የኦሮሞ እና አማራ ወደመተባበር መሄድ ህወሓትን አስደንግጦታል” [ካሳሁን ይልማ]

Unityበኢትዮጵያ ከሚገኙ የእስልምና አክራሪ ቡድኖች ጋር በመስራት በሳውዲ ኤምባሲ በኩል ብር ሲያዘዋውሩ፣ መስጊድ ሊያሰሩ፣ ህገመንግስቱንና ህገመንግሥታዊ ሥርዓቱን በህገወጥ መንገድ ለማፈራረስ ሙከራ ሲያደርጉ ተይዘዋል …ተብለው ህወሓት ባሌበታቸውን ወይዘሮ ሐቢባን አዋርዶ እሳቸውን አኝኮ የወረወራቸው የቀድሞው የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት አቶ ጁነዲን ሳዶ ብቅ ብለዋል።
አፍሪካ አርግዩመንትስ በተባለ ድረ_ገጽ ላይ ለመጀመርያ ጊዜ ተንፍሰዋል።በጽሑፋቸው በአሁኑ ሰዐት የኦሮሞና አማራ ሕዝብ የሚያደርገው ተጋድሎ የሚያስገርም እንዳልሆነ ጽፈዋል። ለዛሬው ቀውስ ምክንያት ከሽግግር መንግስቱ ጀምሮ የነበረውን ሂደት አጠር አድርገው ዳስሰዋል።
ጁነዲን ህወሓት ሁለቱን ትልቅ ብሔሮች አማራንና ኦሮሞን ሆን ብሎ እና በተሰላ ዘዴ እንዳገለለ ገልጸዋል (The eruption of mass protests in the two largest regions of Oromia and Amhara was inevitable as these communities have been deliberately and systematically marginalised) በአሁን ሰዐት እነዚህ ሁለት ብሔሮች አረመኔው ስርዓት ላይ በጋራ በመነሳት ወደመተባበር መሄዳቸው እንዳስደነገጠው አብራርተዋል (The brutal response of the regime is also in keeping with its paranoia about the rise of either the Oromo or Amhara against Tigrayan domination or of the alliance between the two)
ህወሓት የማይለወጥና ለለውጥ ፍላጎት የሌለው ነው ብለዋል። መለስ ሞቶ እንኳ አምጠው ከወር በኋላ የሾሙት ኃይለማርያም ስልጣኑን ከርክመው፣ ጎማምደው ባዶ እንዳስቀሩት በማስረጃነት ያቀርባሉ።
*አቶ ጁነዲን የስርዓቱ አካል ነበሩ፣ የሚጠየቁባቸውም ወንጀሎች ይኖራሉ። ህወሓት ገፍቷቸውም ቢሆን ከወጡ በኋላ ከዝምታ ይልቅ ስለስርዓቱ የሚያውቁትን መጻፋቸው ጥሩ ነው። ኃጢያታቸውን ተናዘው ንስሐ ይገባሉ ብለን ተሰፋ እናደርጋለን

[ካሳሁን ይልማ]

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.