ዐማራን ትጥቅ ለማስፈታት አንድ ግብረ ኃይል ተቋቋመ

Amhara Fighterየዐማራን ሕዝብ ትጥቅ ለማስፈታት በወያኔ የሚመራ አንድ ግብረ ኃይል መቋቋሙን ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ሰማን፡፡ ግብረ ኃይሉ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት፣ የፌደራል ፖሊስና መከላከያን ያከተተ ነው፡፡ ይህ ግበረ ኃይል በዐማራ ክልል የጸጥታ ዘርፍ ቢሮ ፈቃድ የሰጣቸውን ወይም ደግሞ መሣሪያቸውን ሕጋዊ ያደረገላቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር በወረዳና በቀበሌ ለይቶ እንዲልክ በግልጽ ጠይቋል፡፡

ብአዴን በምክር ቤት ያወጣውን አዋጅ ሕወሓት ምን ታመጣለህ ብሎ ሲጥስበት በዐይኑ እያየ ከሕዝብ ጋር ሊቆም አይደለም ዐማራውን ትጥቅ ለማስፈታት የወያኔ ፊታውራሪ እንዲሆን ሲታጭ ምንም ተቃውሞ አላቀረበም፡፡ ሰሞኑን በምዕራብ ጎጃም መራዊና በጎንደር ከተማ አካባቢ የተወሰኑ ሰዎች መሣሪያቸውን ሲነጠቁ ብአዴን የአህያ ባል መሆኑን በተግባር አሳይቷል፡፡
ይህ ግብረ ኃይል መሣሪያ ያላቸውን ዐማሮች በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት የመረጃ ቋት ውስጥ በጥናት ለመመዝገብና በዚሁም መሰረት እርምጃ ለመውሰድ ከክልሉ የሚላከው ዳታ መነሻ አድርገው ጥናቱን የሚመሩና የሚያስፈጽሙ ወያኔዎች ተሰይመዋል፡፡ በዚህ ሒደት ቅጥረኛ የሆኑ ዐማሮች እንዳሉበትም አውቀናል፡፡ ግብረ ኃይሉን በበላይነት የሚመራው የወያኔ የግል ቤት የሆነው ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ባለሥልጣን ነው፡፡

ይህን መረጃ ካቀረብን በኋላ ይህ እቅድ ተግባራዊ ሊሆን ይችላል ወይ የሚለውን ማየት አስፈላጊ ይመስላል፡፡ ወያኔዎች የዐማራው ሕዝብ ላይ ማንኛውንም እርምጃ ለመውሰድ ወደ ኋላ አይሉም፡፡ ነገር ግን ይህ እቅድ እንዲኮላሽ የእኛ የዐማራው ልጆች ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ ዝም ካልን የማይተገበርበት ምክንያት የለም፡፡ ቅጥረኛ ባንዳ ካልሆነ በስተቀር ይህ እንዲሆን የሚሻ ዐማራ አይኖርም፡፡

ስለዚህ እኛ የዐማራው ሕልውና ያሳስበናል የምንል የዐማራው ተወላጆችና ወዳጆች በአገር ቤት ያሉ ዐማሮች መሣሪያቸውን ሊቀማ የሚመጣውን ማንኛውንም ኃይል ዝም ብለው መመልከት እንደሌለባቸው ማስገንዘብ ይኖርብናል፡፡ መሣሪያው ተመዘገበ አልተመዘገበ፤ ሕጋዊ ነው ወይም አይደለም የሚል ጨዋታ በወያኔዎች ዘንድ የለም፡፡
ስለዚህ መሣሪያ ያላችሁ ሰዎች ከጎበዝ አለቆች ጋር ያላችሁን ግንኙነት ማጠንከር አለባችሁ፡፡ መሣሪያ የሌላቸው ዐማሮች ደግሞ የመጣው ጊዜ የከፋ መሆኑን በመገንዘብ ያላችሁን ማንኛውንም ጥሪት አሟጣችሁ ቢሆን መሣሪያ ለመያዝ መንቀሳቀስ አለባችሁ፡፡ አሊያ ግን ከትግራይ የበቀሉት ጥቁር ፋሽቶች የዐማራውን ደም ለማፍሰስ ወደ ኋላ አይሉም፡፡ ዐማራው በተደራጀ መልኩ ሁሌም በተጠንቀቅ መቆም አለበት፡፡

የዐማራው ተጋድሎ የማይቆምና እስከ ነጻነትም ወደ ፊት የሚሔድ መሆኑን በመገንዘብ በመደራጀት ራሳችሁን ተከላከሉ፡፡
(መረጃውን በተቻላችሁ ሁሉ በማባዛት የዐማራው ተጋድሎ አካል ይሁኑ)

የዐማራ ተጋድሎን የሚቀለብስም ምንም ዓይነት ምድራዊ ኃይል የለም!!

#AmharaResistance;

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.