳዳጊ የለም
፲፰ኛ/ በቀን ፫ ጊዜ የሚያዛጋ እንጅ በቀን ፫ ጊዜ የሚበላ የለም።
፲፱ኛ/ ድብደባ እንጂ ዳቦ የለም።
፳ኛ/ ዘረኝነት እንጂ ኢትዮጵያዊነት የለም።
፳፩ኛ/ ቤተመንግስት እንጂ መንግስት የለም።
፳፪ኛ/ አፍ መክፈት እንጂ መፅሀፍ መክፈት የለም።
፳፫ኛ/ የኮንደም ጥራት እንጂ የኮንደሚንየም ጥራት የለም።
፳፭ኛ/ ፍርድቤት እንጂ ዳኛ የለም።
፳፮ኛ/ ሙስና እንጂ መስኖ የለም።
፳፯ኛ/ ኃ/ማርያምን ሲያታልሏት ጠቅላይ ሚኒስቴር አሏት።
፳፰ኛ/ ትንሹ መሪያችን እንጂ ታላቁ መርያችን ገና አልተወለደም።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.