አርተስት መላኩ ቢረዳ በወልቂጤ ከተማ ለመስቀል ሊያቀርብ የነበረውን ኮነሰርት ሰርዞ የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፏል!

melaku-satenaw-news-7
መላኩ ቢረዳ

ስላም ውድ ወገኖቼ በመላው አለም ያላችሁ ኢትዮጵያዊያን እንደ ክፉ ልማድ ሰላም ቢሆንም ባይሆን ስንገናኝ ሰላም ነው የሚሉት ሶስቱ ፊደላት ልማዳችን ሆነዋል።

    መልእክቴ ይህ ነው በበቅርቡ ሙሉ ገቢው ለሶስት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የሚውል ሙሉ አልበም ስርቼ መጨረሴ ይታወቃል ። ሆኖም ከፈጣሪ ቀጥሎ አስታዋሽ ባልበረኝ ሰአት ከጎዳና አንስተህ አልብሰህ አጉርሰህ አስተምረህ ላሳደከኝ ውድ የኢትዮጵያ ህዝብ ደስታህ ደሰታዬ ሀዘንህ ሀዘኔ ካልሆነ ምኑ ያንተ ልጅ ሆንኩት ። በተጨማሪም ከመስከረም 5/1/2009 ጀምሮ ለመስቀል በአል በወልቂጤ ከተማ ላይ በሚደረጉ የሙዚቃ ባዛርና ኮንሰርቶች በምንም መልኩ በሙዚቃ ዝግጅቱ ላይ ስለማልሳተፍ እባካችሁ ፕሮሞተሮች ያለፍላጎቴ ፎቶዬን በፖስተር በማሳተም ሰውን አታደናግሩ።ይህ የፖለቲካ ጉዳይ አይደለም ይህ የእምቢተኝነት ጉዳይ አይደለም ።ይህ የህሊና ጉዳይ ነው  ።

ገንዘብ እድሜም እውቀትም ችሎታም ሁሉም አላፊ ነው ። ግን የአለም ፍፃሜ እስኪደርስ ሀገርና ህዝብ ዘላለማዊ ነው። ይህ ቁጥር ሶስት አልበሜ ሀገራችን ሰላም ፣ ህዝባች ሰላም እሲኮሆን ሳይሸጥ መቆየቱ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ከገባሁት ቃሌ ይልቅ ህዝቤና ሀገሬ ሰለላቀብኝ ነውና እንዴትስ ወገኔን ህይወቱን ማንነቱን ሰላሙን እያጣ ሀገሬ አዝና ወገኔ እንካ በአዲሱ አልበሜ ጨፍር ተዝናና እንዴት ልለው እችላለሁ። ሰላም ሰላም ሰላም ለኢትዮጵያንና ለኢትዮጵያዊያን።

መላኩ ቢረዳ ።

ዝም አልልም

ጭለማ ላይ ሆኜ ብርሀኑን አየሁት፣
ጭለማ ላይ ሆኜ አንዳርጌን አየሁት፣
ጭለማ ላይ ሆኜ ታደሰን አየሁት፣
መቼ ይነጋል ብዬ እራሴን ጠየቅኩት፣
ብርሀኑም ነጋና ቀኑን ባይኔ አየሁት።

ሀብትና ገንዘብ ደስታን አያመጣም
ህሊናዬ ሽጨ እራሴን አልቀጣም
ነፍሼ አልኖርም ወደ ነፈሰበት
ህሊና ዳኛ ነው ፀፀት የሌለበት

የነገው ስንቄ ይህ ነው ማንነቴ
አንድነሽ ኢትዮጵያ ምድራዊ ገነቴ
ዝም አልልም ባንድ አንቺ ለመጣ
ካለበት ጨለማ ብርሀኑ እስኪወጣ።

መላኩ ቢረዳ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.