ዛሬ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ፣ የወያኔ ተላላኪዎች ቢገባቸው ብሎ አንድ መምህር የሚከተለውን ተረት ተረተላቸው

haramaya-university
አንድ ያረጀች አሮጊት፣ ወጣት መሆን አማራት አላቸው። ወደ ወጣትነቷ ለመመለስ ሰዎችን ማማከር ጀመረች። ሰዎችም እንደሚከተለው ምክር ለገሷት፡ የመጀመሪያ መካሪዋ፡
“አንቺ አንዴ አርጅተሻል፣ ወደ ወጣትነትሽ መመለስ አይቻልሽም” አሏት። አሮጊቷ ወጣት የመሆን ፍላጎቷ ከፍተኛ ስለሆነ ሃኪሞችን ለማማከር ወሰነች። በዚሁ መሠረት አሮጊቷ መጀመሪያ የሄደችው ለሆዳቸው ያደሩና ሞያዊ ስነምግባር የማያውቁ ሃኪሞችን ዘንድ ነበር፤ እነሱም እንዲህ አሏት “አንቺ ወደ ወጣትነትሽ መመለስ ትችያለሽ፣ ለዚህም ደግሞ ይሄን፣ ይሄን መድሀኒት ውሰጂ” አሏት። በዚሁ መሠረት አሮጊቷ የታዘዘላትን መድሀኒት ብትውጥ፣ ብትውጥ፣ ወጣት መሆን አልቻለችም። አሮጊቷ በዚህም ተስፋ አልቆረጠችም የመጨረሻ እድሏን ለመሞከር ወደ ፕሮፌሽናል ሃኪሞች ዘንድ ተጓዘች፤ እነሱንም እንደዚህ አለች “የእርጅናዬ ነገር በጣም አሳስቦኛል፣ ወደ ወጣትነቴ ዘመን መመለስ እፈልጋለሁ፣ ለዚህም ደግሞ ሞያዊ ምክራችሁን ለግሱኝ” ብላ ጠየቀቻቸው።

እነሱም እንዲህ አሏት “እኛ እንደ ፕሮፌሽናል እርጅናሽ ምልክት የሆነውን ሽበትሽን ከማድነቅ ውጪ፣ ወደ ወጣትነትሽ ዘመን ትመለሺ ዘንድ የምናዝልሽ መድሀኒት የለም” አሏት።
በተመሳሳይ ኢህአዴግም ከእርጅናው ለመላቀቅ መፍትሄ ወይም ምክር ከኛ ከፕሮፌሽናሎቹ መምህራን የሚፈልግ ከሆነ መልሳችን አንድ ነው፤ እሱም “የኢህአዴግን እርጅናን ከማድነቅ ውጪ እሱ እንዲታደስ የምንለግሰው ምክር የለንም” አላቸው።”

#OromoProtests

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.