የማለደ ወግ … ክበረ ነክ ፣ ጸያፍ ስድብ በመንግሥት ቴሌቪዥን ! [ነቢዩ ሲራክ ]

1435-satenaw-news* ቴሌቪዥኑ ከዘባተሎ ፖለቲካ መረጃ ቅበላ ወደ ብሽሽቅ መድረክነት

በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩው የኢትዮጵያ ሶማሌ ዲያስፖራዎች የወያኔ / ኢህአዴግን መንግሥት ደግፈው ፣ ግንቦት 7 እነ ኦነግን ተቃውመው ሰልፍ መውጣታቸውን ሰምተናል ። በዚሁ ሰልፍ ይዘውት የወጡት መፈክርን የያዘውን ክበረ ነክና ጸያፍ ስድብ ከትናንት ምሽት ጀምሮ በማህበራዊ ድረ ገጾችና በፊስ ቡክ ሲሰራጭ ተመልክተናል ። ምራቃቸውን የዋጡ አባቶች ፣ ወንድሞች ሂጃብ ያደረጉ የኢትዮ ሴቶች የተካተቱበት የድጋፍና ተቃውሞ ሰልፍ ይዘውት የወጡት” ኦነግ ተ… ዳ !” የሚለውን መፈክር ይገኝበታል ፣ ደጋግሜ አይቸው ማመን እቅቶኝም ነበር ። ወደ ኋላ ግን እርጠኝነቱን ስረዳ እዝነ ልቦና ያለው ያደርገዋል በማልለው ስድብ አዘል መፈክር ለእነሱ እኔ እስከ መሸማቀቅ ደርሻለሁ ፣ ያሳፍራል ፣ ያሳዝናል 🙁

ዛሬ እኩለ ቀን ደግሞ ክበረ ነክ ፣ ጸያፍ ስድቡ በመንግሥት ቴሌቪዥን ላይ ቀርቦ ስመለከተው ደግሞ ይበልጥ ተሸማቀቅኩ ፣ አዘንኩ 🙁 የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ተገቢ የልሆነ መረጃ ለመሰራጨቱ አዲስ ባይሆንም ” ኦነግ ተ… ዳ !” ብሎ የተጻፈን ነውረኛ መልዕክት በህዝቡ በሚደጎም ጣቢያ ማሳዬት ትልቁ የመንግሥት ተቋም ምን ያህል በዘቀጠ አስተደደር እንደሚመራ በገሃድ ያሳይ ይመስለኛል ።

በመንግሥት ቴሌቪዥን ይህን መሰል ጸያፍና ተገቢ ያልሆነ ተራና የወረደ የወሮበላ ስድብ ማስተናገዱ ያስቆጫል ። ይህም የመንግሥት ቴሌቪዥኑ ወደ ከተራ የተዛባ ዘባተሎ ፖለቲካ መረጃ ቅበላ ወደ ብሽሽቅ መድረክነት እየቀየረው መሆኑ በእርግጥም እንደ ዜጋ ያስቆጫል … በዚህች ሀገር የሰው ሰብአዊ መብት በጠመንጃ ሲጣስ ብቻ ሳይሆን ክብረ ነክ ጸያፍ የሚባል ነውር በአደባባይ ሲናኝ ” ተው ” ባይ ሽማግሌ ጠፍቶ እንዲህ መባዘናችን ልብ ይሰብራለረ ያማል 🙁

እስኪ ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ
መስከረም 9 ቀን 2009 ዓም

1 COMMENT

  1. TPLF, please die peaceful death!
    Stop further ruining our history, centuries build names/cultures!

    It is better for TPLF to die now than latter!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.