አዲስ የቂልንጦ እስር ቤት ጉድ

መሃል አዲስ አበባ ልጁ የታሰረው ከስድስት ወር በፊት ነው።በሰፈሩ ጨዋ ልጅ ነው።በመጨረሻም አስከሬኑን መጥታችሁ ውሰዱ ተብለው እናት ተጠርተው አስከሬኑን እንዳትከፍቱ ብለው አስፈርመው ሰጧቸው።
አስከሬኑ ሲመጣም ሆነ እስኪ ቀበር ድረስ ሁለት ፖሊስ እና ሁለት ደህንነት ተመድቦ ሌሊቱን ከአስከሬኑ ጋር አድረው እስከ ቀበር ድረስ ፖሊሶቹ እና ደህንነቶቹ ቆይተው ሄዱ።እናት ቆይቶ ጉዳይ ይከነክናቸውና ምሽት ላይ ቤተሰብ የቤተክርስቲያኑን ዘበኛ እባክህ ከልጃችን ጋር የተቀበረ ሀብል አለ ሲቢንቶም ይቀራል በሚል በገንዘብ ለምነው ምሽት ላይ አስከሬኑን ቆፍረው አውጥተው ሲመለከቱ ከአንገቱ በታች በጥይት በሳስተውታል። አንገቱ ላይ ጥቁር ነገር አለ።እናት ፎቶ አንስተው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፈርደኛል ብለው ይዘውታል።ሰፈሩ ሁሉ እድሩ ሁሉ ሃዘን ላይ ነን ….ሙሉ ቃሉን የኢሳት ራድዮ ማክሰኞ መስከረም 3/2009 ዓም ያስተላለፈው የቂልንጦ ጉዳይ የሚመለከተውን ክፍል ብቻ ከስር ያዳምጡ።

Comments are closed.